የአገሪቱን የመድኃኒት የቁጥጥር ስርዓት ለመገምገም የዓለም ጤና ድርጅት ለሚያደርገው የመጨረሻ የኦዲቲንግ ስራ ተገቢ የማስተካከያ ስራዎች በትኩረት እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገለፀ፡፡
ጥር 24/2017 ዓ.ም አዳማ ከተማ በተዘጋጀው የግምገማ መድረክ ላይ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ሰኔ 13/ 2015 ከተካሄደው የመጀመሪያ ኦዲት በኃላ ተቋማዊ የልማት ዕቅድ በማዘጋጀት እንደ ቁጥጥር ዘርፉ መስተካከል ያለባቸውን ዶክሜንቶችና ሌሎች ጉዳዮች በማስተካከል ለሁለተኛ ዙር የኦዲቲን ስራ አስፈላጊው ዝግጅቶች ተደርጓል፡፡
እንደ አገር የመድኃኒት ቁጥጥር ስርዓቱ በመገምገም ማቹሪቲ ሌቭል ስሪ ለማግኘት ባለስልጣኑ ከራሱ የስራ ክፍሎች በተጨማሪ ባለሙያዎችን የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ድረስ በመላክ እስከ አራት የሚደርሱ ድጋፋዊ ክትትሎች ማድረጉን ዋና ዳይሬክተሯ ጠቁመዋል፡፡
በዛሬው ዕለትም የአራተኛው የድጋፋዊ ክትትሉ ያለበት ደረጃን በመገምገም የዓለም ጤና ድርጀት ለሚያደርገው የመጨረሻ ኦዲት የሚያበቁ የማስተካከያ ስራዎች በሁለት ቀናት ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ ዋና ዳይሬከተሯ አብራርተዋል፡፡
በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የባለስልጣኑ የመድኃኒት ዘርፍ እና ጉዳዮች የሚመለከታቸው የስራ ክፍሎች እንዲሁም የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ የከተማ አስተዳደር የጤና ግብዓት ተቆጣጣሪ አካላት ኃላፊዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