የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ሊካሄድ ነው!
#FastMereja I የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 እና 15 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኃይሌ ግራንድ ሆቴል እንደሚያካሂድ በዛሬው ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል።
የዘንድሮው የአመታዊ የህክምና ኮንፈረንስ “በኢትዮጵያ የሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ደህንነት አሁናዊ ሁኔታና አማራጭ መፍትሄዎች" በሚል መሪ ቃል የሚከበር ሲሆን በኮንፈረንሱ ሐኪሞች ብቻ ሳይሆኑ እንደአጠቃላይ የጤና ባለሙያው እያጋጠመው ያለውን ማህበራዊ ጫና እና ይህ የሚያስከትለውን ሀገራዊ ቀውስ በሃገራችን ከሚገኙ እውቅ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ምክክር እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር 61ኛው ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከ400 በላይ የተከበሩ የህክምና ባለሙያዎችን እና ከውሳኔ ሰጪዎች በተጨማሪ ከሁሉም ክልል የሚመጡ የማህበሩ አባላት ተወካዮች፤ ከተለያዩ የጤና ባለሙያዎች ማህበራት የተውጣጡ ተወካዮች የህክምና ኮሌጅ ኃላፊዎች እና የመንግስት አካላት ጨምሮ የሚያሳትፍ ጉባዔ ሲሆን ዓለም አቀፍ የጤና አዉደርእዩ ከ70 በላይ ድርጅቶች የሚሳተፉበት እንዲህ ከ12,000 በላይ ሰዎችም ይጎበኙታል ተብሎ ይጠበቃል።
በዚህ መድረክ ላይ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ እውቅ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እና በየዓመቱ ተጠባቂው የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የሽልማት መርሃግብር ይካሄዳል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ከተመሰረተ 1940ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፤ በታካሚዎች ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ ቁልፍ ሚና በመጫወት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ ማህበር ነው።