❇️ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ
👉 ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በግንባታ ግብዓት አቅርቦት እና በሌሎች መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡
👉 ስምምነቱን የኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ተፈራርመውታል፡፡
👉 የሆልዲንጉ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ብሩ ወልዴ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ግዙፍ የኮንስትራክሽን ተቋም እንደመሆኑ የትብብር ስምምነቱ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ለኮርፖሬሽኑ የግንባታ ግብዓትን በተለይም የናሽናል እና የለሚ ሲሚንቶ ምርቶችን በበቂ ሆኔታ የሚያቀርብለት ይሆናል ብለዋል፡፡
👉 ኢ.ኮ.ሥ.ኮ በምህንድስና ዘርፍ፣ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በኮንስትራክሽን ማኑፋክቸሪንግ ጠቃሚ ልምድ ያለው ተቋም ነው ያሉት አቶ ብሩ ፤ ኢስት አፍሪካን ሆልዲንግ ከትብብሩ ከፍተኛ ተጠቃሚ እንደሚሆን ሙሉ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡
👉 ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው ኮርፖሬሽኑ ከዚህ በፊትም ሆልዲንጉ የሚያመርተውን ናሽናል ሲሚንቶ ይጠቀም እንደነበር ገልጸው በቅርቡ በሃገሪቱ ግዙፍ የሆነውን የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካን ገንብቶ ወደ ሥራ ማስገባቱ የኮንክሪት መንገዶችን በሲሚንቶ ለመስራት የሚያጋጥምን የሲሚንቶ ችግር በእጅጉ እንደሚያቃልለው ጠቁመዋል፡፡