መንግሥት በራሱና በውጭ ተቋራጮች ግንባታዎችን በመቆጣጠሩ የግል ሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ
መንግሥት የመንገድና የሕንፃ ፕሮጀክቶችን ለመገንባት የራሱን የግንባታና የዲዛይን ድርጅቶች በማቋቋም፣ ፕሮጀክቶችን መያዙና የተቀረውን ለውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች እየተሰጠ መሆኑ፣ የአገር ውስጥ የግል የሥራ ተቋራጮች ከሥራ ውጪ መሆናቸውን አስታወቁ።
ይህ የተገለጸው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ከግሉ የግንባታ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ጋር ባለፈው ሳምንት ባደረገው የምክክር ጉባዔ ላይ ነው።
ሚኒስቴሩ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች በአሥር ዓመታት ውስጥ በአገር ውስጥ ያላቸውን የገበያ ድርሻ ወደ 75 በመቶ፣ በቀጣናው ደግሞ የ25 በመቶ ድርሻ እንዲያሳድጉ ዕቅድ ቢይዝም፣ የሥራ ተቋራጮች በበኩላቸው መንግሥት በውጭ ተቋራጮች ላይ ያለውን ከፍተኛ ጥገኝነት፣ የክፍያዎች መዘግየት፣ በቅርብ የተካሄደው የኢኮኖሚክ ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ያሳደረውን ጫናና ሌሎችም ማነቆዎችን በማንሳት፣ መንግሥት በእርግጥ ኢንዱስትሪውን ያውቀዋል ወይ? የሚል ጥያቄ አንስተዋል።
አቶ ሀብታሙ ጌታቸው የተባሉ ተሳታፊ፣ መንግሥት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት ወደ መቆጣጠር እያመራ ነው ሲሉ ወቅሰዋል።
‹‹ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ያው ከመሰላቸትምም ተነስቶ ሊሆን ይችላል፣ ግን በመንግሥት በኩል ኢንዱስትሪውን በብቸኝነት የመያዝ ሒደት ነው እያየን ያለነው። መንግሥት የራሱን የዲዛይን፣ የኮንስትራክሽን ተቋማት እያደራጀና እያዘጋጀ ነው። ስለዚህ ፕሮጀክት ሲመጣ ራሱ ዲዛይን ያደርጋል፣ ራሱ ግንባታ ይፈጽማል፣ በጣም ከእሱ አቅም በላይ የሆነውን ለውጭ ኩባንያዎች ይሰጣል። ስለዚህ ለግሉ ዘርፍ ቦታው ባዶ ነው ብዬ ነው የምገምተው፤›› ብለዋል።
በሌላ በኩል በምክክር መድረኩ የቀረቡ ሁለት ጥናቶች፣ በአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የሚገነቡ መንገዶች በ143 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ110 በመቶ ከተያዘላቸው ጊዜ አሳልፈው እንደሚጠናቀቁ፣ ከተያዘላቸው በጀትም እንዲሁ የመንገድ ፕሮጀክቶች በ18 በመቶ፣ ሕንፃዎች ደግሞ በ35 በመቶ እንደሚያሳልፉ አመላክተዋል።
ከሚኒስቴሩ በኩል ጥናት ያቀረቡት ባለሙያ፣ ‹‹ከዚህ ጥናት በኋላ በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት በተደረጉ የፕሮጀክቶች ክትትል በብዙ ፕሮጀክቶች እያንዳንዱ እየተነጠለ ሲታይ የጭማሪዎቹ መጠን ከዚህም በላይ እንደሆነ ማየት ተችሏል፤›› ብለዋል።
ሳሙኤል ሳህለ ማርያም (ኢንጂነር) የተባሉ ጥናት አቅራቢ በበኩላቸው፣ የውጭ ኮንትራክተሮች የሚይዙት ግንባታ መጠን አነስተኛ ሆኖ፣ ነገር ግን የሚይዙት የገበያ ድርሻ እስከ 62 በመቶ እንደሚደርስ አሳውቀዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞም ያሉ ሥጋቶች ላይ ማብራሪያ ሲሰጡ፣ ‹‹የግንባታ ዘርፉ አሁንም ትልልቅ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ትልቁን ድርሻ የያዙት የውጭ ሥራ ተቋራጮች ናቸው። ይህንን ልንቀይርበት የምንችልበት አካሄድ እስካልተፈጠረ ድረስ አሁን በቅርብ ይህ ንግድ ለዓለም የንግድ ድርጅት ክፍት ነው የሚሆ ነው።
ስለዚህ እኛ ምን ይዘን ነው የምንቀላቀለው? ምን ይዘን ነው ለውድድር ልንቀርብ የምንችለው? በዚህ ሁኔታ ከሆነ የምንቆየው ሁላችንም ተበልተን ነው የምናልቀው፤›› ብለዋል።
በሚኒስቴሩ በኩል የቀረቡት ባለሙያ የውጭ ተቋራጮች ጉዳይ እስከ ሉዓላዊነት የደረሰ ችግር ሊያስከትል ይችላል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ ያሉት የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮችና አማካሪ ኩባንያዎች 35 ሺሕ መድረሳቸውን፣ የባለሙያዎች ብዛትም 151 ሺሕ መሆኑን ጠቅሰዋል።
