የሞሮኮ ብሔራዊ ነጻነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሃመድ ሲዲቂ ማን ናቸው...
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በብልጽግና ፓርቲ ሁለተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ማምሻውን አዲስ አበባ የገቡት የሞሮኮ ብሔራዊ ነጻነት ሰልፍ ፓርቲ ተወካይ ሞሃመድ ሲዲቂ ማን ናቸው...
የ68 ዓመቱ መሃመድ ሲዲቂ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ከሃሰን ሁለት ዩኒቨርሲቲ አግኝተዋል።
በተጨማሪም በ1990 ከሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ በአግሪ ካልቸራል ኢኮኖሚክስ የዶክትሬት ዲግሪ አላቸው።
መሃመድ ሲዲቂ ከ1984 እስከ1990 በመምህርነት፣ ከ2005 እስከ 2021የሞሮኮ ሳይንስና ምርምር ማዕከል ዳይሬክተር እንዲሁም የሃሰን ሁለት ዩኒቨርሲቲ አግሮ ኢኮኖሚክስ ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል።
ከ2021 ጀምሮም የግብርና፣ የአሳ ሃብት፣የውሃ እና የደን ልማት ሚኒስትር በመሆን ሀገራቸውን እያገለገሉ ይገኛሉ።