ከአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ጋር አብሮ መስራት የምግብ ጥራትንና ደህንነትን ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ታሃሳስ 23/2017 አዲስ አበባ፦ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከኦሮሚያ ኢንዱስትሪ ፓርክ የልማት ኮርፖሬሸ(OIPDC)ን ጋር የምግብ ጥራትንና ደህንነትን ለማስጠበቅ የጋራ መግባብያ ሰነድ ተፈራረሙ፡፡ በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት የምግብ ጥራትና ደህንነት ማስጠበቅ ዋና ተግባራችን እንደመሆኑ ተቋማችን የምግብ አግሮ ኢንቨስትመንቶች ከመሰረቱ ጀምሮ የተሻለ ደህንነትና ጥራት ኖሯቸው ምርታቸውን እንዲያመርቱና ለገበያ እንዲያቀርቡ እንደግፋቸዋለን፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ኢንቨስተሮች መዋለ-ንዋያቸውን በምግብ አግሮ-ፕሮሰስ ላይ እንደያፈሱ በማበራታታት የማሰተናገድ አቅማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደግን ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የበኩላችንን እያተወጣን አንገኛለን ያሉ ሲሆን ፊርማውም ከወረቀት አልፎ ተግባራዊ ይሆናል ሲሉ ተነግረው ሁሉም የአግሮ ፕሮሰሲንግ ፓርኮች የምግብ ጥራት ምርመራ ላብራቶሪ እንዲያደረጁ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡
የኦሮሚያ አግሮ ፕሮሰሲንግ እንዱስትሪ ፓርክ ምክትል ስራ አሰኪያጅ አቶ መንግስቱ ረጋሳ በበኩላቸው ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ጋር ለመስራት በመፈራራማችን ለስራችን መቃናት ግማሽ መንገድ የተጓዝን ያህል ይሰማናል ያሉ ሲሆን ከህዳሴ ግድብ በመቀጠል ብዙ ገንዘብ የሚፈስበት ዘርፍ ኢንዱስተሪ ፓርክ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የባለሀብቶች ጥያቄ ላመረቱት የምግብ ምርት የገበያ ፈቃድ ማግኘት ነው፤ በመሆኑም ከተቋሙ ጋር ስንሰራ የምግብ ጥራትና ደህንነትን በማስጠበቅ ሁሉንም ባለድርሻ አከላት ተጠቃሚ እናደርገለን ሲሉ ተነግረዋል፡፡