የአንድ ስታዲየም ስፋት ያለው የጠፈር አለት ከሰማይ ወደ መሬት እየተምዘገዘገ ነው ተባለ፡፡
የአሜሪካ ጠፈር ሳይንስ ምርምር ማዕከል ወይም ናሳ እንደገለጸው ከሆነ አሜሪካ በዓለም ጦርነት ወቅት በጃፓኗ ሂሮሽማ ላይ ከጣለችው ቦምብ በመቶዎች እጥፍ ሀይል ያለው የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ወደ ምድር እየመጣ ነው ብሏል፡፡
አፍሪካ፣ ፓስፊክ፣ እስያ እና ደቡብ አሜሪካ ይህ ጠፈር አለት ያርፍበታል ተብሎ ከሚጠበቁ ቦታዎች መካከል ዋነኞቹ ናቸው፡፡ ኤኤፍፒ የጠፈር ሳይንስ ባለሙያው ብሩስ ቤትስን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የጠፈር አለቱ እንዲሰባበር እና ጉዳት ወደ ማያደርስ ቦታ ለማሳረፍ ጥረቶች በመደረግ ላይ ነው፡፡
ዓለም አቀፉ የጠፈር አለት ማስጠንቀቂያ ማዕከል በበኩሉ ወደ ምድር እየመጣ ያለውን የጠፈር አለት ወይም አስተሮይድ ጉዳት ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡ ናሳ እንደተነበየው ከሆነ ይህ የጠፈር ዓለት አሁን ባለበት ፍጥነት መሰረት ወደ ምድር በፈረንጆቹ 2032 ላይ ወደ መሬት ይደርሳል፡፡
አሁን ላይ ወደ ምድር እየመጣ ነው የተባለው ይህ ግዙፍ ዓለት የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ ካይነቲክ ኢመፓክተር የተሰኘ ቴክኖሎጂን በመጠቀም ጉዳት ወደማያደርስ መልኩ መቀየር እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይሁንና ይህንን ቴክኖሎጂ ለመተግበር ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን ብዙውን ጊዜ የበለጸጉ ሀገራት ወጪውን የሚሸፍኑት በአለቱ ሊጠቁ እንደሚችሉ ከተገነዘቡ ብቻ መሆኑ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል፡፡
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