ቀበሌዎች እና ገበሬ ማህበራት ኬላዎችን በማሰር ክፍያ እየጠየቁ ነዉ ተባለ፡፡
አሽከርካሪዎች በአጭር ኪሎሜትር ልዩነት በተደጋጋሚ ኬላዎች ላይ ክፍያ እየተጠየቁ መሆኑንም አስታዉቀዋል፡፡
ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የጣና ከባድ መኪና አሽከሪካሪዎች ማህበር ዋና ጸሃፊ አቶ ሰጡ ብርሃን፤በአማራ ክልል በ2014 ላይ ኬላዎች ተነስተዉ ነበር ያሉ ሲሆን፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ወደ ነበረዉ አሰራር በመመለሱ ቀበሌዎች እና ገበሬ ማህበራት ሳይቀሩ ኬላዎች በማድረግ ክፍያ በመጠየቅ ላይ ናቸዉ ብለዋል፡፡
በአጭር ኪሎሜትር ልዩነት በተደጋጋሚ ኬላዎች ላይ ክፍያ እንጠየቃለን ይህ ለትራንስፖርት አገልግሎቱ ከባድ ተጽዕኖን እየፈጠረ ነዉ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይሄ ጉዳይ አሽከርካሪዎች ላይ ከሚያሳድረዉ ጫና ባልተናነሰ በሸማች ማህበረሰቡ ላይ የራሱን ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑንም ነዉ አቶ ሰጡ የተናገሩት፡፡
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ፤ በኢትዮጵያ ኬላ ይነሳ ተብሎ በመንግሥት ደረጃ ቢወሰንም በተለያዩ ምክንያቶች ግን 2መቶ83 ሕገወጥ ኬላዎች በመላዉ አገሪቱ ይገኛሉ ማለታቸዉ ይታወሳል ።
እነዚህ ኬላዎች የምርት ነፃ ዝውውርን በመገደብ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዉ ላይም አሉታዊ ጫና ያላቸው መሆናቸዉ በተደጋጋሚ ተነስቷል፡፡
Via ኢትዬ ኤፍ ኤም
@sheger_press