ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም/Ethio con radio perogram/


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Musiqa


በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Musiqa
Statistika
Postlar filtri


የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የኢትዮጵያ ታምርት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ ወደ ስራ ከገባ ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ከ625 በላይ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን ገለፁ።

የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የእቅድ አፈፃፀም የስትሪንግ ኮሚቴ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የአምራች ኢንዲስትሪዎች የማምረት አጠቃቀም 46 በመቶ የነበረ መሆኑን የጠቀሱት አቶ መላኩ ንቅናቄው ከተጀመረ አንስቶ እስከ አሁን ያለንበት ደረጃ በአማካይ የማምረት አጠቃቀም ወደ 61 በመቶ ደርሷል ብለዋል፡፡

ንቅናቄው ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ  ከላይ እስከታች ያለው የመንግስት የበላይ አመራሩን ትኩረት እንዲያገኝና በዘርፉ ችግሮች ዙሪያ ተከታታይነት ያለው ውይይት በማድረግ ለችግሮቹ የመፍትሔ ባለቤት በመሆን በጋራ መስራት በመቻሉ የማምረት አቅም አጠቃቀም፣ ገቢ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርቶች መተካት፣ በራስ ምርት የመኩራትና የመጠቀም ባህላችን እየተሻሻለ መምጣቱን ጠቅሰዋል።

በውይይት መርሃ ግብሩ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አፈፃፀም መቅረቡን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።




በግንብ የታጠሩ 22 አስደናቂ የአለማችን ታሪካዊ  ከተሞች።
**
…የቀጠለ
11. የ
ሀረር ጀጎል ግንብ / Harar
የሐረር ጀጎል ግንብ የተገነባው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን ከኢማም አህመድ አስተዳር በኋላ በአሚር ኑር አማካኝነት ነው።
ግንቡ የተገነባበት ዋና ምክንያት የሐረርን ከተማ ከወራሪዎች ለመከላከል ሲባል እንደሆነ ይነገራል፤ ሐረር በምራቅ አፍሪካ የንግድ ማዕከልም ነበረቸ።

ስለ ግንቡ አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች
🔷አጠቃላይ ርዝመቱ 3342 ሜትር፣
🔷  ከፍታው4.5 ሜትር፣
🔷 የግንቡ ውፍረት ከ40-50 ኢንች፣
🔷 ግንቡ ያረፈበት የቦታ ስፋት 48 ሄክታር፣
🔷 በግንቡ ውስጥ የሚገኙ መስጊዶች ብዛት ከ90 በላይሲሆኑ፣
🔷በግንቡ ውስጥ ከ2000 በላይ ጥንታዊና ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፣
🔷  የሐረረ ጀጎል በምስራቅ አፍሪካ በግንብ የተከበበች ብቸኛ ጥንታዊ ከተማ ናት።

10. ታሩዳንት/ Taroudant
ታሩዳን በሞሮኮ ምትገኝ አስደናቂ እና ውብ የበርበሮች በግንብ የታጠረች ከተማ ናት፤ ከተማይቱም የሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ቅድመ አያትም በመባል ትጠራለች፤ ታሩዳንት የተፀነሰችውም በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ነበር።

9. ቶሌዶ /  Toledo
ቶሌዶ የቀድሞው የእስፔን ስርወመንግስት ዋና መቀመጫ የነበረች ስትሆን፤ ታሪኳ ግን የሚጀምረው ከሮማውያን አገዛዝ ግዜ አንስቶ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል።

ቶሌዶ በእስፔን ሙስሊም ሱልጣኔቶች አገዛዝ ስር ወድቃ የነበረ ቢሆንም በ 1500 ዓመት ገደማ  ማድሪድ የእስፔን መናገሻ አስክትሆን ድረስ  ቶሌዶ መናገሻ ከተማ ነበረች፨

8. ፒንጊያው /Pingyao
የቻይናዋ ፒንጊያው  በአለማችን ከሚገኙ ታሪካዊ ከተሞች ጥንታዊ ይዘቷን ሳትለቅ የዘለቀች ከተማ እንደሆነች ተመስክሮላታል።
ስድስት መግቢያ ዋና በሮች እና 72 የጥበቃ ማማዎች ያሏት ይች ከተማ በሆነ ወቅት  አጥሯ ፈርሶ የነበረ ቢሆንም ዳግም ሊታደስ ችሏል።

7. ኦቢዶስ /Obidos
በከፍታ ቦታዎች የተገነባችው ይች ከተማ በ8ተኛው ክፍለዘመን በሞርሞር ሙስሊሞች  እንደታነፀች ይነገራል።

