የዓይኔ ማረፊያ
አሉኝ የሚላቸው እኔ በምድር ላይ
ገንዘብና ዝና ቢኖር ለሰው ሚታይ
እኔ ግን ትኩረቴን ልቤን የሚወስደው
የልጁ ፍቅር ነው ቀልቤን የማረከው
ኢየሱስ ትኩረቴ የዓይኔ ማረፊያ
ልቤ ላያሸልብ ከቶ ካ'ንተ ወድያ
አፍቅሬ ማልረካብህ የፍቅር ጥጌ ነህ
አንቴ ማለት ለኔ ከህይወትም በላይ ነህ
እውሩ እየጮሄ የዳዊት ልጅ ማረኝ
አለ እያነባ ዓይኖቼን አብራልኝ
አይኖቹ ተከፍቶ እነን የገረመኝ
ከዓይኖቹ መከፈት ይልቅ ያስደነቀኝ።
ዓይኖቹ ተከፍቶ ያ ምስክን እውሩ
ሊያያቸው ሚመኘው ብዙዎቹ ነበሩ
ግና....
ሊከተልህ አለው እነሱን ተወና
የዓይኑ ማረፊያው ኢየሱስ ነውና።
ለእነም እንዲሁ ነህ ዓይኖቼ ሲገለጥ
ቀድሜ የማይህ ከራሴ የሚትበልጥ
የእግዚአብሔር እንዲያ ውዱ ኢየሱሴ
ከእኔ አንተ እርቀህ አልችልም በራሴ
የምሬን ነው ሚልህ ኢየሱስ አባቴ
መኖርን አልችልም ተለይቼ ካ'ንተ
ለነፍሴ እንኳ ነፍሷ ነህና እራስህ
ለኔ ህይወት ማለት ጌታ አንተ ነህ
✍️አማኑኤል ነጋሽ(አቡ)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
አሉኝ የሚላቸው እኔ በምድር ላይ
ገንዘብና ዝና ቢኖር ለሰው ሚታይ
እኔ ግን ትኩረቴን ልቤን የሚወስደው
የልጁ ፍቅር ነው ቀልቤን የማረከው
ኢየሱስ ትኩረቴ የዓይኔ ማረፊያ
ልቤ ላያሸልብ ከቶ ካ'ንተ ወድያ
አፍቅሬ ማልረካብህ የፍቅር ጥጌ ነህ
አንቴ ማለት ለኔ ከህይወትም በላይ ነህ
እውሩ እየጮሄ የዳዊት ልጅ ማረኝ
አለ እያነባ ዓይኖቼን አብራልