ኢትዮጵያ በ39 ስፖርተኞች የምትሳተፍበት የ ፓሪስ_ኦሊምፒክ ዛሬ ይጀመራል
በፓሪስ የሚካሄደው 33ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የመክፈቻ ስነ ስርዓት ዛሬ ሐምሌ 19 ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ30 በይፋ ይጀመራል።
ከ100 ዓመታት በኋላ ለ3ኛ ጊዜ ታላቁን የስፖርት መድረክ የማስተናገድ ዕድል ያገኘችው ፓሪስ፤ የዘንድሮው ኦሊምፒክ መክፈቻ በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከስታዲየም ውጪ በወንዝ ላይ ታደርጋለች።
ይህ የመክፈቻ መርሃግብር በፓሪስ ሰሜናዊ ክፍል ዘወትር የመዝናኛ ጀልባዎች በሚንሸራሸሩበት ሴን ወንዝ ላይ የሚከናወን ሲሆን፤ ተሳታፊ ሃገራትም ባንዲራቸውን ይዘው የሚታዩት በተዘጋጁላቸው 94 ጀልባዎች ላይ ሆነው የ3 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ጉዞ ያደርጋሉ፡፡
በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ከ203 ሀገራት የተወጣጡ 10 ሺህ 500 አትሌቶች በ32 የስፖርት አይነቶች እንደሚወዳደሩ የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ በዋናነት በተለያዩ ርቀቶች በሚደረጉ የአትሌቲክስ የስፖርት ውድድሮች በ39 ስፖርተኞች የምትካፈል ሲሆን አትሌቶቹ ከሚያዚያ 2016 ዓ.ም አንስቶ ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርጉ ቆይተዋል።
ፈረንሳይ የኦሊምፒክ ተሳታፊ ሀገራትን ቀይ ምንጣፍ በመዘርጋት እየተቀበለቻቸው ሲሆን ለታላቁ ድግስ 9 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ያደረገች ሲሆን በአጠቃላይ እስከ 12 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ገቢ ታገኛለች ተብሎም ይጠበቃል፡፡የማሊና የፈረንሳይ ጥምር ዜግነት ያላት የ29 ዓመቷ ድምጻዊና የዜማ ደራሲ አያ ናካሙራ በመክፈቻው ስነ ስርዓት ስራዋን ታቀርባለች። አሜሪካዊቷ ሌዲ ጋጋና ካናዳዊቷ ኮከብ ሴሊን ዲዮን የሙዚቃ ስራቸውን ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።(ኢዜአ,ኢፕድ)
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