ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እንዲያስቆሙ ፑቲንን አሳሰቡ ‼️
አዲሱ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን ያለውን ጦርነት እንዲያስቆሙ ፕሬዚዳንት ፑቲንን አሳስበዋል፡፡
ትራምፕ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ጦርነቱን ማስቆም ካልቻሉ በሀገሪቱ ላይ ከፍተኛ ቀረጥ እና ተጨማሪ ማዕቀብ እንደሚጥሉም አስጠንቅቀዋል።
ትራምፕ በምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻቸው ወቅት የሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነትን “በአንድ ቀን” ውስጥ አስቆመዋለሁ ማለታቸው ይታወሳል፡፡
ከዶናልድ ትራምፕ ንግግር ጋር ተያይዞ እስካሁን ከሩሲያ በኩል የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ከሰሞኑ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቅርቡ ከፑቲን ጋር እንደሚነጋገሩ በመግለጽ ፤ “ይህን አታካች ጦርነት ማስቆም ይገባል” ማለታቸው አይዘነጋም፡፡