Exit Exam For All Department


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


For all department GC Exit Exam batch
For info and promo @akismart_One

Bog‘liq kanallar  |  O‘xshash kanallar

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


Exit Exam Study Bot — ለኢትዮጵያ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ሁሉንም የጥናት ፍላጎቶቻችሁን የሚያሟላ የጥናት አጋዥ። 🇪🇹


📄ያለፉ የመውጫ ፈተና ጥያቄዎች

📝 የልምምድ እና ሙሉ ፈተናዎች

🧠 ብልህ ልምምድ + የስህተት መዝገብ

📊 እድገታችሁን ተከታተሉ

🏆 የደረጃ ሰንጠረዥ + ሽልማቶች

⚔️ Duel — ከጓደኞቻችሁ ጋር ተወዳደሩ

📚 ማስታወሻዎች + የጥናት ምንጮች

🚀 Pro — ያልተገደበ ልምምድ + ሁሉም Department ክፍሎች

🔗
https://t.me/ExitExamStudyBot?start=link_THLV4PP

ይሞክሩት!👆


🔴አዳዲስ የሚወጡ ሰራዎችን በዚህ channel ለመልቀቅ ነበር :: የስራ post እንዲደረግ ትፈለጋላችሁ??
So‘rovnoma
  •   አዎ እፈልጋለሁ
  •   አይ አልፈልግም
51 ta ovoz


የፈተና ክፍያ ተመን ጭማሪ ተደረገ

​የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሚመራበት ደንብ ቁጥር 260/2004 መሠረት የሚሰጣቸውን የፈተና አገልግሎቶች በመንግሥት በጸደቀ ተመን መሠረት ያስተዳድራል።

በአዲሱ የመንግሥት አገልግሎት አስተዳደር ሪፎርም መሠረት የተሻሻለው ክፍያ ተመን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 593/2016 መሠረት ከሐምሌ 22/2016 ዓ.ም. ጀምሮ ተገቢ ሆኗል።

​በመሆኑም በተሻሻለው ተመን መሠረት በእያንዳንዱ ተፈታኝ ላይ ለምዝገባና ለፈተና አሰጣጥ:-

👉 ለዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና 2,000 ብር

👉 ለድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና 3,500 ብር

👉 ለሙያ ብቃት ፈተና ምዘና 3,500 ብር እና

👉 ለሊቃውንት ማረጋገጫ ፕሮግራም ፈተና 950 ብር በምዝገባ ሲስተሙ ላይ በተቀመጠው የክፍያ ሥርዓት የሚፈጸም ይሆናል።

እንዲሁም የተሻሻለው ተመን ከመውጣቱ በፊት ለተከፈሉ ፈተናዎች የሚከፈል ቀሪ ክፍያዎች 750 ብር በእያንዳንዱ ተፈታኝ ተሰልፎ እንዲፈጸም፤ ያልተከፈሉ ክፍያዎችም የተሻሻለው ተመን በሲስተሙ ላይ ከመጫኑ በፊት በመክፈል ተገቢውን አገልግሎት እንድታገኙ እናሳስባለን።


#MoH

ጳጉሜን 03/2018 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ከዛሬ መስከረም 06/2019 ዓ.ም ጀምሮ ውጤታችሁን ማየት እንደምትችሉ ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባት የብሔራዊ መለያ ቁጥር (FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁ. 952 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

🔔 ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከነገ መስከረም 07/2019 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፈቃዳችሁን 12ኛ ክፍል በጨረሳችሁበት ክልል ማውጣት ትችላላችሁ።


Academic Calendar for HEIs (2019 E) FINAL.pdf
1.8Mb
የ 2019 ዓ.ም የከፋተኛ ትምህርት አካዳሚክ ካላንደር!

👉Exit Exam --ሰኔ 3--13/2019

👉Grade 12 Exam -- ሰኔ 28--ሐምሌ 9/2019

የትምህርት ሚንስትር አጠቃላይ የአመት ካላንደር ከላይ ተያይዟል


#NGATResult

ነሐሴ 20 እና 21/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ውጤት ተለቋል።

ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et

ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'NGAT Results' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።


#NGAT

ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

ትናንት ነሐሴ 20/2018 ዓ.ም መሠጠት የጀመረው የNGAT ፈተ፤ ዛሬ ጠዋት እየተሰጡ በሚገኙ ፈተናዎች እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል፡፡ የተወሰኑ ዩኒቨርሲቲዎች ፈተናውን ትናንት ሰጥተው አጠናቀዋል፡፡

ምስል፦ እንጅባራ፣ ዋቸሞ፣ ወራቤ እና ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲዎች


#Update‼
#NGAT
 ማሳሰቢያ NGAT ተመዝጋቢዎች በሙሉ

👉 አገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ተመዝግባችሁ የፈተና ጣቢያ ምርጫችሁን Update እያደረጋችሁ ያላችሁ ተፈታኞች፣ በፈተና ሲስተሙ ላይ የሚገኝ የትኛውንም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲ በፈተና ማዕከልነት መምረጥ ትችላላችሁ።
 
👉 የተመዝጋቢዎች Username፣ Password እና Entrance Ticket የ NGAT ፈተና ከሚሰጥበት ሁለት ወይም ሦስት ቀናት ቀደም ብሎ በእያንዳንዳችሁ Dashboard ላይ የሚመጣላችሁ ስለሆነ ዳሽቦርዳችሁን ቶሎቶሎ ቼክ አድርጉ።

መልካም የፈተና ዝግጅት ጊዜ ይሁንላችሁ ‼️


@GATExams Wollo University GAT Model Exam 1 2017.pdf
319.7Kb
በወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የተዘጋጀ NGAT / GAT ሞዴል ፈተና -1 ነው፡፡ አንብቡት ትጠቀሙበታላቸሁ፡፡


@GATExams Wollo University GAT Model Exam 2 2017.pdf
346.7Kb
በወሎ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የተዘጋጀ NGAT / GAT ሞዴል ፈተና -2 ነው፡፡ አንብቡት ትጠቀሙበታላቸሁ፡፡


Exit Exams For all department!!

በዚህ Channel ብዙ የ Exit Exam ፈተናዎችን ለቀናል 👏👏

የ ሁሉም ደፓርትመንት ፈተናዎች አሉ

ቀጣይ ብዙ ፈተናዎችን ለቀጣይ ተፈታኞች እንለቃለን : ለ ሁሉም ይሄን መልክት አድርሱ

https://t.me/Exit_Exams
https://t.me/Exit_Exams


የNGAT ምዝገባ ለማድረግ በቴሌብር ክፍያ ከመፈፀም ጋር አጋጥሞ የነበረው ችግር ከትናንት ምሽት ጀምሮ መፈታቱ ተገልጿል፡፡ አሁን ላይ አገልግሎቱ በደንብ እየሠራ በመሆኑ ክፍያዎን በመፈፀም ምዝገባዎን ማድረግ ይችላሉ፡፡

ለድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ምዝገባ እስከ ቅዳሜ ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም ብቻ የሚከናወን መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል፡፡

ምዝገባዎን ያድርጉ 👇
https://ngat.ethernet.edu.et

ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ የግድ እንደሚያስፈልግ ያስታውሱ፡፡





14 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.