የትግራይ ክልል ጊዜዊ አስተዳደር 'የሰራዊት አመራር ውሳኔ ' በሚል ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ስልጣን ለማስረከብ የተጀመረ እንቅስቃሴ እንዲቆም " ሲል ትእዛዝ ሰጠ።
ትእዛዙን የሰጡት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ህገ-ወጥ ተግባሩ " አስነዋሪ ፣ ለውጥ አደናቃፊና እርባና ቢስ " ሲሉ አጣጥለውታል። ፕሬዜዳንቱ በቀጥታ ለጊዚያዊ አስተዳደሩ ምክትል ፕሬዜዳንትና የሰራዊት አዛዥ ሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የካቲት 26/2017 ዓ.ም በፃፉት ደብዳቤ ህገ-ወጥ ተግባሩ በአስቸኳይ እንዲቆም አዘዋል።
"ህገ-ወጥ ጉባኤ ያካሄደ ቡድን " ሲል የገለፁት የደብረፅዮኑ (ዶ/ር) ህወሓት የክልሉ ማእከላዊና ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን የጊዚያዊ አስተዳደር መዋቅሮች በሰራዊት በመታጠቅ መቆጣጠሩ አንስቷል። ህገ-ወጥ ድርጊቱ በተቀሩት ምስራቃዊ ፣ ደቡባዊ ፣ ደቡብ ምስራቅና መቐለ ዞኖች ለመፈፀም ያለመ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነውም ብለዋል። አቶ ጌታቸው ፤ " ማንኛውም ጥያቄ አለኝ የሚል የሰራዊት አመራር በህጋዊ መንገድ ጥያቄው ማቅረብ የሚችልበት ስርዓት በመጣስ በቀበሌ ፣ በወረዳ እና በመንደር ሰራዊት እያሰማሩ የመንግስት መዋቅር ለማፍረስ ማህተም ለመቀማት የሚደረግ እንቅስቃሴ ከስርዓት አልበኝነት ውጪ የሚያመጣው ፋይዳ የለም " ብለዋል።
" በተወሰኑ የሰራዊት አመራር ስም ሰራዊቱ በማሰመራት የመንግስት መዋቅሮች ህገ-ወጥ ጉባኤ ላካሄደ ቡድን ለማስረከብ የሚደረግ እንቅስቃሴ እጅግ አደገኛና የማያባራ ቀውስ የሚያዋልድ በመሆኑ በአስቸኳይ ቆሞ ህገ-ወጥ ተግባሩ እንዲፈፀም ያዘዙ የሰራዊት አመራሮች እንዲጠየቁ " ሲሉም ፕሬዜዳንቱ በደብዳቤያቸው በአፅንኦት አሳስበዋል።
T.me/ethio_mereja
ኢትዮ-መረጃ