ማህበራዊ ግዴታን እንደማስታወቂያ...
ተቋማት ከትርፍ ባሻገር በተለያየ መንገድ ማህበራዊ ግዴታቸውን መወጣታቸው፣ በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ፣ በድርቅ ምክንያት የተቸገሩ፣ በድህነት ምክንያት ለተቸገሩ ወገኖች ከትርፋቸው ቀንሰው ማካፈላቸው፣ ለማህበረሰቡ መልሰው መስጠታቸው የሚያስመሰግናቸው ተግባር ነው።
ይሁንና ይሄንኑ ዜና ለማስታወቂያ ለመጠቀም እርዳታ የሚሰጣቸውን ግለሰቦች ፎቶግራፍ እያነሱ እና እየቀረጹ በየማህበራዊ ድረገጻቸው ማካፈላቸው በተለይም በረመዳንና በወርሀ ፋሲካ የጾም ወራት፣ ልግስና በድብቅ መስጠት በሚሰበክባቸው ወራት የተረጂዎችን ፎቶግራፍ መለጠፋቸው ከማስተዋወቅ ይልቅ ሰዎችን የሚያሳቅቅ እና ዓላማውን ያልመታ የማስታወቂያ ሙከራ ከመሆን የዘለለ ትርፍ ስለማያስገኝላቸው ከእዚህ ድርጊት ቢታቀቡ ብዬ ቀና ምክሬን አስተላልፋለሁ።