🚨ጠ/ሚ አብይ ለህውሃት 50ኛ አመት ያስተላለፉት መልእክት
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ አኹንም የፖለቲካ ልዩነቶችን በኃይል የመፍታት ፍላጎት ጎልቶ እንደቀጠለ መኾኑን ዛሬ የሚከበረውን የሕወሓት 50ኛ ዓመት በዓል አስመልክተው በትግርኛ ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።
ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስና ኢኮኖሚያዊ ማገገምና ማኅበራዊ መረጋጋትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፍትሕ እንዲሠፍን መስራት እንደሚያስፈልግም ዐቢይ አሳስበዋል።
የየካቲት 11 ትሩፋት ማንኛውም ልዩነቶች በድርድር የሚፈቱበት መኾኑን እንደገና መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ዐቢይ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ልዩነቶችን ለመፍታት የተመረጡ የግጭት መንገዶች ከየካቲት 11 ዓላማዎች ያፈነገጡ መኾናቸውን አውስተዋል።
ዐቢይ አያይዘውም፣ ኾኖም ብዙ ዋጋ ከተከፈለ በኋላም ቢኾን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚበረታታ ርምጃ ነው ብለዋል።