¶ ብቸኝነት ሲሰማህ ማሰብ ከቻልክ የሀሳብህ ጓደኛ ነህ።
¶ ማሰብ ካልቻልክ ብቻህን ነህ።
¶ መነጠል የስጋ ሳይሆን የአሳብ ስሜት ነው።
¶ ብቸኝነትህን ሀሳብህ ሲጋራ የሀሳብ ጓደኛ አለህ።
¶ ብቸኝነትም ጓደኝነትም ስጋ አይደለም። የአብሮነትና የመነጠል ስሜት ነው።
° ከሰው ጋር ስትሆን ለብቻህ እንደሆንክ ከተሰማህ በግርግር መሀል ብቸኛ ነህ።
° በስጋህ ብቻህን ሆነህ ከአሳብህ ጋር አብረህ ከሆንክ አንተማ ጓደኛ አለህ።
° ከቻልክ የወዳጅ አስፈላጊነትን ቀንስ።
° ሰው ብታጣም ያጣኸው ስጋ ነው።
° አብሮህ የሆነ አላቂ ነው።
° ዛሬ የሚቀርብህ ነገ የሚርቅ ነው።
° ወሳኙ ጉዳይ ህሊናህን አለማጣትህ ነው።
° የሌላ ስጋ ሲለይ አሳብህ ካንተ ጋር ነው።
.
መለየት የስጋ ነው። ብቻህን እንዳልሆንክ ከተሰማህ የአንተ ጓደኛ ስሜትህ ነው።
ይስማዕከ ወርቁ!
👉ቻናሉን ከወደዳችሁት ቢያንስ ለ አንድ ሰው Share ያድርጉ!
####JOIN####
👇👇👇👇👇👇
👉
@ethiopiameker👉
@ethiopiameker👉
@ethiopiameker⚠️SHARE