ጥራዝ ነጠቆቹ
(ፉአድ ሙና)
.
ዛሬ ስለፍቅር ጋብ አድርገን ስለ ጥላቻ ብናወራስ? ስለነዚያ ቢችሉ የጀነትን በር ይዘው ሌላ ሰው እንዳይገባ ለማድረግ ስለሚሹት ሠዎች እንወያይ! ደግሞ የሆነ አራት ኪታብ ቀርተዋል። በእነሱ አለም በራስ ጭንቅላት ማሰብ ነውር ነው። በኡስታዛቸው ጭንቅላት ይነዳሉ።
ከተግባርህም ሆነ ከንግግርህ ውስጥ በጉጉት የሚጠብቁት ወደ ስህተት ሊተረጎም የሚችል ነገርን ነው። ስህተት መሆን አይጠበቅበትም። ከመሰለ ይበቃቸዋል። «አላህን ፍራ!» በሚል ተቀፅላ ጀምረው የስድብ ጥማታቸውን ያስታግሱብሀል።
እነዚህ ሰዎች ለመምሰል እንደሚሞክሩት ብፁዕም አይደሉም። በወንጀል እጅጉን ሊበልጡህ ይችላሉ። በማስመሰል ህይወታቸውን ይመራሉ የምቀኝነትና የቅናት ድግሪ አላቸው። የእነሱ የእስልምና ትርጓሜ ሰውንም ሆነ ራስን ማስጨነቅ ነው።
እነዚህ ሰዎች ገጥመዋችሁ አያውቁም? እስኪ የገጠማችሁን አካፍሉን!
ባልተያያዘ ዜና የውሀ ጉድጓድ ለማስቆፈር ገንዘብ እየተሰበሰበ ነው። ለመሳተፍ የምትፈልጉ @Fuadmuna ላይ አካውንት ጠይቁኝ።
.
@Fuadmu