የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በአዋጅ ቁጥር 1112/2011 አንቀፅ 4/8 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ያዘጋጃል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ይከልሳል፡፡ በዚህም መሠረት የ3ኛዉ እትም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከመንግስትና ከግል ዘርፍ የተወጣጡ የሕክምና የመድኃኒትን ባለሙያዎች የቴክኒካል የስራ ቡድን ተቋቁሞ ለአንድ ዓመት ያህል ሲሰራ የቆየ ሲሆን በጤና እና ፋርማሲዩቲካል ሳይንስ አዳዲስ ለውጦችን መሰረት በማድረግ እንዲሻሻል በማደርግ ተዘጋጅቷል፡፡
የተከለሰው ፎርሙላሪ በቅርቡ ስራ ላይ የዋለውን 7ኛውን እትም ብሔራዊ መሠረታዊ የመድኃኒት መዘርዝርን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ ሲሆን ፎርሙላሪው በተለያዩ ዙሮች ከተለያዩ ዩኒቨርስቲ እና ሆስፒታሎች በተወጣጡ የመስኩ ባለሙያዎች በምክክር እንዲዳብር ተደርጓል፡፡
ከህዳር 20-21/ 2017 ዓ.ም በአደማ ከተማ በ3ኛው እትም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ ዙርያ የክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት፣ የክልል ጤና ቢሮ የፋርማሲ አገልግሎት ባለሙያዎች እና ከተለያዩ ሆስፒታሎች የተወጣጡ ባለሙያዎች የተሳተፉበት የምክክር አውደ ጥናት ሲካሄድ የባለስልጣኑ የመድኃኒት ደህንነት ክትትልና የሕክምና ሙከራ መሪ ስራ አስፈፃሚ ተወካይ ኃላፊ አቶ ተሽታ ሹቴ እንደተናገሩት ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ በየአምስት ዓመቱ መዘጋጀት ያለበት ሲሆን በዚሁ መሠረት የመጀመሪያው እና የሁለተኛው በ2000 እና በ2006 ዓ.ም ተዘጋጅቷል፡፡ ይሁንና 3ኛውም ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪ በ2011 ዓ.ም መዘጋጀት የነበረበት ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን መቆየቱን አስታውቀው በተለያዩ ባለድርሻ አካላት የዳበረው 3ኛው ብሔራዊ የመድኃኒት ፎርሙላሪው በቅርቡ በባለስልጣኑ ማኔጅመንት ፅድቆ ታትሞ ስራ ላይ እንደሚውል አስታውቀዋል፡፡