ቃልህ
*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*
የእረፍቴ ስፍራ፣ማግኛ ነው ሰላሜ
ዘውትር እያጠጣኝ፣ሚያኖር በልምላሜ
የህይወት እንጀራ፣ከድካም ማገገምያ
በልቤ የፃፍከው፣የህይወት መመርያ
መታመኛ ጋሻ፣ጠላት መመከቻ
ብሩህ መስታወት ነው፣ውስጥን መመልከቻ
መልህቅ ነው ለኑሮ፣በማዕበል ለሚርድ
ፍቱን መድሀኒት፣በልጦ የሚወደድ
ቃልህ
ነፍስን ማረጋግያ፣በማዕበሉ መሀል
ፃድቅ አሰላስሎት፣ከግቡ ይደርሳል
አይደል ሳለሳል፣እያመንኩት ስኖር
እጅግ ደስ ይለኛል፣በእጄ ይዤው ስዞር
ቃልህ
ስንቴ በረታሁበት፣ዳንኩበት ስንት ጊዜ
ነፍሴን ገላገላት፣ከሀጥያት አባዜ
ስንቅ ሆነኝ ለህይወት፣ብርሀን ለመንገዴ
ቃል አይገልጥልኝም፣ቃልህ ለመውደዴ
አንተን እንዳልበድል፣በልቤ ሰውሬ
በብሩቱ ወድጄው፣አለው እስከዛሬ
ውዴን ሚያወራልኝ፣የሆነኝ ወዳጄ
ቃሉ አላጣጥልም፣በፍፁም ለምጄ
ሁል ጊዜ ተወዳጅ፣ሁል ጊዜ ብርቅ ነው
ልቤ ሚለውን ነው፣ብዕሬ የሚፅፈው
ውዴ ሆይ ቃልህን እወደዋለው
✍ኤርሚያስ ክፍሌ
react 👍 🥰
@gitim_alem
*-*-*-*-*-*-*-*-*-*-*
የእረፍቴ ስፍራ፣ማግኛ ነው ሰላሜ
ዘውትር እያጠጣኝ፣ሚያኖር በልምላሜ
የህይወት እንጀራ፣ከድካም ማገገምያ
በልቤ የፃፍከው፣የህይወት መመርያ
መታመኛ ጋሻ፣ጠላት መመከቻ
ብሩህ መስታወት ነው፣ውስጥን መመልከቻ
መልህቅ ነው ለኑሮ፣በማዕበል ለሚርድ
ፍቱን መድሀኒት፣በልጦ የሚወደድ
ቃልህ
ነፍስን ማረጋግያ፣በማዕበሉ መሀል
ፃድቅ አሰላስሎት፣ከግቡ ይደርሳል
አይደል ሳለሳል፣እያመንኩት ስኖር
እጅግ ደስ ይለኛል፣በእጄ ይዤው ስዞር
ቃልህ
ስንቴ በረታሁበት፣ዳንኩበት ስንት ጊዜ
ነፍሴን ገላገላት፣ከሀጥያት አባዜ
ስንቅ ሆነኝ ለህይወት፣ብርሀን ለመንገዴ
ቃል አይገልጥልኝም፣ቃልህ ለመውደዴ
አንተን እንዳልበድል፣በልቤ ሰውሬ
በብሩቱ ወድጄው፣አለው እስከዛሬ
ውዴን ሚያወራልኝ፣የሆነኝ ወዳጄ
ቃሉ አላጣጥልም፣በፍፁም ለምጄ
ሁል ጊዜ ተወዳጅ፣ሁል ጊዜ ብርቅ ነው
ልቤ ሚለውን ነው፣ብዕሬ የሚፅፈው
ውዴ ሆይ ቃልህን እወደዋለው
✍ኤርሚያስ ክፍሌ
react 👍 🥰
@gitim_alem