በ14 ተኛው ክፍለ ዘምን ግንቡ በፓርቹጋል ንጉስ አገዛዝ  ስር እንደወደቀ እና የግንቡ ይዘት ላይም ለውጥ እንደተደረገበት ይነገራል።

6. ዢያን / Xi’an
ዢያን በቻይና ከሚገኙ ከተሞች ጥንታዊት ከተማ ስትሆን፤ 3100 አመት ገደማ የስቆጥራለች።

በ 1000 አመት ታሪኳም 13 ስርወመንግስታት ሲፈራረቁባት 73 ንጉሶች ደግም ይህችን ከተማ እንደመሩባት ይነገራል።
የሲልክሮድ  ንግድ መስመር እንደነበረች እና የዝነኛው ትራኮቴ ሰራዊት መገኛም ነበረች።
ዢያን በ14ተኛው ክፈለዘመን በሚንግ ስርወመንግስት ስር ስትወድቅ እድሳት ተደርጎላታል።

5. ኢቻን ካላ/ Itchan Kala
የዩዝቤኪስታኗ በግንብ የታጠረችው ከተማ የተገነባችው በፀሀይ በደረቁ የጭቃ ጡቦች በመሆኑ ግንቡ ልዩ ያደርገዋል።

ኢቻን ካላ በርካታ ጊዜ የመደርመስ አደጋ የገጠማት  ቢሆንም ዳግም እየታነፀች ቆይታለች።

4. አቪላ / Avila
በአስራ አንደኛው ክፍለዘመን እንደተገነባች ሚነገርላት ይች የእስፔኗ ከተማ የታነፀችው ድንጋያማ በሆነ ኮረብታማ ስፍራ ነው።

3. ካርካሶኔ Carcassonne
ካርካሶኔ በፈረንሳይ የምትገኝ በደንብ ታሪካዊ ይዘታቸውን ከጠበቁ  በግንብ ከታጠሩ ከተሞች በቀዳሚነት ልትጠቀስ የምትችል ናት።

ይች ከተማ በአውሮፓ ከሚገኙ መሰል ከተሞችም በትልቅንቷ ተወዳዳሪ የላትም።
ካርካሶኔ ‘ሮቢን ሁድ’ የመሰሉ እና ሌሎች ፊልሞች ቀረፃ የተካሄደባት  ከተማም ናት።

2. እየሩሳሌም/ Jerusalem
እየሩሳሌም የሶስቱም የአብራሀም እምነቶች ቅድስት ከተማ ስትሆን፤ በአሁኑ ወቅት በፍልስጤም እና እስራኤል የቁርሾ መነሻ የሆነች ታሪካዊ ዝነኛ ከተማ መሆንዋ ይታወቃል።

እየሩሳሌም ወይም አል-ቁድስ የረዥም ታሪክ ባለቤት ስተሆን የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ታሪኳ በተለይ እየሩሳሌም በግንብ ለመታጠሯ  የኦቶማን ስርወመንግስት ሰፊውን ድርሻ ይወስዳል።

1. ዱብሮሜክ / Dubrovnik
በክሮሺያ ባህር ዳርቻ የምትገኘው ዱብሮሜክ የተጠበቀች ውብ በግንብ የታጠረች ከታማ ናት።

ይች ከተማ በሜድትራኒያን ባህር ጠረፍ የምትገኝ ስትሆን በጥንት ዘመን የባህር በር ንግድ ይቀላጠፍባት የነበረች የበለፀገች ከተማ ነበረች።

በ12-17ተኛው ክፍለዘመን አካባቢ እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ቢሆንም ታሪካዊ ይዘቷን  አሁን ድረስ የጠበቀች እንደሆነች ይነገራል።

(https:www.touropia. com)


በ1.6 ቢሊዮን ብር የተገነባው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ተመረቀ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድና መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል የሚረዳው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ በ1.6 ቢሊዮን ብር ወጪ የተገነባ መሆኑ ገልጸዋል።

በቀን 30 ሺህ ሜትሪክ ኪዩብ ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው እና 240 ሺህ ነዋሪዎችን የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።

በነዋሪው  የሚነሳው የውሃ አቅርቦት ለማሻሻልም የፍሳሽ ማስወገጃ ውሃን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እንደሚያግዝ ተገልጿል።

የፍሳሽ ማጣሪያ ግንባታ ስራው በቻይናው ኩባንያው CGCOC Group የተከናወነ ሲሆን  የግንባታ ቁጥጥር ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን  ማከናወኑ ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ ቆሻሻን በዘመናዊ መንገድ ለማስወገድና ለማገናኘት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ የተጠቆመ ሲሆን  ዛሬ ተመርቆ ወደ አገልግሎት የገባው የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያም  የስራው አካል ሆኖ ይቀርባል።ማጣሪያ ጣቢያው ከህብረተሰቡ የሚሰበሰበውን ፍሳሽ  ሦስት የማጣራት ሂደት የሚያልፍ ነው።

