በዩኤስኤድ 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ በዘጠኝ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግ የአደጋ ሥጋት አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
በአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ በጀት የተመደበለት በተለያዩ ክልሎች ተግባራዊ የሚደረግና የአደጋ ሥጋት አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
ለፕሮጀክቱ ትግበራ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ከአሜሪካ አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት ጋር ትላንት ጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ የውል ስምምነት ተፈራርሟል።
ፕሮጀክቱ በዘጠኝ ክልሎች ባሉ 120 ወረዳዎች ተግባራዊ ይደረጋል ሲሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማሪያም(ዶ/ር) ገልጸዋል። ይፋ የተደረገው የአደጋ ሥጋት አስተዳደር ስርዓት ፕሮጀክት ከ14 ሚሊዮን በላይ ወገኖችን ማዕከል ያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ፕሮጀክቱ ሀገራችን ወደ ስጋት አስተዳደር ለመሸጋገር የምታደርገውን ጥረት እንደሚያግዝም አመልክተዋል። የአደጋ ስጋት ችግሮችን ሀገር በቀል በሆነ መንገድ ቀድሞ መፍታት የሚያስችልና የአደጋ ስጋት ቅነሳ አመራር ስርዓታችንን የሚያጠናክር ነው ሲሉም ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱ አደጋ ከመከሰቱ በፊትና ከተከሰተ በኋላ እንዴት ማስተዳደር እንደሚገባ፣ ችግሮችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ያግዛል ብለዋል። በአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳይ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሄኖክ ከወንድበላይ በበኩላቸው፣ አምስት ዓመት ለሚቆየው ለዚህ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ከአምስት ቢሊዮን ብር በላይ ከድርጅቱ መመደቡን ገልጸዋል። እንደሀገር ወደ ስጋት አስተዳደር ስርዓት ለመሸጋጋር የሚደረገውን ጥረት የሚያፋጥን ታሪካዊ ፕሮጀክት መሆኑን መግለጻቸውን ከኢዜአ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።