የባዮኢኩቫለንስ ጥናት ፍኖተ ካርታ ትግበራ በጥሩ መግባባት ላይ ተመሥርቶ እየተሠራ እንደሚገኝ ተገለፀ
ጥር 21/2017 በተካሄደው አውደ ጥናት በአገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶች ንፅፅራዊ የፈዋሽነት ደረጃን የሚፈትሸው የባዮኢኩቫለንስ ጥናት ፍኖተ ካርታ ትግበራ ተገምግሟል፡፡
የባዮኢኩቫለንስ ጥናት ፍኖተ ካርታ ትግበራ ደረጃ ክትትልና ግምገማ በየወሩ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከጤና ሚኒስቴርና ከአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም በተወከሉ ባለሙያዎች በጋር የሚያካሂድ ነው፡፡
የመድሃኒቶች ባዮኢኩቫላንስ ጥናት በእንክብል መልክ ተዘጋጀተው በአፍ የሚወሰዱ መድኒሃቶች ባበለስልጣን መስሪያ ቤቱ የገበያ ፈቃድ ለማግኘት ከሚያስፈልጉ መሰራታዊ መስፈርቶች አንዱ መሆኑንና ከዚህ ቀድም ከውጭ ሀገር በሚገቡ መድኃኒቶች ላይ ብቻ ተግባራዊ ሲሆን የነበረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ፍኖተ ካርታው ከተዘጋጀ ወዲህ ደረጃ በደረጃ በአገር ውሰጥ ለሚመረቱ መድኃኒቶች ጭምር ጥናቱ መካሄድ እንደለበት ከዓለም ጤና ድርጅት በቀረበው ሀሳብ መሰረት የባዮኢኩቫለንሱ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መግባቱ ታውቋል፡፡
የፍኖተ ካርታው መዘጋጀት የመድሃቶችን ፈዋሽነት በአስተማማኝ ሁኔታ የሚያረጋግጥ፣ የአገር ውስጥ የመድኃኒት አምራቾችን አቅም የሚገነባ፣ ምርቶቻቸውን ከአገር ውጭ ለመላክ ዕድል የሚፍጥርና አጋርነትና ትብብርን በዘርፉ የሚፈጥር ነው፡፡