በማህበር የተደራጁ ነዋሪዎች ያቀረቡት የኃይል ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ ነው
የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ወጪ ከፍለው ሲጠባበቁ የነበሩ ሦስት ማኅበሮች በቀጣይ ሳምንት ውስጥ ያቀረቡት የኃይል ጥያቄ ምላሽ ሊያገኝ መሆኑን የባህር-ዳር ሪጅን ቁጥር 3 አገልግሎት መስጫ ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ አዲሱ ፈረደ አስታወቁ፡፡
ማኅበራቱ በዘነዘልማ ከተማ በመቶ ካሬ ሜትር ተደራጅተው በኤቢሲ ገመድ፣ በትራንስፎርመር እና በምሶሶ እጥረት ለአምስት ወራት ሲጠባበቁ የቆዩ ናቸው ብለዋል፡፡
በአጠቃላይ በዘንዘለማ መንደር በሦስት ማኅበራት ተደራጅተው አዲስ ሃይል ሲጠባበቁ የነበሩ 497 ነዋሪዎች መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የማዕከሉ ስራ አስኪያጅ በሚቀጥለው ሳምንት 8 ሺህ 9 መቶ ሜትር የኤቢሲ ኬብል በማሟላት የማህበራቱ የሃይል ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ አስታውቀዋል፡፡
በማዕከሉ የዘንዘልማ ነዋሪዎችን የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ የአንድ ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ የተደረገ ሲሆን 14 ምሰሶ መተከሉንም ተናግረዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ አክለውም 2 ሺህ ሜትር ኤ.ቢ.ሲ የኤሌክትሪክ ሽቦ በቄስ እሸቴ ስም ለተደራጁ 127 አባወራዎች ተዘርግቷል ብለዋል፡፡
በቄስ እሸቴ ስር ለተደራጁ ማኅበራት ቀሪ 1 ሺህ 500 ሜትር ኤቢሲ የኤሌክትሪክ ሽቦ እስከ ሰኞ የአቅርቦት ችግሩ ተቀርፎ ኤሌክትሪክ የሚያገኙ ይሆናል፡፡
በአቶ ኑርልኝ ስም የተደራጁት ማኅበራት በቀጣይ ማክሰኞ ኤሌክትሪክ እንደሚያገኙ ተገልፆ በአቶ መእረ ስም ለተደራጀው ማኅበር ደግሞ ትራንስፎርመር ለማቅረብ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት