የኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ ወር ጀምሮ የፍጆታና የአገልግሎት ታሪፍ ጭማሪ ሊያደርግ ነው
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ የፍጆታ የአገልግሎት ታሪፍ ተመን ጭማሪ ሊያደርግ መሆኑ ታወቀ፡፡
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከሚያዝያ እስከ ሰኔ ወር ድረስ በመኖሪያ ቤት ታሪፍ ላይ 0.50 ኪሎ ዋት ሰዓት የሚጠቀሙ ደንበኞች የፍጆታ ታሪፍ 0.60 ሳንቲም እንዲከፍሉ የሚደረግ ሲሆን፣ የአገልግሎት ክፍያ ተመንን በተመለከተ ለድኅረ ክፍያ አሥር ብር ከ95 ሳንቲም ሲከፍሉ፣ ለቅድመ ክፍያ አራት ብር ከ18 ሳንቲም እንደሚከፍሉ ሪፖርተር ያገኘው ሰነድ ያሳያል፡፡
የመኖሪያ ቤት ታሪፍን በተመለከተ ከ51 እስከ 100 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች አንድ ብር ከ49 ሳንቲም፣ ከ101 እስከ 200 ኪሎ ዋት ሁለት ብር ከ67 ሳንቲም፣ ከ201 እስከ 300 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ ደንበኞች ሦስት ብር ከ84 ሳንቲም እንደሚከፍሉና በየኪሎ ዋቱ መጠን ክፍያው የሚለያይ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል፡፡
የአገልግሎት ክፍያ ተመንም እንደ ኪሎ ዋቱ የሚለያይ እንደሆነና ለድኅረ ክፍያ ከፍተኛው 45 ብር ከ80 ሳንቲም ሲሆን፣ ለቅድመ ክፍያ 15 ብር 97 ሳንቲም እንደሆነ በነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን የወጣው ሰነድ ይጠቁማል፡፡
የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን የኢነርጂ አቅርቦት ሥርጭት ሬጉሌሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ባህሩ ኦሊጅራ እንደገለጹት፣ በየሦስት ወራት በፍጆታና በአገልግሎት ታሪፍ ላይ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ ጭማሪ ይደረጋል፡፡
የመኖሪያ ቤት፣ የንግድ፣ የአነስተኛ ኢንዱስትሪ፣ የመካከለኛ ኢንዱስትሪዎችና የመንገድ መብራቶች ላይ እንደ ኪሎ ዋቱ ልዩነት ጭማሪ የሚደረግ መሆኑን አክለው ገልጸዋል፡፡
ከጥር እስከ መጪው መጋቢት ወር ድረስ 0.50 ኪሎ ዋት የሚጠቀሙ የመኖሪያ ቤት ደንበኞች 0.52 ሳንቲም እንዲከፍሉ የተደረገ ሲሆን፣ የአገልግሎት ክፍያ ተመን ለድኅረ ክፍያ ደግሞ 10 ብር 71 ሳንቲም እንዲከፍሉ ሲደረግ፣ ለቅድመ ክፍያ ደግሞ 4 ብር 01 ሳንቲም እንዲከፍሉ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በተመሳሳይ የንግድ፣ የአነስተኛ ኢንዱስትሪ፣ የመካከለኛ ኢንዱስትሪዎችና የመንገድ መብራቶች በተቀመጠላቸው አኃዝ መሠረት እንዲከፍሉ እየተደረገ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡
በተለይ ማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጠር በየሦስት ወራት የፍጆታና የአገልግሎት ታሪፍ ተመን ጭማሪ እንዲደረግ ውሳኔ መተላለፉን፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮሙዩኑኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ታዬ ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡
የኃይል ማመንጫ ዋጋ በመጨመሩ ብቻ የተጨመረው ታሪፍ (Cost Reflection Tariff) በአንድ ኪሎ ዋት ሰዓት ከአራት ዓመታት በኋላ 6.01 ብር እንደሚሆን ከዚህ በፊት መዘገባችን አይዘነጋም፡፡
ዘገባው የሪፖርተር ነው።