ፍቅርን ❤️ በፍቅር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


♥♥💚💚💚♥♥♥💙💙💙♥♥
ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን
ይህ Channel የናንተ Channel ነው!! ስለ ፍቅር የምናውቅበት ቤታችን ነው።


ፍቅርን በተመለከተ post እንድደረግ የምትፈልጉ እና ሀሳብ አስተያየት 👉 @photopicBot ላኩልን
for Promotion @Promoandcomment_bot

♥ይቀላቀሉን♥

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


❤️‍🔥#ትሂድ🚶‍♀🚶‍♀

እንዲያው ጥላ መሄድ የሚወዳትን ሰው
የልቧን ፍላጎት ሙሉ ካደረገው😏
አልከለክላትም ትሂድ ትነሳና
ይበጀኛል ብላ ባየችው ጎዳና
ከእኔ ጋር መሆኑ እሬት ከሆነባት😟
የሰጠኋት ፍቅር ሰላሟን ከነሳት
እንግዲያውስ ትሂድ አልከለክላትም❤️‍🔥
ውደጂኝም ብዬ አላስገድዳትም💔
ልቧም ተጓዥ ካላት ብረሪ ክነፊ
ሂጂ ነው የምላት ካሻሽ ዘንድ እረፊ☹️
መንገደኛው ልቧ ለመሄድ የቃጣው
ታግዬ አላስቀረው ከመንገዱ አልገታው
ስለዚህ ትገስግስ መንገዱን ካሰበች💔
እኔም 'ሸኛታለው ድካሙን ሳልሰለች😖



      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


​​​​​​​​❤️‍🔥°••በዝናብ ቅጠሪኝ••°❤️‍🔥

አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ😔
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ😥

ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ😕

ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ😔

ውዴ፦❤️
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ💔
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ🥺

ሳለቅስ እንዳታዪኝ😟
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።❤️‍🔥

      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


💔#አታፍቅሪኝ❣️
      
❣️❣️
😔😔
ተኝቸም ቁጭ ብየም በቁሜም ሳስብሽ፤
#ለእኔ የሚሆን #ቦታ ባይኖርም #በልብሽ ፤
ወረተኛ ሁነሽ ለፍቅር #ባትሞች፤
ባክሽ #እኔ ላፍቅር #አታፍቅሪኝ አንቺ🤕
መለየት አቅቶኝ ቀን መሽቶ መንጋቱን፤
አንገቴን ደፍቼ ስገፋ ጊዜያቱን፤
#በሳቅ በጨዋታ ሰፈሩ #ሲቦርቅ፤
ፍቅርሽ ፍቅሬን #ሰብሮት ከህል ውሃሽ #ስርቅ፤💔
ሊያጽናናኝ የሚያስብ ባገር ቢሞላም ሰው፤
የፍቅርሽን ስቃይ ብቻየን #ልቅመሰው😢
#የሚያስተሳስረን ያ ቀን እስኪመጣ፤
#አንች ሰላም #ሁኝ እኔ ሰላም #ልጣ!🥺
እስከማገኝሽ ድረስ ከእንግዲህ አቻየን
ባክሽ አታፍቅሪኝ #ላፍቅርሽ ብቻየን😞💔

      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


💔💔💔
አፈቅርሻለውኝ❤
ካጣውሽ ሞታለው
የሚል አንድ አካል
እንዴት ለአፍቃሪው?
ሚሆን ጊዜን ያጣል??🥺


      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


🌎 💔

በውሸት ተከባ በታጠረች አለም
#መታመን ነው እንጂ #መካድ ብርቅ አይደለም‼️

#ለራሳችን_እንታመን።
በዚኛዉ አለም ጥቅም ባይኖረዉም
ለላይኛዉ ስንቅ ይሆነናል እና🙏

          ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


✍....
❤️‍🔥 ❤️‍🔥 ❤️‍🔥

ጦሴን ይዛው ትሂድ፤ ለኔ አላላትም❤️‍🔥
ብትጠራኝ እንኳን፤ አልከተላትም😏
ረስቻታለሁ፤ ከፈለገች ትጥፋ😤
ሌላ ቆንጆ ሞልቷል፤ ቅንጣት አልከፋ☹️        .
.
             . 
.
   እልና ሰዎች ፊት😎
እንባዬ ይወርዳል በጨለማ ለሊት🥺😥


            ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


(◍•ᴗ•◍)❤(◍•ᴗ•◍)❤

ሁሌም ልብህ ንጹህ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ሰውን አንዴ ከፈጠረ እንዴት አድርጎ እንደሚያኖር ራሱ ያውቃል የሰው ልጅ ብዙ ስለሮጠ ስኬታማ አይሆንም መስራት መሮጥ መጥፎ ነው እያልኩ አይደለም ግን አንድ አንድ ሰዎች አለን አይደል በመሮጥ ብቻ ስኬት የሚገኝ መስሎን የሰውን ሃቅ ጭምር በእጃችን ለማስገባት ቀን በእግር ማታ በሃሳብ እየሮጥን ውለን የምናድር!
ብዙዎች አለን አይደል ለገንዘብ ብለን ጓደኛን የምንክድ💔💔
ብዙዎች አለን  አይደል ለራሳችን ስኬት ብለን ቤተሰቦቻችን ሲቸገሩ አይተን ዝም የምንለው😢😢
ዛሬ ብር መሰብሰብ ብቻ ሀብታም አያደርግህም ምን አይነት ንግግር ነው ብር ከተሰበሰበ እንዴት ሀብት አይሆንም ልትሉኝ ትችላላችሁ ግን እውነታው ብር ስለሰበሰብክ ብቻ ሀብታም መሆን አትችልም!
ሀብታም መሆን የምትችለው የምትሰበስበው ብር ላይ ምንም እንከን የማይደርስ ከሆነ ነው እንከን የሚደርስ ከሆነ አንተ ዝም ብለህ ትሮጣለህ አንተ ለብዙ አመታት ሮጠህ ያጠራቀምከው ሁሉ በአንድ አጋጣሚ ተበትኖ ታያለህ ለዚህ ነው መሮጥ ብቻ ስኬታማ አያደርግም ያልኩት
ስኬታማ መሆን የምትችለው
በቅንነት
በታማኝነት
በእምነት መሮጥ ስትችል ነው።

•ቅንነት ሲኖርህ ለሌሎች መልካም ነገር ማድረግ ትጀምራለህ ለሌሎች መልካም ነገር እያደርክ ነው ማለት ደሞ ለፈጣሪ ብድር እየሰጠህ ነው እንደማለት ነው ስለዚህ ፈጣሪ ለአንተም ይሰጣል ማለት ነው

• ታማኝነት ሲኖርህ አንተ ለሌላ ሰዎች ታማኝ እንደሆንክ ሁሉ ፈጣሪ ደሞ ለአንተ ታማኝ ይሆናል ማለት ነው

• እምነት ሲኖርህ በፈጣሪ በሙሉ ልብ ማመን ትጀምራለህ በሙሉ ልብህ ፈጣሪን ማመን የምትችል ከሆነ ደሞ ፈጣሪ በእሱ የሚያምኑትን መቼም ቢሆን አይጥልም ማለት ነው
ስለዚህ የስኬት ቁልፍ መሮጥ መስራት ብቻ ሳይሆን ከስራ እና ከሩጫ ጋር ቅንነት ታማኝነት እና እምነት ጭምር ይዞ መሮጥ እና መስራት ነው።


            ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143


✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን አደረሳችሁ !!

EID MUBARAK 🌙

            ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


ዛፍ ላይ የተቀመጠች ወፍ🦆 እምነቷ በዛፉ ሳይሆን በክንፏ ነው። ዛፉ ቢሰበርም በክንፏ መትረፍ ትችላለች።🦅 አንተም እምነትህን በራስህ ላይ አድርግ ያመንከው ቢሸሽህ መቆም እንደምትችል አሳያቸው።
                  #መልካም_ምሽት_ምርጦቼ


      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺


ፍቅረኛ ለመያዝ እና ግንኙነትን ለማራመድ ዋና ዋና የሆኑ ነገሮች፡-

1. ክትትል እና ቅን ውይይት (Communication)
➴ ሀሳብ፣ ስሜት፣ እና ፍላጎቶችን በነጻነት ማካፈል።
➷ ቅጣት ሳይሰማችሁ የሌላውን አቋም መረዳት።

2. መተማመን (Trust)
➴ ቃል ለመስጠት እና ድርድሮችን መጠበቅ።
➴ ጥርጣሬ ሳይፈጠር የጋራ ስሜት ማሳደግ።

3. አክብሮት (Respect)
➴ የእርስዎን ልዩነቶች፣ ወሰኖች፣ እና ምርጫዎች መከበር።
➴ በቃል ወይም በተግባር አድናቆት ሳይቀር መተሳሰብ።

4. ርህራሄ እና መረዳት (Empathy)
➴ ከጎን ቆሞ ስሜታቸውን መለየት እና መደገፍ።
➴ ችግሮች ሲከሰቱ በሰላማዊ መንገድ መፍታት።

5. የጋራ ጊዜ (Quality Time)
➴ ትኩረት የሚሰጥ ጊዜ ማሳለፍ (ምሳሌ፦ ጉዞ፣ መጫወት)።
➴ የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በጋራ መስራት።

6. አመስጋኝነት (Gratitude)
➴ ትንሽ ነገሮችን እንኳ በቃል ወይም በተግባር መገለጽ።
➴ "አመሰግናለሁ" ማለት ስሜትን ያጠነክራል።

7. ትዕግስት እና ምህረት (Patience & Forgiveness)
➴ ስህተቶች ሲደረጉ በጥሩ ልቦና መቀበል።
➴ ትዕግስት ማዳበር ለረዥም ጊዜ ግንኙነት ያስፈልጋል።

8. የጋራ አላማዎች (Shared Goals)
➴ ስለ ወደፊት ዕቅዶች (እንደ ቤተሰብ፣ ሥራ፣ የገንዘብ እቅድ) በጋራ መወያየት።
➴ የተለያዩ ሀሳቦችን በሰላማዊነት መስማማት።

9. ግለሰባዊ ቦታ (Personal Space)
➴ እያንዳንዱ አጋር የራሱን የባህርይ፣ የዝንባሌ፣ እና ጊዜ መጠበቅ።

10. አካላዊ እና ስሜታዊ ቅርበት (Intimacy)
➴ ስሜትን የሚያሳዩ ትንሽ ተግባራት (ምሳሌ፦ መያዝ፣ መስማማት)።
➴ ለሌላው ስሜት ትኩረት መስጠት።

11. መማር እና መለወጥ (Growth)
➴ እርስ በርስ መተባበር እና ከስህተቶች መማር።
➴ የሕይወት �ውጦችን በጋራ መቋቋም።

ማስታወሻ፦ ፍቅር ማለት ቀን በቀን ሥራ ነው። በትዕግስት፣ ትህትና፣ እና አለማቋረጥ ልምምድ ይበልጥ ዘላቂ ይሆናል።


      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


(◍•ᴗ•◍)❤(◍•ᴗ•◍)❤

😘(አለመኖር )#️⃣

"አዎ መሸነፍ ነዉ።
ፍቅር መሸነፍ ነዉ።
ፍቅር መያዝ ነዉ።
ፍቅር ለስሜት ተገዢ መሆን ማለት ነዉ።
ፍቅር ከምክንያት ዉጪ ሆኖ መኖርን መቀበል ነዉ።
ፍቅር ከራስ ቁጥጥር ዉጪ መሆን ነዉ። ስለዚህ አዎ መሸነፍ ነዉ።

ያስፈራል ፍቅር፣የማይታከሙት ህመም፣
የማይጠገን ቁስል ፣
የማያባራ እንባ እና ሰቆቃ ሊሆን ይችላል ።"

"የሚያስፈራው ያፈቀርሽዉ ሰዉ ሳይሆን፤ ማፍቀር ራሱ ነዉ ካፈቀርሽ በኋላ 'እኔ' ምትይዉ ሁሉ ይጠፋል ለራስሽ ትርፍ ትሆኛለሽ። በፈቃደኝነት ከራስሽ ምታስቀድሚዉ እና ምታስበልጪዉ ሌላ ሰዉ ይኖራል ማለት ነዉ።"

"ፍቅር ያለ ዉጊያ መማረክ ነዉ ፤ እጅ መስጠት፤ ወዶ መግባት፤ ከራስ መነጠል ፣መጥፋት በማያዉቁት አለም ዉስጥ ገብቶ መሰደድ ፤ አያስፈራም አትበይኝ ያስፈራል።



         ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


by the way ገና is not about ur Red dress💃, Green tree🎄 or ዶሮ ወጥ🐓, but about የትልቅነት ልክ የሆነው ኢየሱስ ሊያድነን በበረት መገኘቱ! 🤷‍♂️
መልካም የክርስቶስ ልደት 🤩🙏


ለኔ ካለህ ❤️
የትም አትሄድም🚶
ውደደኝ ብዬ ሙጥኝ አልልም😭💔💔


         ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


😔😔 #መልስህን ንገረኝ 😔😔

ድሮስ የወደደውን መች ሰው ይፈልጋል
የማይፈልገውን ሄዶ ይለምናል።

እኔም ከነዛ ውስጥ አንዷ ነሽ ብለዋል
አንተ የኔ እንደሆንክ ማን በቅጡ ያቃል።

እኔ ስፈልግህ አንተስ እርቀሀል
እንዴት የኔ ላርግህ ሌላ ሰው ይዘሀል።

የኔን ልብ ስሰጥህ መች አንተ ይገባሀል
ለኔ ያለህን ስሜት ማወቅ ተስኖኛል።

እኔ አንተን ስፈልግ አንተ ስትል ሌላ
የኔ ልብ በስቃይ በሀዘን ተሞላ።

አሁን የማሳይህ ላይገባህ ይችላል
ስታቀው ሲገባህ እግርህ ይመልስሀል።

ተስፋ እንዳትቆርጥ ልቤ ይቀበልሀል
ጥላቻንም ገፍቶ ፍቅርን ያለብስሀል።

በርግጥ አልዋሽህም ልቤ ይፈልግሀል
በአፍ ባልነግርህም አይኔ አሳይቶሀል።

አልገባኝም ማለት አውቃለው እንደምችል
ግን ጥቅም የለውም አይገባኝም ብትል።

አውቃለው እንደሌለህ የኔ እምትላት
እኔ እኮ የለኝም የቅናት ስሜት።

ለኔ ያለህን ስሜት ንገረኝ እባክህ
ልሂድልህ በቃ ሙሉ ከሆነ ልብህ።

ልቤ መውደድ ይበቃሀል
ለእሱ እኔ አለሁ ለኔ ማን ያስብልብኛል።

የሰማዩ ጌታ የኔ ሁን ካላለው
ለኔ የፃፈውን እስኪ ልፈልገው።

ካንተ ጋር መሆኑን ልቤ ይመኘዋል
ያላንተ መኖሩን እንዴት ይችለዋል።

አንድ ቀን አስበህው ይገባህ ይሆናል
የሰው ልብ እንዲ ነው በተራው ይመጣል።

ፈላጊ ነኝ እንጂ ማን ይፈልገኛል
የሚፈልገኝስ መቼ ፍቅር ያውቃል
እስኪጠግበኝ ብቻ ከጎኔ ይቆያል።

😔😔

••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
                  @fkrbefkr143      
                  @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


🤩 ለፈገግታ 😍👇👇👇

#ተቀበል 
ትዳር ተወደደ አወጣ ሚሊዮን የኔ አይነቱን ደሀ ምን ይውጠው ይሆን

ጀለስ፦ ድሀ እንደሆንክማ ስምህ ያሳብቃል አባትህ ቢጨንቀው #ተስፍዬ ብሎሃል
😂😂😂😂😂


🗒የ ማስታወቂያ ሰዓት 👇👇👇


ከቁስልህ ለመዳን ከፈለክ ቁስልህን መንካት ተዉ!! ደና ትሆናለዉ።


      ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
    @fkrbefkr143      
    @fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


😍ጠብቄሽ ነበረ😁

የቆሸሸ ትሪ ድስት እና መክተፊያ ሰብስቤ አስቀምጬ በአንድመዘፍዘፊያ

ጠብቄሽ ነበረ ...

መምጣትሽን አምኜ
በናፍቆት ዉስጥ ሆኜ
የቆሸሸ ልብሴን ደጅ ላይ ቆልዬ
ሳሙና ገዝቼ ተስፋን አንጠልጥዬ
እጄን ጎሮሮዬን በአልኮል ወልዉዬ

ጠብቄሽ ነበረ...

ጥም እያቃጠለኝ ደርሶ እንደበረሀ
ወይ አልገዛሽ ነገር መሆኔን እያወቅሽ የናጠጠ ደሀ

ጠብቄሽ ነበረ...

ደረቅ ቧንቧ እያየሁ፡ አዘንኩብሽ ዉሀ😂😂

#JUST_🤣🤣

    ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
    @fkrbefkr143   
@fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺  


እንባ እንባ ይለኛል
ይተናነቀኛል
እንባ ግን የታባቱ
ደርቇል ከረጡቱ

ሳቅ ሳቅም ይለኛል
ስቆ ሳይስቅ ጥርሴ
ስቃ እየነደደች
መከረኛ ነፍሴ
✍✍✍

     ••●◉Join us share

      💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
    @fkrbefkr143   
@fkrbefkr143

✽‌»‌🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽‌»‌🌺   


🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻   
                         እንኳን
              ለ2017 አመተ ምህረት
              በጌታ ምህረትና ጥበቃ
                        በሰላም
                      አደረሳችሁ                   

🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.