❤️🔥°••በዝናብ ቅጠሪኝ••°❤️🔥
አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ😔
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ😥
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ😕
ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ😔
ውዴ፦❤️
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ💔
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ🥺
ሳለቅስ እንዳታዪኝ😟
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።❤️🔥
••●◉Join us share
💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@fkrbefkr143
@fkrbefkr143
✽»🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽»🌺
አማልዱኝ ባልልም አስታራቂ ልኬ
ባልማፀንሽም ፊትሽ ተንበርክኬ😔
ዕንባዬ እንዳይታይ ካንቺ ተደብቄ
አነባለሁ ዛሬም ዝናቡን ጠብቄ😥
ልቤ በስቃይ ጣር ብሶቱን ሲያሰማ
ሀዘኔ ተሰምቶሽ ልብሽ እንዳይደማ
ቀኑ ጨላልሞልኝ ክረምቱ እስኪገባ
መጥተሽ አትጠይቂኝ ሆድሽም አይባባ😕
ዝናብ የኔን ብሶት ሀዘኔን ባያጥበው
ሳለቅስ እንዳታዪ ዕንባዬን ይጋርደው
በጉንጬ 'ሚፈሰው ዝናብ እንዲመስልሽ
ሁሌ ክረምት ይሁን ጉዳቴ አይታይሽ😔
ውዴ፦❤️
ጥፋቴ ሲገባኝ ዛሬ ተመልሼ
ነይልኝ አልልም እፊትሽ አልቅሼ💔
አዲሱ ኑሮሽን ልረብሽ በ'ንባዬ
በበጋ አልጣራም 'ናፍቀሽኛል' ብዬ🥺
ሳለቅስ እንዳታዪኝ😟
ሁሌ በያመቱ በክረምት ነዪልኝ
የናፈ'ኩሽ እንደሁ
ጉርምርምታው ሲብስ በክረምት ጠይቂኝ
አንቺን ያገኘሁ 'ለት
ከንፈሬ ተላቆ ስስቅ እንድታዪኝ
ቀን የጨለመ 'ለት
ዶፍ እየወረደ ዝናብ ውስጥ ጠብቂኝ።❤️🔥
••●◉Join us share
💌 ይከታተሉን | Follow us፡ 💌
@fkrbefkr143
@fkrbefkr143
✽»🌺 ━━━━━━━✦✿✦━━━━━ ✽»🌺