ከጥቂት ሳምንታት በፊት መሠረት ሚድያ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ሊቀነሱ እንደሆነ መረጃ አቅርቦ ነበር
መረጃው በወጣ በነጋታው የመንግስት ሀላፊዎች ተሯሩጠው "ውሸት ነው፣ አዲስ የፀደቀው የሰራተኞች አዋጅ ተቋማት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲፈፅሙ የሚያስችል ብቻ ነው" ብለው ነበር።
ዛሬስ?
እንደ አንበሳ አውቶቡስ አገልግሎት፣ ፖስታ አገልግሎት፣ የተለያዩ የክፍለ ከተማ ፅህፈት ቤቶች... ወዘተ በመቶዎች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ማሰናበት ጀምረዋል።
በዚህ ሳምንት ብቻ 450 የፖስታ አገልግሎት ሰራተኞች "በሪፎርም ምክንያት" በሚል ከስራቸው ተነስተው በሌሎች ተተክተዋል፣ ድርጊቱ በዘመድ፣ በእውቅ እና በብሄር ተለይቶ እንደሆነ ሰራተኞቹ ነግረውኛል።
አሁን በዚህ የኑሮ ውድነት የእነዚህ ሰራተኞች እና ቤተሰብ እጣ ምንድን ነው? ጎዳና ላይ መውጣት?
@EliasMeseret