#repost
🤔እረስቼዋለሁ‼
#አንድ ሴት ወደ አንድ መንፈሳዊ አባት ዘንድ ቀርባ "እግዚአብሔር ሁሌም ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትዮዋ ሁኔታ ግራ የተጋቡት እኚህ አባትም በሁኔታው ተበሳጭተው ጥለዋት ይሄዳሉ።
ከዚያን ቀን በኋላ እቺ ሴት እየደጋገመች በመምጣት "እግዚአብሔር ማታ ማታ እየመጣ ያናግረኛል" ትላቸዋለች። በሴትየዋ ጭቅጭቅ የተሰላቹት እኚህ አባትም እንደለመደችው አንድ ቀን መጥታ ስታናግራቸው እንዲህ አሏት ....
"እውነት አንቺን እለት እለት እየመጣ ፈጣሪ የሚያናግርሽ ከሆነ አምንሽ ዘንድ ሁለት የቤት ሥራ ልስጥሽ" አሏት ትኩር ብለው እየተመለከቷት!
ሴትዮዋም የሚሏትን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገባች! ፡
እኚህ አባትም ከዚች ሴት ጭቅጭቅ ይገላግለኛል ያሉትን ጥያቄ አቀረቡላት እንዲህ በማለት "እውነት አንቺን እግዚአብሔር የሚያናግርሽ ከሆነ እስቲ ዛሬ ማታ ሁለት ጥያቄ ጠይቂልኝ" አሏት።
ሴትየዋም በእርጋታ "ምን ልጠይቅልዎ አባቴ?" አለቻቸው።
አባትም ጥያቄያቸውን እንዲህ ሲሉ ቀጠሉ አንደኛው የቤት ስራሽ "አንዲት ሴት ከእኔ ዘንድ በተደጋጋሚ እየመጣች አንድ በጣም ህመም የሆነባትን ችግሯን እያነባች እየነገረቺኝ ትሄዳለች። እኔም ይሄ ችግሯ ይወገድላት ዘንድ እየጸለይሁላት ነው፡፡ እስቲ እውነት ፈጣሪ ካንቺ ጋር የሚያወራ ከሆነ ይህቺ ሴት ለኔ አንብታ የነገረቺኝ ችግሯ ምን እንደሆነ ጠይቂልኝ አሏት፡፡
ሁለተኛው የቤት ስራሽ "ለረጅም አመት ልተወው ያልቻልኩት የዛሬ ወር ገደማ ግን ንስሀ ገብቼ የተውኩት አንድ ከኃጢያት እሰራ ነበር። ያ በፊት እሰራው የነበረ አሁን ግን ንሰሀ ገብቼ የተውኩት ኃጢያት ምን እንደነበረ ጠይቀሽ ንገሪኝ። እነዚህ ሁለቱን ጥያቄዎች በትክክል ከነገርሺኝ እውነትም ላንቺ እግዚአብሔር እንደሚናገር አምናለሁ" አሏት።
ሴትዬይቱም ወደ ቤቷ ሄደች።
አባት ተመልሳ እንደማትመጣ ገምተው ነበር። ዳሩ ግን በንጋታው ያቺ ሴት መጥታ አባን አስጠራቻቸው።
አባም ሴቲዮይቱን ሲያዩ በጣም ተገርመው ወደ እርሷ በመሄድ በፌዝ መልክ "እህስ ልጄ! ... እግዚአብሔርን የሴትቷን ችግር ምን እንደ ሆነና እኔም እግዚአብሔርን ንስሀ ገብቼ ያቆምኩት ኃጢያት ምን እንደነበር ጠየቅሺው?" አሏት ሳቅ እያሉ፤
"አዎን አባ" አለቻቸው ሴትየዋ አንገቷን እንዳቀረቀረች ...
"እህሳ ምን አለሽ?" አሏት አባ በመጓጓት ...
"የሴቷ ችግርና ጭንቀት ልጅ መውለድ አለመቻሏ ሲሆን የእርስዎን ግን እረስቼዋለሁ አለኝ" አለቻቸው፡፡
እኚህ መንፈሳዊ አባት ባልገመቱት ሁኔታ እውነተኛውን የልጅቷን ጭንቀት ሲሰሙ እጅግ ደነገጡና ለእርሳቸው ኃጥያት የእግዚአብሔር ምላሽ ልባቸው ተነክቶ ስቅስቅ ብለው እያለቀሱ ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት!
እ.. ረ .. ስ .. ቼ .. ዋ .. ለ .. ሁ ..!!
ሰው እንጂ ፈጣሪ ያለፈ ስህተትህን አያስብም ወይም እንደ ፍርድ ቤት የሰራሃውን ነገር ፋይል አድርጎ መዝገብ ቤት አያስቀምጠውም.... በቃ ወደ እርሱ በንስሃ ስትቀርብ ጥፋትህን ሙሉ ለሙሉ ይረሳዋል። ይቅርታዉ ትላንትን አያስብም። የሰው ልጅ ግን ሙሉ ይቅርታ የለውም። ዛሬ ምን ፍሪዳ አርዶ ቢታረቅህ፣ ምን በልቅሶ ታጅበህ እየተንፈራፈርክ ይቅር በለኝ ብትለው "ይቅር ብዬሀለሁ" ይልህና የሆነ ቀን ስታስቀይመው ይቅር ያለውን በደልህን እየቆጠረ ሲወቅስህ ይውላል! በአንድ ወቅት ያደረግከኝን የረሳሁት እንዳይመስልህ ይልሃል።
ፈጣሪ ግን ይቅር ካለህ በቃ ረሳው! ፍቅር ነዋ!
ታዲያ ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪን በኛ መጠን መትረን ንስሀ በገባንበት ኃጢያት ዘወትር የምናለቅስ? ስንቶቻችን እንሆን ፈጣሪ እንደኛ ቂመኛ መስሎን በፍቅር ያጠበውን ኃጢያታችንን እያስታወስን ዘወትር በፀፀት አለንጋ ራሳችንን የምንገርፍ? ... ይቅርታ ከመለመን እኮ ይቅር ማለት ይከብዳል! ምሬሀለሁ ከማለት ማረኝ እያሉ እግር ስር መደፋት አቤት በቀለለ!
#LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት‼
❤መልካም ምሽት🙏
SHARE|

"ፈጣሪ ይቅርታን የሚጠይቅ አንደበት እና ይቅርታን የሚያደርግ ልብ ይስጠን!"
አሜን!🙏
#LIKE👍👍 እና
ለምትወዱት 10 ሰው ሼር አርጉት‼
❤መልካም ምሽት🙏
SHARE|