የባልሽኝ ልብ ለመያዝ
የትዳር ህይወትን በኢማን ያበበ ጣፋጭ ለማድረግ የትዳር ክህሎቶችን ማወቅ ያስፈልጋል። ወደ አዲስ የትዳር ህይወት እግሯን ያስገባች ወጣት ሴት የትዳር ክህሎቶችን በተለይም የትዳር አጋሯን ልብ መቆጣጠር የምትችልባቸውን ባህሪያት ጠንቅቃ ማወቅ አለባት። በርግጥ የትዳር ህይወት ክህሎቶችን ማወቅ አዲስ ትዳር ውስጥ የገቡ ወጣት ሴቶችን ብቻ ሳይሆን በትዳር ውስጥ ያሉትን ሁሉ ይመለከታል።
@ ጓደኛው ሁኚ
ባልሽ ሚስቱ ብቻ ሳይሆን ጓደኛውም እንድትሆኚ ይፈልጋል። ልቡን በእጅሽ ለማስገባት ከማንም በላይ የሚቀርበው ጓደኛ ሁኚለት ሁሉንም ጉዳዩቹን ተካፈይው። ችግሮቹን አድምጪው። ለርሱ ችግር መጨነቅሽንና በችግሩ ፊት አብረሺው እንደምትቆሚ አስረጂው ጓደኝነታችሁ የጠለቀ እንዲሆን በምድር ላይ የሚያስፈልግሽ ብቸኛው ሠው እርሱ እንደሆነ እንዲሠማው አድርጊው ጓደኛሞች የሚያደርጉት ሁሉ አብራችሁ አድርጉ።
@ እናቱን ሁኚለት፣
እንደ እናቱ ተንከባከቢ ሁኚለት፤ እንደ አባት አሳቢ ይሆንልሻል፤ ልቡን አሳልፎ ይሰጥሻል። ህፃን መሆን ሲያምረው እቀፊው። እናት ለልጇ የምትሠጠውን እንክብካቤ ስጪው። አርፍዶ ሲገባ መጨነቅሽን አሳይው። ዓለሙን ሁሉ ሁኚለት በሚወዳቸው ትናንሽ ነገሮች ላይ ሳይቀር ትኩረት አድርጊ። እንክብካቤሽና የምታሳይው አሳቢነት ልቡን ይቆጣጠረዋል። ከአንቺ መለየት ከእናቱ እንደመለየት ይከብደዋል።
@ ከግትርነት ራቂ
ወንድ ልጅ ግትራና ጨቅጫቃ ሴትን አይወድም። በንዝንዝ ህይወቱን ወደ እስር ቤት የምትለውጥበትን ሴትን አይወድም ግትርነት እና ጭቅጭቅ የትዳር ሠላምን ያናጋል። በምትነጋገሩበት ወቅት ስህተቱን ብትነግሪው ችግር የለውም። በፍጹም ግን ከብሩንና ወንድነቱን አትፈታተኞው። የምትፈልጊውን የሟሟላት ብቃት አንደሌለው እንዲሰመው አታድርጊ። ከዚህ በኋላ ልቡ ውስጥ ቦታ አይኖርሽም። የወንድ ልጅ ክብር የሚቆስለው በፍጥነት ነው። ከዚያ በኋላ ለማከም ያስቸግራል።
@ ንፁህ ልብ ይኑርሽ
ባል ንፁህ ልብ ያላት ሚስቱን እስከ እድሜው መጨረሻ ከመውደድ አይቆጠብም። ረሡል አላህ ሠላምና ሠላት በርሳቸው ላይ ይሁን) የመጀመሪያ የህይወት አጋራቸውን ኸዲጃ ቢንት ኹወይሊድን ምን ያህል ይወዷትና ከህልፈቷ በኋላም ምን ያህል ያስታውሷት እንደነበረ አስታውሺ ለኸዲጃ ካላቸው በጣም ብዙ የውዴታ ምክንያቶች አንዱ ኸዲጃ ንፁህ ልብ ያላት ምርጥ ሴት መሆኗ ነው።
በተንኮል ልቧን ለሞላች ሚስት ልቡን አሳልፎ የሚሠጥ ባል የለም። ሚስቱን መጀመሪያ ላይ የሚወድ ቢሆን እንኳ ተንኮለኛ ልብ ካላት በሂደት እየጠላትና ልቡን ከእርሷ እያራቀ ይሄዳል። ቀስበቀስም አንዲትም ደቂቃን ቢሆን ከእርሷ ጋር ለማሳለፍ ይጠላል። የባልሽን ልብ ለመቆጣጠር ንፁህ ልብ ይኑርሽ።
@ ቀልድ እወቂ
ባልሽ ፈገግ እንዲል ቀልድ ንገሪው በራስሽ ላይ ፣ በርሱ ላይ ለጨዋታ የሚሆን ቀልድ ፍጠሪ ቀኑን ብሩህ አድርጊለት፤ ልቡን አሳልፎ ይሠጥሻል። ጭንቀቱን ቀላል ስላደረግሽለት ያመስግንሻል፤ ከልቡ ይወድሻል። ባሎች ቀልድ የሚችሉ ሚስቶችን ይወዳሉ።
@ በዐይኖችሽ አናግሪው፤
ዐይን የልብ መስተዋት ነው። አንደበትሽ ሳይናገር በዐይኖችሽ ብቻ ምን ያህል እንደምትወጂው ንገሪው። ዐይኖችሽ ወደ ዐይኖቹ ፍቅርሽን ያደርሱልሻል። የዓይኖችሽ መልዕክቶች ከአንደበትሽ በበለጠ ወደ ባልሽ ልብ በፍጥነት የደርሳሉ። ልቡንም ይቆጣጠሩታል። ተፅዕኖአቸውም ከባድ ነው። ዓይኖችሽን መናገር ያስቻላቸው መናገር አላህ የተመሠገነ ይሁን።
✍ @eross_eross