❗ኢትዮ ቴሌኮም የሳይበር ጥቃት❗
ኢትዮ ቴሌኮምበ6 ወራት ዉስጥ ከ 260 ሺህ በላይ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች እንደተደረጉበት ገለፀ
መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ ከ266,162 በላይ የሚሆኑ ሙከራ የተደረገባቸውን የሳይበር ጥቃቶች ማክሸፉን አስታውቋል።
ኩባንያው በፍጥነት እየተሻሻለ ያለውን የሳይበር ስጋት ሁኔታን በብቃት መቋቋሙን የገለፀ ሲሆን ይህ አስቀድሞ የወሰደው አካሄድ የዳታ መመዝበር ፣ ከአገልግሎት መቋረጥ እና የገቢ ብክነት ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ጉዳት ለመከላከል አስችሏል ብሏል።
ተቋሙ እንዳስታወቀዉ የሳይበር ጥቃቶችን ለመመከት አዳዲስ የቁጥጥር ዘዴዎችን በመተግበር ከ266,162 በላይ የሚሆኑ ሙከራ የተደረገባቸውን የሳይበር ጥቃቶች ምንም ጉዳት ሳያስከትሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከሽፍ ማድረጉን ነዉ ያስታወቀዉ።