በመጀመሪያ ደረጃ  ቆሻሻን መቀበል፣ የፍሳሽ መጠን መለካት፣  ፕላስቲክ መሰል ቆሻሻን መለየት ያካትታል።

በሁለተኛ ደረጃም ከመጀመሪያ ምዕርፍ ያለፉ ቆሻሻን የማጣርት ሂደት የሚከናወንበት ሲሆን በሶስተኛው ምዕራፍ ደግሞ ካሎሪን በመጠቀም ውሃ ይጣራል። በስተመጨረሻ የተጣራው ፍሳሽ  ለተለያዩ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚለው ይሆናል።

በመርሃ ግብሩ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ  ተገኝተዋል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ሞገስ ባልቻ ፣ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር አባይና ሌሎች የከተማ አስተዳድሩ ከፈተኛ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።


2017 2nd QUARTER CONSTRUCTION WORKS (ONLY DIRECT COST).pdf
20.0Mb
🔵 የ2017 2ኛ ሩብ ዓመት የኮንስትራክሽን ስራዎች ቀጥተኛ ዋጋ ጥናት




ከመንግሥት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ባሻገር ተቋራጮች በራሳቸው ደካማ የሆነ የውል አስተዳደር (Contract Administration) ትግበራ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።

ሳሙኤል (ኢንጂነር)፣ ‹‹ለምሳሌ የዋጋ ማስተካከያ ይፈቀድልን በሚል ገንዘብ ሚኒስቴር ሲጠየቅ፣ ‹ማን ከለከላችሁ?› የሚል ጥያቄ ሲያነሳ፣ የከለከለን አማካሪው በልዩ ሁኔታ (Special Condition) በማስፈረም መሆኑን ሲገልጹ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደዚህ ያለ ውል ማን ፈርሙ አላችሁ? ብሎናል። የእኛንም ችግር ራሳችን መውሰድ መቻል አለብን። ግን ፍፁም የተከለከለ አይደለም። በፊት የ12 ወር ተባለ አሁን የ18 ወር ሆነ፣ ከዚያ ውጪ ግን ሙሉ ለሙሉ ይህ ፕሮጀክት ይህንን አያካትትም ብሎ መከልከልን ያመጣው በደካማ ውል አስተዳደር ትግበራችን ችግር ነው፤›› ብለዋል። 

ከዚህ ባሻገር የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገሮች ለማስመጣት፣ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን ያህል ገንዘብ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ግዥ ለመፈጸም የሚዋዋሉት አገር ውስጥ ካለ አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆኑ፣ ዕቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት ጊዜ ፍጥነት አስተማማኝ አለመሆኑን ጥናቶቹን ያቀረቡት ባለሙያዎች አስረድተዋል።

(ሪፖርተር )


መንግሥት በራሱና በውጭ ተቋራጮች ግንባታዎችን በመቆጣጠሩ የግል ሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ

መንግሥት የመንገድና የሕንፃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የራሱን የግንባታና የዲዛይን ድርጅቶች በማቋቋም፣ ፕሮጀክቶችን መያዙና የተቀረውን ለውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች እየተሰጠ መሆኑ፣ የአገር ውስጥ የግል የሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።

ይህ የተገለጸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከግሉ የግንባታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ ነው።

ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች በአሥር ዓመታት ውስጥ በአገር ውስጥ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ወደ 75 በመቶ፣ በቀጣናው ደግሞ የ25 በመቶ ድርሻ እንዲያሳድጉ ዕቅድ ቢይዝም፣ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸው መንግሥት በውጭ ተቋራጮች ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኝነት፣ የክፍያዎች መዘግየት፣ በቅርብ የተካሄደው የኢኮኖሚክ ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ጫናና ሌሎችም ማነቆዎችን በማንሳት፣ መንግሥት በእርግጥ ኢንዱስትሪውን ያውቀዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።

አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የተባሉ ተሳታፊ፣ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት ወደ መቆጣጠር እያመራ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።

‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያው ከመሰላቸትምም ተነስቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን በመንግሥት በኩል ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት የመያዝ ሒደት ነው እያየን ያለነው። መንግሥት የራሱን የዲዛይን፣ የኮንስትራክሽን ተቋማት እያደራጀና እያዘጋጀ ነው። ስለዚህ ፕሮጀክት ሲመጣ ራሱ ዲዛይን ያደርጋል፣ ራሱ ግንባታ ይፈጽማል፣ በጣም ከእሱ አቅም በላይ የሆነውን ለውጭ ኩባንያዎች ይሰጣል። ስለዚህ ለግሉ ዘርፍ ቦታው ባዶ ነው ብዬ ነው የምገምተው፤›› ብለዋል።

በሌላ በኩል በምክክር መድረኩ የቀረቡ ሁለት ጥናቶች፣ በአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የሚገነቡ መንገዶች በ143 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ110 በመቶ ከተያዘላቸው ጊዜ አሳልፈው እንደሚጠናቀቁ፣ ከተያዘላቸው በጀትም እንዲሁ የመንገድ ፕሮጀክቶች በ18 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ35 በመቶ እንደሚያሳልፉ አመላክተዋል።

ከሚኒስቴሩ በኩል ጥናት ያቀረቡት ባለሙያ፣ ‹‹ከዚህ ጥናት በኋላ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተደረጉ የፕሮጀክቶች ክትትል በብዙ ፕሮጀክቶች እያንዳንዱ እየተነጠለ ሲታይ የጭማሪዎቹ መጠን ከዚህም በላይ እንደሆነ ማየት ተችሏል፤›› ብለዋል።

ሳሙኤል ሳህለ ማርያም (ኢንጂነር) የተባሉ ጥናት አቅራቢ በበኩላቸው፣ የውጭ ኮንትራክተሮች የሚይዙት ግንባታ መጠን አነስተኛ ሆኖ፣ ነገር ግን የሚይዙት የገበያ ድርሻ እስከ 62 በመቶ እንደሚደርስ አሳውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ያሉ ሥጋቶች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ‹‹የግንባታ ዘርፉ አሁንም ትልልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ትልቁን ድርሻ የያዙት የውጭ ሥራ ተቋራጮች ናቸው። ይህንን ልንቀይርበት የምንችልበት አካሄድ እስካልተፈጠረ ድረስ አሁን በቅርብ ይህ ንግድ ለዓለም የንግድ ድርጅት ክፍት ነው የሚሆ ነው።

ስለዚህ እኛ ምን ይዘን ነው የምንቀላቀለው? ምን ይዘን ነው ለውድድር ልንቀርብ የምንችለው? በዚህ ሁኔታ ከሆነ የምንቆየው ሁላችንም ተበልተን ነው የምናልቀው፤›› ብለዋል።

በሚኒስቴሩ በኩል የቀረቡት ባለሙያ የውጭ ተቋራጮች ጉዳይ እስከ ሉዓላዊነት የደረሰ ችግር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪ ኩባንያዎች 35 ሺሕ መድረሳቸውን፣ የባለሙያዎች ብዛትም 151 ሺሕ መሆኑን ጠቅሰዋል።

‹‹በቁጥር ይግዘፍ እንጂ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች በብዛት የተያዙት በሚያሳዝን ሁኔታ በውጭ ኮንትራክተሮች ነው። መጀመሪያ የአገራችንን 75 በመቶ ይዘን የቀጣናውን 25 በመቶ ገበያ ለመያዝ ነው ዕቅዳችን። እነዚህ ቁጥሮች ሳይሆኑ እኛን የሚታደጉን ሄዶ ሄዶ ጉዳዩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ጋር ይመጣል፤›› ብለዋል።
ሳሙኤል (ኢንጂነር) የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች ከዚህም ባሻገር ከበጀት ጋር የተያያዙ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

‹‹አንድ በውጭ ተቋራጭ የሚሠራ በጀቱ 800 ሚሊዮን ብር የነበረ ፕሮጀክት፣ ግንባታውን በመሀል አቁመው 3.2 ቢሊዮን ብር ካልከፈላችሁን አንሠራም ማለታቸውን እናውቃለን። ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚሠራው ስታዲየምን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጀመር በጀቱ ከሁለት ቢለዮን ብር ጥቂት ነበር ከፍ የሚለው። ግን በኋላ ላይ እስከ 12 ቢሊዮን ብር አይበቃም ማለታቸውን ሰምተናል፤›› ብለዋል።

ባለሙያው ይህ ዓይነቱ አሠራር ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች እንደማይሠራ ገልጸው፣ ኩባንያዎች፣ ከባንኮች ከግንባታ ዕቃ አቅራቢዎች ጋር ተያይዞ ሊሠራበት የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።

