በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች ተገቢውን ሥነ-ምግባር የተከተሉና የህብረተሰቡን ችግሮ የሚፈቱ ሊሆኑ እንደሚገባ ተጠቆመ።
------------------------------------
(የካቲት 22/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር በጥናትና ምርምር ሥነ ምግባር ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለመንግስትና ለግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰጥቷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ተጠባባቂ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰራዊት ሀንዲሶ (ዶ/ር) በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ በርካታ ጥናትና ምርምሮች ቢሰሩም ህብረተሰቡ ላይ ያመጡት ለውጥ ግን የሚጠበቀውን ያክል አይደለም ብለዋል።
እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ እንዳልሂነም ገልጸዋል።
ጥራት ያለው ጥናት ለመስራትና ለሳይንስ ያለን እይታ እንዲጨምር የምንፈልግ ከሆነ በቅንጅት መስራት ያስፈልጋልም ብለዋል።
በዚህም የሚሰሩ ምርምሮች ተገቢውን ስነምግባር የተከተሉ፣ የህብረተሰቡን ችግር የሚፈቱና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሊሆኑ እንደሚገባም አሳስበዋል።
በከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) በበኩላቸው ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተለያዩ ሪፍርሞችን ቀርፆ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም በመንግስትም ሆነ በግል ተቋማት የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች ከመመረቂያነት ባለፈ ጥራት ያላቸው ችግር ፈቺ እንዲሆኑ ለማድረግና ወጥ የሆነ አሰራር ሥርዓትን ለመከተል እንዲቻል ይህ ስልጠና መዘጋጀቱን ገልፀዋል።
በስልጠናው ከመንግስትና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተወከሉ ምሁራን ተሳታፊ ሆነዋል።