የከሰም ስኳር ፋብሪካ በሚታየው መልኩ በመሬት መንቀጥቀጡ ተጎድቷል፣ ከ400 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር በላይ ውሀ የያዘው እና ለስኳር ፋብሪካው ግብአት የሚሆነውን የሸንኮራ አገዳ ለማልማት የተሰራው ግዙፉ የከሰም ግድብ ያለበት ሁኔታ ግልፅ አይደለም
የዛሬ ሶስት ወር ገደማ የፃፍኩትን መልሼ ላጋራው ⬇️
ከሰሞኑ ከሚያባንኑኝ ጉዳዮች አንዱ በቅርብ ቀናት አዋሽ አካባቢ የተከሰተው ርዕደ መሬት እና አያድርስ እና ከፍ ያለ መጠን ያለው መንቀጥቀጥ ቢከሰት በአካባቢው ያሉ ግድቦች ላይ መደርመስ አስከትሎ ዜጎች ላይ ሊያደርስ የሚችለው ጉዳት ነው።
በአካባቢው ያለው ግዙፉ የከሰም ግድብ ላይ ጉዳት ቢደርስ ሊለቀው የሚችለው ግዙፍ የውሀ መጠን በታችኛው ተፋሰስ ላይ ያሉ ዜጎችን ሊውጥ ይችላል።
"ግድቡ በክረምቱ ወቅት ግዙፍ የውሀ መጠን ይዞ ይገኛል፣ አደጋ ቢከሰት ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለማሰብ ይከብዳል" ያሉኝ አንድ ባለሙያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም ለአደጋው ተጋልጠው ይገኛሉ ብለዋል።
አደጋ ከደረሰ በኋላ "ብዬ ነበር" ማለት ወይም ከንፈር መምጠጥ ዋጋ የለውም፣ ስለዚህ ሌላው አለም ላይ እንደሚደረገው ቢያንስ ሁኔታው በደንብ እስኪጠና ተጋላጭ ወገኖችን ወደ ሌላ ቦታ ማስፈር ቢቻል እጅግ መልካም ነው።
እባካችሁ የሚመለከታችሁ አካላት ትኩረት፣ ትኩረት፣ ትኩረት!
Photo: Tamiru Huliso
@EliasMeseret