በግንብ የታጠሩ 22 አስደናቂ የአለማችን ታሪካዊ ከተሞች።
**
…የቀጠለ
11. የሀረር ጀጎል ግንብ / Harar
የሐረር ጀጎል ግንብ የተገነባው በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን ከኢማም አህመድ አስተዳር በኋላ በአሚር ኑር አማካኝነት ነው።
ግንቡ የተገነባበት ዋና ምክንያት የሐረርን ከተማ ከወራሪዎች ለመከላከል ሲባል እንደሆነ ይነገራል፤ ሐረር በምራቅ አፍሪካ የንግድ ማዕከልም ነበረቸ።
ስለ ግንቡ አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎች
🔷አጠቃላይ ርዝመቱ 3342 ሜትር፣
🔷 ከፍታው4.5 ሜትር፣
🔷 የግንቡ ውፍረት ከ40-50 ኢንች፣
🔷 ግንቡ ያረፈበት የቦታ ስፋት 48 ሄክታር፣
🔷 በግንቡ ውስጥ የሚገኙ መስጊዶች ብዛት ከ90 በላይሲሆኑ፣
🔷በግንቡ ውስጥ ከ2000 በላይ ጥንታዊና ባህላዊ ቤቶች ይገኛሉ፣
🔷 የሐረረ ጀጎል በምስራቅ አፍሪካ በግንብ የተከበበች ብቸኛ ጥንታዊ ከተማ ናት።
10. ታሩዳንት/ Taroudant
ታሩዳን በሞሮኮ ምትገኝ አስደናቂ እና ውብ የበርበሮች በግንብ የታጠረች ከተማ ናት፤ ከተማይቱም የሞሮኮዋ ማራካሽ ከተማ ቅድመ አያትም በመባል ትጠራለች፤ ታሩዳንት የተፀነሰችውም በ16ተኛው ክፍለ ዘመን ነበር።
9. ቶሌዶ / Toledo
ቶሌዶ የቀድሞው የእስፔን ስርወመንግስት ዋና መቀመጫ የነበረች ስትሆን፤ ታሪኳ ግን የሚጀምረው ከሮማውያን አገዛዝ ግዜ አንስቶ እንደሆነ ታሪክ ያስረዳል።
ቶሌዶ በእስፔን ሙስሊም ሱልጣኔቶች አገዛዝ ስር ወድቃ የነበረ ቢሆንም በ 1500 ዓመት ገደማ ማድሪድ የእስፔን መናገሻ አስክትሆን ድረስ ቶሌዶ መናገሻ ከተማ ነበረች፨
8. ፒንጊያው /Pingyao
የቻይናዋ ፒንጊያው በአለማችን ከሚገኙ ታሪካዊ ከተሞች ጥንታዊ ይዘቷን ሳትለቅ የዘለቀች ከተማ እንደሆነች ተመስክሮላታል።
ስድስት መግቢያ ዋና በሮች እና 72 የጥበቃ ማማዎች ያሏት ይች ከተማ በሆነ ወቅት አጥሯ ፈርሶ የነበረ ቢሆንም ዳግም ሊታደስ ችሏል።
7. ኦቢዶስ /Obidos
በከፍታ ቦታዎች የተገነባችው ይች ከተማ በ8ተኛው ክፍለዘመን በሞርሞር ሙስሊሞች እንደታነፀች ይነገራል።
በ14 ተኛው ክፍለ ዘምን ግንቡ በፓርቹጋል ንጉስ አገዛዝ ስር እንደወደቀ እና የግንቡ ይዘት ላይም ለውጥ እንደተደረገበት ይነገራል።
6. ዢያን / Xi’an
ዢያን በቻይና ከሚገኙ ከተሞች ጥንታዊት ከተማ ስትሆን፤ 3100 አመት ገደማ የስቆጥራለች።
በ 1000 አመት ታሪኳም 13 ስርወመንግስታት ሲፈራረቁባት 73 ንጉሶች ደግም ይህችን ከተማ እንደመሩባት ይነገራል።
የሲልክሮድ ንግድ መስመር እንደነበረች እና የዝነኛው ትራኮቴ ሰራዊት መገኛም ነበረች።
ዢያን በ14ተኛው ክፈለዘመን በሚንግ ስርወመንግስት ስር ስትወድቅ እድሳት ተደርጎላታል።
5. ኢቻን ካላ/ Itchan Kala
የዩዝቤኪስታኗ በግንብ የታጠረችው ከተማ የተገነባችው በፀሀይ በደረቁ የጭቃ ጡቦች በመሆኑ ግንቡ ልዩ ያደርገዋል።
ኢቻን ካላ በርካታ ጊዜ የመደርመስ አደጋ የገጠማት ቢሆንም ዳግም እየታነፀች ቆይታለች።
4. አቪላ / Avila
በአስራ አንደኛው ክፍለዘመን እንደተገነባች ሚነገርላት ይች የእስፔኗ ከተማ የታነፀችው ድንጋያማ በሆነ ኮረብታማ ስፍራ ነው።
3. ካርካሶኔ Carcassonne
ካርካሶኔ በፈረንሳይ የምትገኝ በደንብ ታሪካዊ ይዘታቸውን ከጠበቁ በግንብ ከታጠሩ ከተሞች በቀዳሚነት ልትጠቀስ የምትችል ናት።
ይች ከተማ በአውሮፓ ከሚገኙ መሰል ከተሞችም በትልቅንቷ ተወዳዳሪ የላትም።
ካርካሶኔ ‘ሮቢን ሁድ’ የመሰሉ እና ሌሎች ፊልሞች ቀረፃ የተካሄደባት ከተማም ናት።
2. እየሩሳሌም/ Jerusalem
እየሩሳሌም የሶስቱም የአብራሀም እምነቶች ቅድስት ከተማ ስትሆን፤ በአሁኑ ወቅት በፍልስጤም እና እስራኤል የቁርሾ መነሻ የሆነች ታሪካዊ ዝነኛ ከተማ መሆንዋ ይታወቃል።
እየሩሳሌም ወይም አል-ቁድስ የረዥም ታሪክ ባለቤት ስተሆን የመካከለኛው ክፍለ ዘመን ታሪኳ በተለይ እየሩሳሌም በግንብ ለመታጠሯ የኦቶማን ስርወመንግስት ሰፊውን ድርሻ ይወስዳል።
1. ዱብሮሜክ / Dubrovnik
በክሮሺያ ባህር ዳርቻ የምትገኘው ዱብሮሜክ የተጠበቀች ውብ በግንብ የታጠረች ከታማ ናት።
ይች ከተማ በሜድትራኒያን ባህር ጠረፍ የምትገኝ ስትሆን በጥንት ዘመን የባህር በር ንግድ ይቀላጠፍባት የነበረች የበለፀገች ከተማ ነበረች።
በ12-17ተኛው ክፍለዘመን አካባቢ እንደተቆረቆረች የሚነገርላት ቢሆንም ታሪካዊ ይዘቷን አሁን ድረስ የጠበቀች እንደሆነች ይነገራል።
(https:www.touropia. com)