❗ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አማራ ክልል ውስጥ ሚሊሺያ እንዲፈጠር አድርገዋል❗
የጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ልዩ መልዕክተኛና የቀድሞው ርዕሰ ብሄር ሙላቱ ተሾመ፣ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ በሕወሓት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል ሊጠቀሙበት ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ በማለት አልጀዚራ ድረገጽ ላይ በጽሁፍ ባወጡት አስተያየት ከሰዋል።
የሰሜኑ ጦርነት ሲቀሰቀስ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ክስተቱን "እንደ መልካም አጋጣሚ አይተውት ነበር" ያሉት ሙላቱ፣ የኤርትራ ወታደሮችም ወደ ትግራይ ዘልቀው በመግባት ከፍተኛ ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት "ተጽዕኗቸውን ለማስፋፋት ላላቸው ፍላጎት" እንቅፋት አድርገው እንዳዩትና ጦርነቱ እንዲቀጥል ፍላጎት እንደነበራቸውም ሙላቱ ጠቅሰዋል።
ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አማራ ክልል ውስጥ ሚሊሺያ እንዲፈጠር አድርገዋል በማለት የከሰሱት ሙላቱ፣ አኹን ደሞ የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት የሚቃወሙ ሕወሓት ውስጥ ያሉ ቡድኖችን ለመጠቀም እየሞከሩ ይገኛሉ በማለት ሙላቱ ወቅሰዋል።
የስምምነቱ ተቃዋሚ የኾነው የሕወሓት ቡድንና ታጣቂዎቹ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማፍረስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ በማለትም ሙላቱ በደብረጺዮን ገብረሚካኤል የሚመራውን ቡድን ከሰዋል።
ሙላቱ፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት እንዲፈርስ የሚፈልጉ እንደ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት ማድረግ ያስፈልጋል በማለትም አስተያየታቸውን ቋጭተዋል።