የውጭና የአገር ውስጥ ተቋራጮች አፈጻጸምን በተመለከተ ለአብነት የቻይና ተቋራጮችን አፈጻጸም ያነሲ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶችን በሚያገኙበት ወቅት ዕቃ አቅራቢ ፋብሪካ አዘጋጅተው፣ አማካሪ ኩባንያው የራሳቸው አገሮች ኩባንያ መሆኑንና ንዑስ ተቋራጮችም በራሳቸው እንደሚያዘጋጁ ጠቅሰው፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ እዚህ ለሚሠሩ ሥራ ተቋራጮች የገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) ችግር እንዳያጋጥማቸው እንደሚያቀርብላቸውና በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያልፍ የውጭ ተቋራጭ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን አከናወነ እንደሚባል ተናግረዋል።

‹‹የእኛ ሥራ ተቋራጭ እኮ በክፍያ ምክንያት የሚያጋጥመው ጫና ምናልባት መንግሥትና ዘርፉ የእውነት ይተዋወቃሉ?› የሚል ጥያቄ እንዳነሳ ነው የሚያደርገኝ። የእውነት ይተዋወቃሉ ወይ? ዘርፉ እኮ እየሞተ ነው ያለው። ክፍያ በአግባቡ ካልተከፈለው የፕሮጀክት ቆይታ በከፍተኛ ሁኔታ ነው እየጨመረ የሚመጣው። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት የሚያስችል የፋይናንስ ሲስተም ያስፈልጋል፤›› ብለዋል።

የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ የትምጌታ አሥራት በበኩላቸው፣ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በውይይት መድረኩ ከተነሱ ዋነኛ ጉዳዩች የውጭ ምንዛሪ ላይ የተደረገው ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ሌላ ጫና ይገኝበታል።

‹‹የኢንዱስትሪው ገበያ የሚንቀሳቀሰው በጥቁር ገበያው ነበር፡፡ እዚህ ላይ ምንም ልንወሻሽ የሚገባ ነገር የለም። ለምን አንድ አቅራቢ ዕቃ ከውጭ አምጥቶ ለመሸጥ ለሒደት ማስፈጸሚያ (Procedure Issue) ብቻ የባንክን ምጣኔ ይጠቀማል። ለምሳሌ 60 ብር በነበረበት ሰዓት ለፕሮሲጀር የባንክን ይጠቀማል፡፡ ሌላውን ግን በጥቁር ገበያ ሴኪውር ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ግን ዋጋ ሲያወጣ በጥቁር ገበያው ምጣኔ ነው የሚያወጣው፡፡ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክት ዋጋ ከፍ ይላል፤›› ብለዋል።

በተጨማሪም፣ ‹‹ምንዛሪ በገበያው መወሰን ሲጀምር በፊት ግብር የሚከፍል የነበረው ባንክ በሰጠው ምጣኔ ነበር። ለምሳሌ ምንዛሪው ሰባት ብር ከነበረ፣ አሁን ግን 125 ሲሆን ግብሩም በዚያው መጠን ከፍ ይላል ምክንያቱም በደረሰኝ ገንዘቡን ዝቅ አያደርግም። እንደነዚህ ዓይነት ዕርምጃዎችን እንዳይሄድና ኃላፊነት እንዲወስድ ብሔራዊ ባንክ አስገዳጅ መመርያ አውጥቶበታል። ያንን ስናይ ደግሞ ከኢንሹራንስና ከትራንስፖርት ጋርና ከሌሎች ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ የወጪ ክፍያዎች አሉበት። ስለዚህ በኢኮኖሚክ ሪፎርሙ የኮንስትራክሽን ዘርፉ አሁንም እንደገና ደግሞ ሌላ ተጋላጭነት አጋጥሞታል፤›› ሲሉ አብራርተዋል።


የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል ሊያስገነባ ነው

የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል ለማስገንባት ከህንጻ ተቋራጮች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ እና የህንጻ ተቋራጮች በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዳዊት መሀሪ፥ ማዕከሉ በኦሮሚያ ክልል በረክ ወረዳ በሰንዳፋ ከተማ አቅራቢያ በ14 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገነባ ተናግረዋል፡፡

የማዕከሉ ግንባታ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚገነባ ሲሆን ሁለት ሀገር በቀል የግንባታ ተጫራቾች ግልጽ ዓለም አቀፍ የጨረታ ሂደትን በማሸነፍ ውል መፈራረማቸውን ገልጸዋል።

ሁለቱም የማዕከሉ ግንባታ ምዕራፎች ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሶስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቁም ጠቁመዋል።

የማዕከሉ መገንባት ኢንስቲትዩቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉን በጥናት፣ በስልጠና፣ በጥራት አስተዳደር፣ በቴክኖሎጂና የክህሎት ሽግግር ለመደገፍ ያለውን ሚና ያጠናክራል ነው ያሉት።

