በሞዛምቢክ ቺዶ በተሰኘው አውሎ ንፋስ የሟቾች ቁጥር 73 ደረሰ
በሞዛምቢክ ውስጥ በቺዶ አውሎ ንፋስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 73 መድረሱን የአደጋ አስተዳደር ባለስልጣናትማ አስታውቀዋል።
የሀገሪቱ ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አስተዳደር ኢንስቲትዩት ሊቀ መንበር ሉዊዛ ሜኬ በሰጡት መግለጫ “አውሎ ነፋሱ በደቡብ አፍሪካ ሀገራት ላይ ያደረሰውን ጉዳት መጠን የሚገመግምው ሂደት ቢቀጥልም ተጨማሪ ስራዎች እየተለዩ ይገኛል። በአውሎ ነፋሱ ምክንያት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር በትክክል ማወቅ አንችልም በየእለቱ የተጎጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ግን መናገር እንችላለን ብለዋል።
ሁኔታው በጣም አስፈሪ እና አስጨናቂ ነው። ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር ለማወቅ ብዙ ድጋፍ እንፈልጋለን ፣ ካልሆነ ግን አስከሬን ለማግኘት በጣም ከባድ እየሆነብን ነው ፣ ምክንያቱም አንዳንዶቹ ህንጻዎች በላያቸው ላይ ከወደቁ በኋላ በጥልቅ የተቀበሩ ናቸው ብለዋል ።አውሎ ነፋሱ እየተረጋጋ በሄደ ቁጥር የጉዳቱን መጠን ስንገመግም የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ የሚችልበት እድል አለ ሲሉ ሜኬ አክለዋል።
2.5 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በአውሎ ነፋሱ ተጎድተዋል ተብሏል። የሞዛምቢክ የህፃናት አፍን ድርጅት የዩኒሴፍ ተወካይ ሉዊዝ ኢግልተን እንዳሉት 90 ሺ የሚያህሉ ህጻናት በአውሎ ነፋሱ “የከፋ ጉዳት” ደርሶባቸዋል። “በተጎጂው ማህበረሰብ ውስጥ ከሞላ ጎደል የተጎዱ ህጻናት ቁጥር እየጨመረ ነው። እነዚህ ልጆች ስንቅ እና መጠለያ ለማግኘት እየታገሉ ያሉ ናቸው። ልጆች የአውሎ ነፋሱን ጫና እየተሸከሙ ይገኛል።
አሁን በሀገሪቱ ያለው ሁኔታ ልብን የሚሰብር ነው ሲሉ ኢግልተን ተናግረዋል። እሮብ እለት የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ለአውሎ ነፋሱ የአደጋ ጊዜ ምላሽ 4 ሚሊዮን ዶላር ሰጥቷል። በአጎራባች ሀገር ማላዊ የሀገሪቱ የአደጋ እና አስተዳደር ጉዳዮች ዲፓርትመንት እንደገለፀው የሟቾች ቁጥር 13 የደረሰ ሲሆን በደቡብ ማላዊ ክልል ውስጥ በሚገኙ አምስት ወረዳዎች 45,000 ሰዎች ቤት አልባ ሆነዋል። ባለፈው ሳምንት ቺዶ አውሎ ንፋስ ሞዛምቢክ ውስጥ ኃይለኛ ንፋስ ፣ ነጎድጓድ እና ከባድ ዝናብ አስከትሏክ። 24 ሰዓታት ውስጥ ከ250 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ የጣለ ሲሆን ከዚያም አውሎ ነፋሱ ወደ ማላዊ ተሻግሯል።