በፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋሙ ላይ ለቀረበው የኦዲት ግኝት የግብረ - መልስ ማብራሪያ ተሰጠ
የፌዴራል ኢዲተር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባካሄደው የኦዲት ግኝት ላይ ለተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የግብረ-መልስ ሪፖርት አቅርቧል፡፡
በተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የኦዲት ሪፖርት ግኝቱ የውይይት መድረክ ላይ ቋሚ ኮሚቴው ምላሽ የሚሰጥባቸውን ጥያቄዎች አቅርቧል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ግኝት በዋናነት
ከ2013 - 2015 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ክትትልና ቁጥጥር ፣ የስራ ተቋራጮች ብቃት ምዘናና ክትትል እንዲሁም የሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ አፈፃፀምን የተመለከተ ነው፡፡
እነዚህን የተመለከቱ ሃያ የኦዲት ግኝቶችና ተያያዥ ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር ተደምጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ የኦዲት ግኝቶቹን ተከትሎ በተቋሙ በአጭር ጊዜ የተከናወኑ የእርምትና የማስተካከያ ስራዎችን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ከኦዲት ግኝቱ በኋላ ማስተካከያ የተካሄደባቸው፣ በድጋሚ ለጨረታ የወጡ፣ በስምምነት ኮንትራታቸው የተቋረጡ እና በፍርድ ቤት ሂደት ያላለቁትን ሪፖርት ዋና ዳይሬክተሩ አስደምጠዋል ፡፡
እንዲሁም ትግበራቸው የተቋረጡ የመንግስት ፕሮጀክቶች የቅድመ ክፍያን ተመላሽ በማድረግ ረገድ ተግባራዊ የተደረጉ እና በሂደት ላይ ያሉትንም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡
የዘርፉን የመረጃ ስርዓት በአስተማማኝ ሁኔታ በማደራጅት እንዲሁም ለተቋሙ የተሰጡትን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎች የሚስተካከሉበት አግባብ በመከናወን ላይ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡
በዋናነትም የኮንስትራክሽን ቁጥጥር አዋጅ እና መመሪያ ፣ ከመረጃ መረብ ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን በመልማት ላይ የሚገኘው የተቀናጀ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ መረጃ አስተዳደር ስርዓት ተጠናቀው ስራ ላይ ሲዉሉ የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በውጤታማነት ለመወጣት የሚያስችል እንደሆነም ኢ/ር መስፍን ነገዎ አስረድተዋል፡፡
ከግንባታ ፕሮጀክቶች ቁጥጥር ስርዓት አንፃር ከክልሎች ጋር መኖር ስለሚገባው ግንኙነት፣ የውጭ አገር ተቋራጮች ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ፣ ሕጎችና ደንቦችን ከማስከበር አንፃር መወሰድ የሚገባቸው ርምጃዎችን እንዲሁም በዘርፉ የሴቶች ተጠቃሚነት የተመለከቱ የኦዲት ግኝቶች ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሪፖርቱን ተከትሎ የፕሮጀክቶችን ጥራት ከማስጠበቅ፣ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን ፣ ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አንፃር ትኩረት በመስጠት በተቋሙ እየተከናወኑ ስላሉ የክትትል ስራዎች በቋሚ ኮሚቴ አባላት የማብራሪያ ጥያቄዎች ቀርበው ከተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ግብረ - መልስ ተሰጥቷል፡፡
የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ከኦዲት ግኝቱ ትምህርት በመቅሰም የግንባታ ፕሮጀክቶች ውጤታማ መሆናቸውን በማረጋገጥ ረገድ ተቋሙ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በቁርጠኝነት ማከናወን እንደሚገባው ትምህርት ሊወሰድ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።
የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት ማጠቃለያ በኦዲት ግኝቶቹ የተለዩና በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች መርሃግብር እንዲዘጋጅላቸውና በሂደት መፍትሄ ያገኙት ላይ ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት እንዲቀርብ አሳስበዋል፡፡
(ኢኮባ)