ማዕከሉ የምርጥ ተሞክሮዎች መቀመሪያ፣ የዘመናዊ ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥራት ማረጋገጫ እንዲሁም ለሜጋ ፕሮጀክቶች እና በዘርፉ ለሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በበኩላቸው፥ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለሀገር ዕድገት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።

ዘርፉን በማዘመንና በማጠናከር ረገድ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል መገንባት ትልቅ አብርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በመሆኑም ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ለመገንባት ውል የወሰዱ ተቋራጮች በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።

ኢንስቲትዩቱም ለግንባታው መፋጠን ተገቢውን ክትትል ከማድረግ ባለፈ በአደረጃጀትና በግብዓት በበቂ ሁኔታ መዘጋጀትና ማሟላት እንዳለበት ጠቁመዋል።


አዲሱ የኢትዮጵያን ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ስራ አመራር ቦርድ አባላት


**ማስታወቂያ*

✅ ላለፉት ተካታታይ ሳምንታት የኢትዮ ኮን ሬድዮ ፕሮግራም እንግዳችን የነበሩት አቶ ዮፍታሔ ዩሀንስ በአይቲ እና በቴሌኮም ፕሮግራም ላይ በመስራት 17 ዓመት ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ናቸው፡፡ በንግዱ ዘርፍ በአይቲ በተለያዩ መሰል መስክ በአመራር ላይ ጥልቅ የሆነ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡

✅ በመካከለኛ ምስራቅ በአህጉራችን አፍሪካ ከ75 በላይ የተለያዩ አገራት ዜጎች ጋር በመስራት ጥቅል የሙያ ክህሎት ያካበቱ ባለሙያ ነው፡፡

✅ ባለሙያ ስለ ዲጂታል ቴክኖሎጂ በተመለከተ ያላቸውን ልምድ እንዲያካችሏችሁ አናንተ አድማጭ ቤተሰቦች ባቀረባችሁት ጥያቄ መሰረት አቶ ዩፍታሄ የአንድ ቀን ወይም የግማሽ ቀን ስልጠና በነፃ ለመስጠት ፍቃደኛ ሆኗል፡፡

✅ እናንተም በዚህ ስልጠና ላይ ተካፋይ ለመሆን ፍላጎት ያላችሁ በዚሁ ቻናላችን ላይ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ስማችሁንና ስልክ ቁጥራችሁን ልታስቀምጡልን ትችላላችሁ፡፡

⭕️ ማሳሰቢያ፡- ስልጠናው የሚሰጥበትን ቦታ እና ሰዓት ወደፊት የምናሳውቃችሁ ይሆናል፡፡

ኢትዮ ኮን ሬድዮ ዝግጅት ክፍል


👉 ኢትዮ ኮን የዛሬ ምሽት ታህሳሰ 21 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን

🚧 👷♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

🛑 በዛሬ ፕሮግራማችን

⭕️ ወቅታዊ ፕሮግራም
የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ምርምር ማዕከል ታህሳስ 16 ቀን 2017 ዓ.ም በኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ዙሪያ ሰፊ የምክክር መድረክ አካሂዷል። ይህንን ጉዳይ እንመለከተዋለን፡፡

⭕️ የእንግዳ ሰዓት

🔻አቶ ዮፍታሔ ዮሀንስ ዛሬም እንግዳችን ናቸው፡፡
በአይቲ እና በቴሌኮም ፕሮግራም ላይ በመስራት 17 ዓመት ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ናቸው፡፡ አቶ ዮፍታሔ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንሰተናል።  ሰዓቱን ጠብቃችሁ ተከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ እጋብዛለሁ።

❇️ በርካታ የሆኑ ልምዶችና ዕውቀቶችን የምታገኙበት በመሆኑ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ በድጋሚ በአክብሮት እጋብዛችኋለሁ፡፡

⭕️ ልዩ ዝግጅት

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ አካል ነው። ኮርፖሬሽኑን በእጅጉ እናመሰግናለን።

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


❇️ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

👉 ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና በሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

👉 ስምምነቱን የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተፈራርመውታል፡፡

👉 የሆልዲንጉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግዙፍ የኮንስትራክሽን ተቋም እንደመሆኑ የትብብር ስምምነቱ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ለኮርፖሬሽኑ የግንባታ ግብዓትን በተለይም የናሽናል እና የለሚ ሲሚንቶ ምርቶችን በበቂ ሆኔታ የሚያቀርብለት ይሆናል ብለዋል፡፡

