የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል ሊያስገነባ ነው
የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል ለማስገንባት ከህንጻ ተቋራጮች ጋር የውል ስምምነት ተፈራረመ፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ታምራት ሙሉ እና የህንጻ ተቋራጮች በፊርማ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ታድመዋል፡፡
የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ዳዊት መሀሪ፥ ማዕከሉ በኦሮሚያ ክልል በረክ ወረዳ በሰንዳፋ ከተማ አቅራቢያ በ14 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገነባ ተናግረዋል፡፡
የማዕከሉ ግንባታ በሁለት ምዕራፍ ተከፍሎ የሚገነባ ሲሆን ሁለት ሀገር በቀል የግንባታ ተጫራቾች ግልጽ ዓለም አቀፍ የጨረታ ሂደትን በማሸነፍ ውል መፈራረማቸውን ገልጸዋል።
ሁለቱም የማዕከሉ ግንባታ ምዕራፎች ከ4 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በሶስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቁም ጠቁመዋል።
የማዕከሉ መገንባት ኢንስቲትዩቱ የኮንስትራክሽን ዘርፉን በጥናት፣ በስልጠና፣ በጥራት አስተዳደር፣ በቴክኖሎጂና የክህሎት ሽግግር ለመደገፍ ያለውን ሚና ያጠናክራል ነው ያሉት።
ማዕከሉ የምርጥ ተሞክሮዎች መቀመሪያ፣ የዘመናዊ ኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥራት ማረጋገጫ እንዲሁም ለሜጋ ፕሮጀክቶች እና በዘርፉ ለሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ትልቅ አበርክቶ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ የትምጌታ አስራት በበኩላቸው፥ የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለሀገር ዕድገት ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰዋል።
ዘርፉን በማዘመንና በማጠናከር ረገድ የኮንስትራክሽን ማኔጅመንትና ምህንድስና ልህቀት ማዕከል መገንባት ትልቅ አብርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በመሆኑም ማዕከሉን በሁለት ምዕራፍ ለመገንባት ውል የወሰዱ ተቋራጮች በጥራትና በፍጥነት በተያዘለት ጊዜ እንዲያጠናቅቁ አሳስበዋል።
ኢንስቲትዩቱም ለግንባታው መፋጠን ተገቢውን ክትትል ከማድረግ ባለፈ በአደረጃጀትና በግብዓት በበቂ ሁኔታ መዘጋጀትና ማሟላት እንዳለበት ጠቁመዋል።