መንግስት ጫና ያደርግብኛል‼️
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት አስፈጻሚዎች ጫና እንደሚደረግበት በፓርላማ ተነገረ
የመንግሥትን ጉዳይ እንጂ ሕዝብ የሚፈልገውን እየሠራ አይደለም ተብሏል
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በመንግሥት ሥራ አስፈጻሚ አካላት ጫና ስለሚደረግበት የመንግሥት አካላት የሚፈልጉትን እንጂ፣ ሕዝብ የሚፈልገው ጉዳይ ላይ አይሠራም የሚል የኦዲት ሪፖርት ትችት ቀረበበት፡፡
ትችቱ የቀረበው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናና ወቅታዊ ጉዳዮች አገልግሎት አሰጣጥና አፈጻጸም ውጤታማነት በተመለከተ፣ የፌዴራል ዋና ኦዲተር በተቋሙ የ2015/2016 ዓ.ም. አፈጻጸም ላይ ባደረገው የኦዲት ሪፖርት ላይ፣ መጋቢት 24 ቀን 2017 ዓ.ም. ከተቋቋሙ ኃላፊዎችና ከዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ሲደረግ ነው፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት አስተያየት፣ ‹‹መንግሥት የሚፈልገውን እንጂ ሕዝብ የሚፈልገው ሚዲያ ላይ አይውልም።
Via:- ሪፖርተር
@Sheger_Press