👉 ኢ.ኮ.ሥ.ኮ በምህንድስና ዘርፍ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በኮንስትራክሽን ማኑፋክቸሪንግ ጠቃሚ ልምድ ያለው ተቋም ነው ያሉት አቶ ብሩ ፤ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከትብብሩ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

👉 ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊትም ሆልዲንጉ የሚያመርተውን ናሽናል ሲሚንቶ ይጠቀም እንደነበር ገልጸው  በቅርቡ  በሃገሪቱ  ግዙፍ የሆነውን የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ  የኮንክሪት መንገዶችን  በሲሚንቶ ለመስራት የሚያጋጥምን የሲሚንቶ ችግር በእጅጉ እንደሚያቃልለው ጠቁመዋል፡፡


🔵 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ
የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ  ቃሊቲ በሚገኘው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የመንገድ ምርምር ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል።

🔷 የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር አዘጋጅነት በመካሄድ ላይ ያለው ይህ መድረክ የኮንስትራክሽን እመርታ ለሀገር ግንባታ በሚል መሪ ቃል ነው እየተከናወነ የሚገኘው።

🔷 በዚሁ መድረክ ላይ  የመንግስት የስራ  ኃላፊዎች፣ ሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች ዘርፋ ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና  ሌሎች የተገኙበት መድረክ ነው።


ሀገር በቀሉ ብሪጅ ኮንስትራከሸን እያካሄደ ያለው የአቃቂ ድልድይ ግንባታ 40 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደርሷል

በአቃቂ ክፍለ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኘው የአቃቂ ወንዝ መሻገሪያ ድልድይ የግንባታ ስራ 40 በመቶ አፈፃፀም ላይ ይገኛል፡፡

የድልድዩን ግንባታ ብሪጅ ኮንስትራክሽን የተባለ ሀገር በቀል የስራ ተቋራጭ ከ447 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እያከናወነው ሲሆን፣ የማማከርና የቁጥጥሩን ስራ ደግሞ ስታዲያ አማካሪ ድርጅት እየተከታተለው ይገኛል፡፡

የግንባታ ስራው በዲዛይን ለውጥ እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በተያዘለት የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይጠናቀቅ ቆያቷል፡፡

በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የተቋሙ አመራርና የሥራ መሪዎች ቡድን በግንባታ ሥፍራው በመገኘት የመስክ ምልከታ ያደረገ ሲሆን፣ የድልድዩ ግንባታ በፍጥነት በሚጠናቀቅበት ሁኔታም ላይ አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

አሁን ላይ ከድልድዩ ግንባታ 2 ዋና ዋና ተሸካሚዎች እና 12 ምሰስዎች መካከል 50 በመቶ የሚሆነው ስራ በመገባደድ ላይ ሲሆን፣ ከዚሁ ጎን ለጎን የድልድዩን የላይኛውን ክፍል ፕሪካስት የማምረት ስራ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የአቃቂ ድልድይ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ፤ ከቃሊቲ ቶታል በዜሮ ስምንት ወደ በአቃቂ ከተማ  እና ወደ ቱሉ ዲምቱ አደባባይ የሚደረገውን የትራፊክ ፍሰት የተቀላጠፈ በማድረግ ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እንቅስቃሴ መሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ይታመናል፡፡

(አአመባ)


👉 ኢትዮ ኮን የዛሬ ምሽት ታህሳሰ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራሞቻችን

🚧 👷‍♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

🛑 በዛሬ ፕሮግራማችን

⭕️ የእንግዳ ሰዓት

🔻አቶ ዮፍታሔ ዮሀንስ ዛሬም እንግዳችን ናቸው፡፡

በአይቲ እና በቴሌኮም ፕሮግራም ላይ በመስራት 17 ዓመት ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ናቸው፡፡ አቶ ዮፍታሔ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን አንሰተናል።  ሰዓቱን ጠብቃችሁ ተከታተሉ ዘንድ ከወዲሁ እጋብዛለሁ።

❇️ በርካታ የሆኑ ልምዶችና ዕውቀቶችን የምታገኙበት በመሆኑ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ በድጋሚ በአክብሮት እጋብዛችኋለሁ፡፡

🏗 የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን የሚያቀርበው ልዩ ዝግጅት የፕሮግራማችን አንድ አካል ነው። ኮርፖሬሽኑን በእጅጉ እናመሰግናለን።                           

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


🚧 9ኛው ዙር የ Health and Safety in Construction እንዲሁም Ethics in Construction ስልጠና ተጠናቀቀ

