«የአያቴን ስም ስትጠይቀኝ ኮስተር ብዬ “ሸሌ” አልኳት፡፡ “እንዴት ሸሌ ትለኛለህ” ብላ ጮኸች፤ ተገፍትሬ ወጣሁ፡፡»
#FatMereja I “ሰውን ማሳቅ ከባድ ነው፤ ኑሮው ተጭኖታል” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ናፍቆት ዮሴፍ ከ12 አመት በፊት በአዲስ አድማስ ጋዜጣ የወጣ ቃለምልልስ እናስታውሳችሁ።
ኮሜዲያንና ድምፃዊ ታሪኩ ሰማኒያ ሸሌ፤ ሀዋሳ ውስጥ ተወልዶ ያደገ ድምፃዊ፣ ኮሜዲያንና ተዋናይ ነው፡፡ “ጫት ያመረቅናል” በሚለው ነጠላ ዜማው የሚታወቅ ሲሆን መድረክ ላይ በሚያቀርባቸው ቀልዶቹ በተለይ በሀዋሳ ከፍተኛ እውቅናን አትርፏል፡፡
“ሸሌ” በተሰኘው የአያቱ ስም ምክንያት ስለገጠሙት ችግሮች እንደሚከተለው ዘና ፈታ ያደርገናል።
ናፍቆት "እንተዋወቅ?" ስትለው "ስሜ ታሪኩ ሰማንያ ሸሌ ይባላል፡፡" ብሎ ይመልሳል።
"ሸሌ የአያትህ ስም ነው? ትርጉሙ ምን ማለት ይሆን?"
ረጅም ሳቅ…
"አንቺ ለምን የአያቴ ስም ላይ ትኩረት እንዳደረግሽ ገብቶኛል፡፡"
"...ሸሌ የሚለው ቃል በህብረተሰቡ ምን ያህል ከባድና ምን ማለት እንደሆነ ስለምታውቂ ነው፡፡ ለማንኛውም ሸሌ የአገር ስም ነው አርባ ምንጭ አካባቢ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ናት፡፡ እናም የአያቴ እናት እርጉዝ ሆነው በዚያ አካባቢ ሲያልፉ ድንገት ምጥ ይዟቸው አያቴ እዛች ከተማ ውስጥ በመወለዳቸው ነው ሸሌ የሚል ስያሜ ያገኙት..."
ጋዜጠኛዋ የሚከተለውን ጥያቄ አቀረበች
"...ሸራተን ስራህን ስታቀርብ ስምህን በእንግሊዝኛ ተርጉመህ ሰውን አስቀኸው እንደነበር ሰምቻለሁ፡፡ እስኪ ለአንባብያን ተርጉሞላቸው…"
"የዛን ቀን እንዲህ አይነት ስም በአለም የለም፣ በጊነስ ላይ መመዝገብ አለበት ብለው አስተያየት የሰጡ ነበሩ፡፡ ስሜ ታሪኩ ሰማኒያ ሸሌ ነው፤ በእንግሊዝኛ ደግሞ “ሒስትሪ ኤይቲ ባር ሌዲ” ይባላል ስላቸው፣ ህዝቡ መሳቁን ማቋረጥ አልቻለም ነበር፡፡"
"ከአያትህ ስም ጋር በተያያዘ የገጠሙህ ፈተናዎች እንዳሉ ሰምቻለሁ፡፡ እውነት ነው?... ከአባትህ ሞት ጋር በተያያዘ ስማቸው ሲነሳ ብዙ ነገር መባሉን ከጓደኞችህ ሰምቻለሁ፡፡ እስኪ አጫውተኝ?"
"...በነገርሽ ላይ አባቴ አቶ ሰማኒያ ሸሌ ከ1986 ወዲህ እስከሞተበት ጊዜ ድረስ ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ በሚባለው በሽመና ስራ ላይ ብዙ እውቅና ነበረው፡፡ የሽመና ኢንዱስትሪ አስፋፍቶ ከ30 በላይ ሰራተኞች ያስተዳድር ነበር፤ ብዙ ሰው ያውቀዋል፡፡ በአጋጣሚ በወጣበት በይርጋለም ከተማ በመኪና አደጋ ይሞትና አስክሬኑ መምጣቱ ሲሰማ፣ ሀዋሳ ላይ የህዝቡ ጩኸት ከዳር እስከዳር ቀውጢ ሆነ...
...የአማረ ሆቴል ባለቤት “አንተ አቡሽ ምንድነው ጩኸቱ?” ብለው አንዱን ልጅ ጠየቁት።
ልጁም “ሰማኒያ ሸሌ በመኪና አደጋ ሞተ” አላቸው፡፡
"እንዴ አንድ መኪና ውስጥ ይሄ ሁሉ ሸሌ በአንዴ? ከካቻማሊ የበለጠ ከ60 ሰው በላይ የሚጭን መኪና አለ እንዴ? እንዴት በአንድ ጊዜ ሰማኒያ ሴቶች ይሞታሉ” ብለው እንደነበር በለቅሶው ሰሞን ሰምቻለሁ።
አንዱ ደግሞ "ሰማኒያ ሸሌ ሞተ!" ሲባል ምን አለ?
“የሀዋሳ ወንድ ጦሙን አደረ በለኛ!”
የሚገርምሽ ፋይናንስ ሀላፊ ተሳደብክ ተብዬ ከመንግስት መስሪያ ቤት ተገፍትሬ ወጥቻለሁ፡፡ የአያቴን ስም በመናገሬ ነው ተገፍትሬ የወጣሁት፡፡ የአያቴን ስም ስትጠይቀኝ ኮስተር ብዬ “ሸሌ” አልኳት፡፡ “እንዴት ሸሌ ትለኛለህ” ብላ ጮኸች፤ ተገፍትሬ ወጣሁ፡፡ ከዚያም በስንት መከራ ነው መታወቂያ አሳይቼ ያመኑኝ፡፡
ታሪኩ ሰማንያ ሸሌ በአሁኑ ወቅት ኑሮውን በሰሜን አሜሪካ አድርጎ የኮሜዲ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።