‹‹በቁጥር ይግዘፍ እንጂ በፌዴራልም ሆነ በክልል ደረጃ የመንግሥት ሜጋ ፕሮጀክቶች በብዛት የተያዙት በሚያሳዝን ሁኔታ በውጭ ኮንትራክተሮች ነው። መጀመሪያ የአገራችንን 75 በመቶ ይዘን የቀጣናውን 25 በመቶ ገበያ ለመያዝ ነው ዕቅዳችን። እነዚህ ቁጥሮች ሳይሆኑ እኛን የሚታደጉን ሄዶ ሄዶ ጉዳዩ የሉዓላዊነት ጉዳይ ጋር ይመጣል፤›› ብለዋል።
ሳሙኤል (ኢንጂነር) የውጭ አገር የሥራ ተቋራጮች ከዚህም ባሻገር ከበጀት ጋር የተያያዙ ጫናዎች እየፈጠሩ መሆናቸውን አሳውቀዋል።
‹‹አንድ በውጭ ተቋራጭ የሚሠራ በጀቱ 800 ሚሊዮን ብር የነበረ ፕሮጀክት፣ ግንባታውን በመሀል አቁመው 3.2 ቢሊዮን ብር ካልከፈላችሁን አንሠራም ማለታቸውን እናውቃለን። ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚሠራው ስታዲየምን መጥቀስ ይቻላል፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጀመር በጀቱ ከሁለት ቢለዮን ብር ጥቂት ነበር ከፍ የሚለው። ግን በኋላ ላይ እስከ 12 ቢሊዮን ብር አይበቃም ማለታቸውን ሰምተናል፤›› ብለዋል።
ባለሙያው ይህ ዓይነቱ አሠራር ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች እንደማይሠራ ገልጸው፣ ኩባንያዎች፣ ከባንኮች ከግንባታ ዕቃ አቅራቢዎች ጋር ተያይዞ ሊሠራበት የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ገልጸዋል።
የውጭና የአገር ውስጥ ተቋራጮች አፈጻጸምን በተመለከተ ለአብነት የቻይና ተቋራጮችን አፈጻጸም ያነሲ ሲሆን፣ ፕሮጀክቶችን በሚያገኙበት ወቅት ዕቃ አቅራቢ ፋብሪካ አዘጋጅተው፣ አማካሪ ኩባንያው የራሳቸው አገሮች ኩባንያ መሆኑንና ንዑስ ተቋራጮችም በራሳቸው እንደሚያዘጋጁ ጠቅሰው፣ የቻይና ኤግዚም ባንክ እዚህ ለሚሠሩ ሥራ ተቋራጮች የገንዘብ ፍሰት (Cash Flow) ችግር እንዳያጋጥማቸው እንደሚያቀርብላቸውና በእነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ የሚያልፍ የውጭ ተቋራጭ በተገቢው ሁኔታ ሥራውን አከናወነ እንደሚባል ተናግረዋል።
‹‹የእኛ ሥራ ተቋራጭ እኮ በክፍያ ምክንያት የሚያጋጥመው ጫና ምናልባት መንግሥትና ዘርፉ የእውነት ይተዋወቃሉ?› የሚል ጥያቄ እንዳነሳ ነው የሚያደርገኝ። የእውነት ይተዋወቃሉ ወይ? ዘርፉ እኮ እየሞተ ነው ያለው። ክፍያ በአግባቡ ካልተከፈለው የፕሮጀክት ቆይታ በከፍተኛ ሁኔታ ነው እየጨመረ የሚመጣው። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት የሚያስችል የፋይናንስ ሲስተም ያስፈልጋል፤›› ብለዋል።
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ደኤታ አቶ የትምጌታ አሥራት በበኩላቸው፣ መንግሥት ፕሮጀክቶችን ለአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች ለማስተላለፍ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል።
በሌላ በኩል በውይይት መድረኩ ከተነሱ ዋነኛ ጉዳዩች የውጭ ምንዛሪ ላይ የተደረገው ሪፎርም በኢንዱስትሪው ላይ ሌላ ጫና ይገኝበታል።
‹‹የኢንዱስትሪው ገበያ የሚንቀሳቀሰው በጥቁር ገበያው ነበር፡፡ እዚህ ላይ ምንም ልንወሻሽ የሚገባ ነገር የለም። ለምን አንድ አቅራቢ ዕቃ ከውጭ አምጥቶ ለመሸጥ ለሒደት ማስፈጸሚያ (Procedure Issue) ብቻ የባንክን ምጣኔ ይጠቀማል። ለምሳሌ 60 ብር በነበረበት ሰዓት ለፕሮሲጀር የባንክን ይጠቀማል፡፡ ሌላውን ግን በጥቁር ገበያ ሴኪውር ያደርጋል። ከዚያ በኋላ ግን ዋጋ ሲያወጣ በጥቁር ገበያው ምጣኔ ነው የሚያወጣው፡፡ በዚህ ምክንያት የፕሮጀክት ዋጋ ከፍ ይላል፤›› ብለዋል።
በተጨማሪም፣ ‹‹ምንዛሪ በገበያው መወሰን ሲጀምር በፊት ግብር የሚከፍል የነበረው ባንክ በሰጠው ምጣኔ ነበር። ለምሳሌ ምንዛሪው ሰባት ብር ከነበረ፣ አሁን ግን 125 ሲሆን ግብሩም በዚያው መጠን ከፍ ይላል ምክንያቱም በደረሰኝ ገንዘቡን ዝቅ አያደርግም። እንደነዚህ ዓይነት ዕርምጃዎችን እንዳይሄድና ኃላፊነት እንዲወስድ ብሔራዊ ባንክ አስገዳጅ መመርያ አውጥቶበታል። ያንን ስናይ ደግሞ ከኢንሹራንስና ከትራንስፖርት ጋርና ከሌሎች ሎጂስቲክስ ጉዳዮች ጋር የተገናኙ የወጪ ክፍያዎች አሉበት። ስለዚህ በኢኮኖሚክ ሪፎርሙ የኮንስትራክሽን ዘርፉ አሁንም እንደገና ደግሞ ሌላ ተጋላጭነት አጋጥሞታል፤›› ሲሉ አብራርተዋል።