🔷 በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሸን ሥራ ተቋራጮች ማህበር የቦርድ ሊቀመንበር ኢ/ር ግርማ ኃ/ማርያም እንዲሁም የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስትቲዩት የስልጠና እና ብቃት ማረጋገጫ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ቅድሰት ማሞ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን ከሰልጣኞች ጋርም ምክክር አድርገዋል፡፡

🔷 ማኅበሩ ሥራ ተቋራጮች ያሉባቸውን ችግሮች ለመፍታት ጥያቄውን ለሚመለከታቸው የመንግሰት መስሪያ ቤቶች እያቀረበ አበረታች ውጤቶችን እያገኘ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡

🔷 ኢንስቲትዩቱም እንደ ኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር እና መሰል ማኅበራት ለሚጠየቁ ስልጠናዎች በሩን ክፍት በማድረግ
ከ Health and Safety in Construction በተጨማሪ በPMP፣ BIM እና OPM ስልጠናዎችን ለባለሙያዎች እየሰጠ ይገኛል፡፡  

🔷 ማኅበሩም ለ10ኛዙር በ Health and Safety in Construction ስልጠና ሌሎች የማኅበሩ አባላት እንዲመዘገቡ በማሳሰብ በቅርቡ ስራ ተቋራጩን አቅም የሚገነቡ ስልጠናዎችን ለመጀመር በዝግጅት ላይ እንደሚገኝም ለማወቅ ተችሏል፡፡


❇️ What is Asphalt Road Construction?

👉 Asphalt road construction: involves the use of asphalt, a mixture of aggregates, binder, and filler, to build and maintain roads, highways, and other pavement surfaces.

👉 The components of asphalt include aggregates, binder, and filler. Aggregates are the inert materials that provide strength and bulk to the asphalt mixture. Common aggregates used include crushed rock, sand, gravel, or slags. The binder is the adhesive substance that holds the aggregates together, with bitumen being the most common binder used. Fillers are fine materials that fill the gaps between the aggregates and binder, such as limestone dust, cement, or hydrated lime.

👉 The asphalt mixture is created by combining the aggregates, binder, and filler in specific proportions. The mixture is then heated to a high temperature (around 300°F) to facilitate mixing and application.

👉 The asphalt road construction process typically involves several steps. First, the site is prepared by clearing the area, removing debris, and grading the surface. Next, a layer of compacted aggregate material is laid down to provide a stable base. The heated asphalt mixture is then applied to the base course using a paver or spreader.

👉 After the asphalt mixture is applied, it is compacted using rollers or compactors to achieve the desired density and smoothness. Finally, the surface is finished with a layer of asphalt emulsion or sealcoat to protect it from the elements.

👉 Asphalt road construction is used for a wide range of applications, including highways and roads, parking areas, railway tracks, ports and airport runways, bicycle lanes and sidewalks, and playgrounds and sports areas. Asphalt is a popular choice for road construction due to its durability, flexibility, and resistance to heavy traffic and harsh weather conditions.

( Civil Wisdom)


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ተመስገን ጥሩነህ ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን የኢንዱስትሪ መንደር ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ካነገበው ራእይ እና ተልእኮ አንጻር  በአፍሪካ ምርጥ ሦስት የኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያስችሉትን ተግባራት እያከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን  የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮርፖሬሽኑ  በቅርቡ የኮንስትራክሽን  ግብአት ምርቶችን በስፋት እና በጥራት በማምረት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ  ገበያ  እንደሚያቀርብ  ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

በጉብኝታቸው  በኮርፖሬሽኑ እየተከናወኑ   ያሉ የሪፎርም  ተግባራት     እና ያስገኙት ውጤት  እውነትም  የኢትዮጵያ  የማንሰራራት  ጊዜ መጀመርን  የሚያሳይ  መሆኑን የጠቆሙት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሥራ አካባቢን ጽዱ እና ምቹ ከማድረግ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም  ከማስተዳደር፣ የሰው ሀይልን ምርታማነት ከማሻሻል፣  የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ከማላቅ እና ትርፋማነትን  ከማሳዳግ አንጻር የተከናወኑ  ተግባራት ሌሎች ተቋማት ሊማሩበት የሚገባ ነው ብለዋል።

የኢ.ኮ.ሥ.ኮ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ   ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የኮርፖሬሽኑን 'ከየት ወዴት' ለጎብኚዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ የኮርፖሬሽኑን የልህቀት ትልሞች በመተግበር  ረገድ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ለውጡን  በላቀ ሁኔታ  እንደሚያረገረጋግጡ  አብራርተዋል።

በጉብኝቱ  የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ጽ/ቤት ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና የኢ.ኮ.ሥ.ኮ  አመራሮች ተገኝተዋል።

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.