አዲስ አበባ ፖሊስ በዘራፊዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን ገለፀ።
ዘራፊዎቹንበቁጥጥር ስር ለማዋል በተደረገ ጥረት አንድ የፖሊስ አባል ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡
የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በዘረፋ ወንጀል ላይ የተሰማሩና በተለይ ትኩረታቸው ለህዝብ ጥቅም ተብለው በተገነቡ የመሰረተ ልማት አውታሮች ላይ የስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ ዘራፊዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ባደረገው እንቅሰቃሴ ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ/ም ሌሊት ወንጀል ፈፃሚዎቹ የመሰረተ ልማት አውታር በመስረቅ ላይ እንዳሉ ፖሊስ ደርሶ አንደኛውን ወንጀል ፈፃሚ በቁጥጥር ስር ሲያውለው ግብረ አበሩ ያመልጣል፡፡
ያመለጠውን ወንጀል ፈፃሚ ለመያዝ በተደረገ ጥረት ወረዳ 5 ልዩ ቦታው 72 ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት ዘራፊው በፖሊሶች ላይ ተኩስ በመክፈት በአንድ የፖሊስ ላይ ጉዳት ያደርሳል፡፡
ግለሰቡ በተደጋጋሚ እጁን እንዲሰጥ በፖሊስ ቢጠየቅም ፍቃደኛ ከመሆን ይልቅ በድጋሚ በዙሪያው በነበሩት የፖሊስ አባላት ላይ ተጨማሪ ጉዳት ለማድረስ መተኮሱን በመቀጠሉ እርምጃ እንደተወሰደበት የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ኢትዮ ቴሌኮም የሚጠቀምባቸው ኬብሎች እና የመቁረጫ ከተር ፣ አጉሊ መነፅር ፣ ልዩ ልዩ ሰነዶችና እርምጃ የተወሰደበት ዘራፊ ሲተኩስበት የነበረ ሽጉጥ በኤግዚቢትነት ይዞ ምርመራን መቀጠሉ አስታውቋል፡፡
ጉዳት የደረሰበት የፖሊስ አባል ለህክምና ወደ ሆስፒታል የተላከ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቆ የከተማውን ሠላምና ደህንነት ለማወክ በሚንቀሳቀሱና መሰል የዘረፋ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ ህጋዊና የማያዳግም እርምጃ የሚወስድ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