ጋራ ብዙ ጊዜ አስቀምጠውት ቆይተዋል፡፡ መስቀሉ በእንጦጦ ጋራ ሳለ እግዚአብሔር አምላክ “አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል፤ መስቀሌን በመስቀለኛ ተራራ ላይ አስቀምጥ” የሚል ቃል ለንጉሡ በራእይ ነገራቸው፡፡ ንጉሡና ሠራዊታቸው በእግዚአብሔር መሪነት መስቀሉን ይዘው ወደ ቦታው ሲያመሩ መስቀለኛው የግሸን ተራራን አገኙ፤ በዚያም ቤተ ክርስቲያን አሠርተው የጌታችንን መስቀል በክብር አስቀምጠውታል፡፡
ከዚህ በኋላ ንጉሡ ‹‹መካከሏ ገነት፤ ዳሯ እሳት ይኹን! የበረረ ወፍ፣ የሠገረ ቆቅ አይታደንባት! በድንገት ሰው የገደለ፣ ቋንጃ የቈረጠ ወንጀለኛ አይያዝባት!›› ብለው ዐዋጅ ነግረዋል፡፡ የእመቤታችን ጽላትም አብሮ በግሸን ደብረ ከርቤ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ ስለዚህም መስከረም ፳፩ ቀን በየዓመቱ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡
የእግዚአብሔር ቸርነት፣
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
አማላጅነት፣ አይለየን፡፡አሜን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፡፡
ዋቤ መጻሕፍት፡-
✍️ መጽሐፈ ጤፉት
✍️ የቤተክርስቲያን መዝገበ ቃላት
✍️ የቤተክርስቲያን ታሪክ በኢትዮጵያ
✍️ የግሸን ደብረ ከርቤ ታሪክ