የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አደረገ
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ውስጥ በአዲስ አበባ እና በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች የደረሱ የ103 የእሳት ቃጠሎ መንስኤዎችን በፎረንሲክ ምርመራ አጣርቶ ውጤቱን ይፋ አድርጓል ።
በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ ምርመራ ዲፓርትመንት በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ዘመኑ ያፈራቸውን ዘመናዊ የላብራቶሪ መሣሪያዎችን በመጠቀም ከሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች የቀረቡለትን የእሳት አደጋ ቃጠሎ መንስኤዎችን በማጣራት የደረሰበትን የፎረንሲክ ምርመራ ውጤት እንደሚከተለው አቅርቧል።
1. በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር ምክንያት የደረሰ 50 ቃጠሎ፤
2. በመካኒካል ችግር ምክንያት የደረሰ 11 ቃጠሎ፤
3. ሆን ተብሎ በሰው አማካኝነት የደረሰ 10 ቃጠሎ፣
4. በቸልተኝነት የደረሰ 17 እና
5. በሌሎች ምክንያቶች የደረሰ 15 ቃጠሎ መሆናቸውን አረጋግጧል።
ባለፉት ስድስት ወራት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ 96 እና በክልሎች ደግሞ ሰባት በአጠቃላይ እንደ ሀገር 103 የእሳት ቃጠሎ አደጋዎች ደርሰው የአደጋ መንስኤዎችን ማጣራቱን ጨምሮ ገልጿል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጥቅምት 11 ቀን 2017 ዓ.ም ምሽት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ሸማ ተራ ነባር የገበያ ማዕከልና በአካባቢው የደረሰው የእሳት አደጋ መንስኤም በኤሌክትሪክ ቴክኒክ ችግር የተከሰተ አደጋ መሆኑን በፎረንሲክ ምርመራ ማጣራት ችያለሁ ብሏል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ።
በግማሽ ዓመቱ በ582 መኖሪያ ቤት፣ በ12 ተሽከርካሪዎች፣ በ1965 ንግድ ቤቶች፣ በስድስት ፋብሪካዎችና የተለያዩ ድርጅቶች በቃጠሎ ምክንያት ጉዳት ስለመድረሱ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የስድስት ወር ሪፖርት አመላክቷል።
ኅብረተሰቡ ቃጠሎ ከደረሰ በኋላ ማስረጃዎች ሳይነካኩ መጠበቅና ለፖሊስ ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት እንዲሁም የቃጠሎ መንስኤዎች በሙያዊ ምርመራ እስካልተረጋገጡ ድረስ አስተያየት መስጠትና መፈረጅ ፍትሕን እንደሚያዛባ ተገንዝቦ ለፍትሕ መረጋገጥ የዜግነት ኃላፊነቱን እንዲወጣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን ያቀርባል።