የሚኒስትሮች ምክር ቤት 581.98 ቢሊየን ብር ተጨማሪ በጀት በማጽደቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ
የሚንስትሮች ምክር ቤት ትናንት ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው 40ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ምክር ቤቱ ተወያይቶ ውሳኔ ካሳለፈባቸው ጉዳዮች መካከል በፌደራል መንግስት የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያ ይገኝበታል።
የተጨማሪ በጀት እና የወጪ አሸፋፈን ማስተካከያው የተሻሻለውን የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ ማስፈጸም በሚያስችል መልኩ የመንግስት የፋይናንስ አቅምና ተጠባቂ ገቢዎችን ታሳቢ በማድረግ እንዲሁም የተጨማሪ በጀት ታሳቢዎችንና የወጭ ታሳቢዎችን ግምት ውስጥ በማስገባት መዘጋጀቱን ከጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ መሰረት ለመደበኛ ወጪዎች እና የወጪ አሸፋፈን ለማስተካከል የሚውል 581.9 ቢሊዬን ብር ለምክር ቤቱ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ማስተካከያ ረቂቅ አዋጁ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ያፀደቀው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለ2017 በጀት አመት አንድ ትሪሊየን ብር የሚጠጋ በጀት ካፀደቀ ከአምስት ወራት በኋላ መሆኑ ተጠቁሟል።
ይህም የ2017 ዓ.ም አጠቃላይ በጀት ከ1.5 ትሪሊየን ብር በላይ እንደሚያደርገው ተመላክቷል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L