ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን❤
👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Free ተለቋል።✅✅✅✅
ቤቲንግ ለጠመመባቹ ብቻ።

ከኛ ጋር የማይቻል ይቻላል
ድንቅ አዲስ ቻናል፣ ምን ትጠብቃላቹ፣ ተቀላቀሉ እና የድሉ ተካፋይ ሁኑ


ሪያል ማድረድ ከ ማን ሲቲ የሚያደርጉትን ተጠባቂ ጨዋታዎች በ ነፃ በስልኮዎ ለማየት ከታች ያለውን ሊንክ LIVE (JOIN) የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉ አሁኑኑ እንዳያመልጥዎ  ✅


Telegram መክፈል ጀምሯል እስካሁን አልሰማችሁም?

✅ JOIN ✅ የሚለውን ንኩ አና በቀላሉ ገንዘብ ይስሩ 🫶🫶


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች

🇪🇺በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 

02:45 |🇩🇪 ዶርትሙንድ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን 🇵🇹
[Agg: ❸-0]
05:00 |🇫🇷 ፒኤስጂ ከ ብረስት 🇫🇷
[Agg:❸-0]
05:00 |🇳🇱 ፒኤስቪ ከ ጁቬንቱስ 🇮🇹
[Agg:➊-➋]
05:00 |🇪🇸 ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ🇬🇧
[Agg:❸-➋]
🇬🇧 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ

04:30 |🇬🇧 አስቶን ቪላ ከ ሊቨርፑል 🇬🇧

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
🇪🇺ትላንት የተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

🇮🇹ኤሲ ሚላን 1-1 ፌይኖርድ 🇳🇱
[Agg : ➊-➋]

🇮🇹አታላንታ 1-3 ክለብ ብሩጅ 🇧🇪
[Agg : ➋-❺]

🇩🇪ባየር ሙኒክ 1-1 ሴልቲክ 🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿
     [Agg : ❸-➋]

🇵🇹ቤኔፊካ 3-3 ሞናኮ 🇫🇷
[Agg : ➍-❸]

የተቆጠሩ ጎሎችን ለመመልከት

@BH_bestgoal

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


🚨ጠ/ሚ አብይ ለህውሃት 50ኛ አመት ያስተላለፉት መልእክት


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ አኹንም የፖለቲካ ልዩነቶችን በኃይል የመፍታት ፍላጎት ጎልቶ እንደቀጠለ መኾኑን ዛሬ የሚከበረውን የሕወሓት 50ኛ ዓመት በዓል አስመልክተው በትግርኛ ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስና ኢኮኖሚያዊ ማገገምና ማኅበራዊ መረጋጋትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፍትሕ እንዲሠፍን መስራት እንደሚያስፈልግም ዐቢይ አሳስበዋል።

የየካቲት 11 ትሩፋት ማንኛውም ልዩነቶች በድርድር የሚፈቱበት መኾኑን እንደገና መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ዐቢይ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ልዩነቶችን ለመፍታት የተመረጡ የግጭት መንገዶች ከየካቲት 11 ዓላማዎች ያፈነገጡ መኾናቸውን አውስተዋል።

ዐቢይ አያይዘውም፣ ኾኖም ብዙ ዋጋ ከተከፈለ በኋላም ቢኾን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚበረታታ ርምጃ ነው ብለዋል።


የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት (SDSN) የአፍሪካ ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍቷል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የጥምረቱ ማዕከል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ያቀርባል ተብሏል።

የማዕከሉ መከፈት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር እና በትብብር ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ለመቅረፅ የራሱን አበርክቶ እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡


የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።

በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።


🚨" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።


ኮካ ኮላ ወደ ሩሲያ ገበያ ለመመለስ እንዳቀደ እና በቀድሞዎቹ ፋብሪካዎቹ ላይ ድጋሚ ማምረት እንደሚጀምር ተዘግቧል

ኩባንያው ቀድሞውንም ወደ ገበያ ለመግባት እና ከሩሲያ ብራንዶች ጋር ለመወዳደር ስልቶችን እየተወያየ ነበር ተብሏል።

Source RT


❗ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ቢልም ተቃራኒ ሪፖርት መውጣቱ ተገለጸ❗

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ባወጣው የእስታትስቲክስ ሪፖርት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህም በባለፈው አመት ጥር ወር ከነበረበት 29.4 በመቶ ወደ 15.5 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህም 13.9 በመቶ ማሽቆልቆሉን የሚያመለክት መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡

እንዲሁም የምግብ ግሽበት በ16.6 በመቶ እና በምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት በ10.2 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

ይሁን እንጂ ትሬዲን ኢኮኖሚክስ ተደረገ ባለው ጥናት ከብሄራዊ ባንክ ሪፖርት ጋር ተቃራኒ የሆነ ቁጥር መመዝገቡን ገልጿል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ አመታዊ የዋጋ ግሽፈት 17 በመቶ እንደሆነ ያስታወቀ ሲሆን የብሄራዊ ባንክ ካወጣው ቁጥር ጭማሪ የሚያሳይ ነው፡፡

ሁለቱም ሪፖርቶች የቁጥር ልዩነት ቢኖራቸውም የዋጋ ግሽበት እንደ አጠቃላይ ከነበረበት መቀነሱን አመላክተዋል፡፡


❗ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አማራ ክልል ውስጥ ሚሊሺያ እንዲፈጠር አድርገዋል❗

የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ልዩ መልዕክተኛና የቀድሞው ርዕሰ ብሄር ሙላቱ ተሾመ፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ሊጠቀሙበት ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ በማለት አልጀዚራ ድረገጽ ላይ በጽሁፍ ባወጡት አስተያየት ከሰዋል።

የሰሜኑ ጦርነት ሲቀሰቀስ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ክስተቱን "እንደ መልካም አጋጣሚ አይተውት ነበር" ያሉት ሙላቱ፣ የኤርትራ ወታደሮችም ወደ ትግራይ ዘልቀው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት "ተጽዕኗቸውን ለማስፋፋት ላላቸው ፍላጎት" እንቅፋት አድርገው እንዳዩትና ጦርነቱ እንዲቀጥል ፍላጎት እንደነበራቸውም ሙላቱ ጠቅሰዋል።

ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አማራ ክልል ውስጥ ሚሊሺያ እንዲፈጠር አድርገዋል በማለት የከሰሱት ሙላቱ፣ አኹን ደሞ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት የሚቃወሙ ሕወሓት ውስጥ ያሉ ቡድኖችን ለመጠቀም እየሞከሩ ይገኛሉ በማለት ሙላቱ ወቅሰዋል።


የስምምነቱ ተቃዋሚ የኾነው የሕወሓት ቡድንና ታጣቂዎቹ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ በማለትም ሙላቱ በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን ቡድን ከሰዋል።

ሙላቱ፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት እንዲፈርስ የሚፈልጉ እንደ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል በማለትም አስተያየታቸውን ቋጭተዋል።


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
🇪🇺ዛሬ የሚደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

02:45 |🇮🇹 ኤሲ ሚላን ከ ፌይኖርድ 🇳🇱
              (Agg : 0-1)

05:00 |🇮🇹 አታላንታ ከ ክለብ ብሩጅ 🇧🇪
              (Agg : 1-2)

05:00 |🇩🇪 ባየር ሙኒክ ከ ሴልቲክ 🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿
              (Agg : 2-1)

05:00 |🇵🇹 ቤኔፊካ ከ ሞናኮ 🇫🇷
              (Agg : 1-0)

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
ትላንት የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት !

🇪🇸በስፔን ላሊጋ

🇪🇸ባርሴሎና 1-0 ራዮ ቫልካኖ 🇪🇸

🇮🇹በጣሊያን ሴሪኤ

🇮🇹ጄኖዋ 2-0 ቬንዚያ🇮🇹

የተቆጠሩ ጎሎችን ለመመልከት

@BH_bestgoal

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


❗ኢትዮጵያ የወዳጅ ሀገራት የውጭ ባንኮችን ልትፈቅድ ነው።❗

ኢትዮጵያ ከወዳጅ ሀገራት የመጡ የውጭ ባንኮች በፋይናንሺያል ሴክተሩ ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ለማድረግ ማቀዷን ያስታወቀች ሲሆን ይህም በሀገሪቱ የባንክ ፖሊሲ ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያሳያል ተብሏል።

ነገር ግን ከሁለት ወራት በፊት የተሻሻለው በጉጉት የሚጠበቀው ረቂቅ ህግ እስካሁን በይፋ ሊተገበር አልቻለም።

አዲስ በፀደቀው የባንክ ሥራ አዋጅ መሠረት ዓለም አቀፍ ባንኮች በተለያዩ የአሠራር ዘዴዎች ወደ ኢትዮጵያ ገበያ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል።


❗ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት❗

ኢትዮ ቴሌኮምበ6 ወራት ዉስጥ ከ 260 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እንደተደረጉበት ገለፀ

መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ266,162 በላይ የሚሆኑ ሙከራ የተደረገባቸውን የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን አስታውቋል።

ኩባንያው በፍጥነት እየተሻሻለ ያለውን የሳይበር ስጋት ሁኔታን በብቃት መቋቋሙን የገለፀ ሲሆን ይህ አስቀድሞ የወሰደው አካሄድ የዳታ መመዝበር ፣ ከአገልግሎት መቋረጥ እና የገቢ ብክነት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ጉዳት ለመከላከል አስችሏል ብሏል።

ተቋሙ እንዳስታወቀዉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት አዳዲስ የቁጥጥር ዘዴዎችን በመተግበር ከ266,162 በላይ የሚሆኑ ሙከራ የተደረገባቸውን የሳይበር ጥቃቶች ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከሽፍ ማድረጉን ነዉ ያስታወቀዉ።


🚨TVTI_Exit_Exam

የመውጫ ፈተና የምትወስዱ የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሰልጣኞች በኦንላይን የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ያበቃል።

ተከታዩን ሊንክ በመጫን የምታገኙትን ቅፅ በመሙላት ምዝገባ ያድርጉ 👇
https://forms.office.com/r/3KgnK1esuc

ኦንላይን መመዝገብ የማትችሉ አመልካቾች በኢንስቲትዩቱ ዋናው ግቢ በመገኘት በየትምህርት ክፍላችሁ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል።

🔔 የምዝገባ ጊዜው ዛሬ የካቲት 10/2017 ዓ.ም ያበቃል።

የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ ለምትወስዱ ተፈታኞች ፈተናው በኢንስቲትዩቱ ዋና ግቢ እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

የመዝገባ ብር 500 በኢንስቲትዩቱ የንግድ ባንክ አካውንት በማስገባት ክፍያ በመፈፀም ደረሰኝ መያዝ ይጠበቅባችኋል።

✍ የምዝገባ ጥሪው በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የጋርመንት ቴክኖሎጂ ሰልጣኞችንም ይመለከታል።

የመውጫ ፈተናው ከመጋቢት 6-11/2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ እንደሚሰጥ ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።


የፕሪቶሪያውን ስምምነት በሚመለከት በአፍሪካ ሕብረት   ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሄደ

በትግራይ ክልል የነበረውን ግጭት ያስቆመው የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ሂደትን በተመለከተና ከስምምነቱ "ሌሎች ምን እንማር?" በሚል ርዕስ ዛሬ የካቲት 9ቀን 2017ዓ.ም
በአፍሪካ ህብረት ሪፓርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።

በዚህ ውይይት ላይም የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና የህወሓት ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል(ዶ/ር) የተገኙ ሲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌድዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ፣ የሰላም ሚኒስትሩ አቶ መሐመድ እድሪስ እና ሌሎች ተገኝተዋል።

የፕሪቶሪያውን ስምምነትና አፈፃፀም የተመለከተውን ሪፓርት ደግሞ ተሰናባቹ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር ሙሳ ፉኪ ማህማት፣ የቀድሞ የናይጀሪያ ፕሬዚዳንትና የአፍሪካ ህብረት አደራዳሪ ቡድን ሰብሳቢ ኡሊሲንጎን ኦባሳንጆ እና ከፍተኛ ኮሚሽነሮች አቅርበዋል።

ከአንድ ሰአት በላይ የዘለቀ ውይይት ከተካሄደ በኋላ አቶ ጌታቸው ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት


❗አብዱ ኪያር ስለአደጋው የተናገረው❗
ከባድ አደጋ ነበር።
ትንሽ የአጥንት መሰንጠቅ ከጉልበቴ በታች አጋጠመኝ። ዳኑ orthopedics ዶክተር ኤልያስ በአስገራሚ ብቃት አክሞኝ አሁን በጣም ጥሩ ነው ያለሁት። አልሓምዱሊላህ።


እንኳን ፈጣሪ አተረፈህ ABD

ተወዳጅ ድምፃዊ አብድ ኪያር ከድንገተኛ የሞት አደጋ ህይዎቱ ተርፏል።
ከ90ዎቹ የሙዚቃ ኮከቦች አንዱ የሆነው አብዱ ኪያር /ABD/ የሊፍት ገመድ(ካቦ) ተበጥሶ አደጋ ደርሶበታል ።
በዚህ ሰዓት ህክምና እየተደረገለት ይገኛል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.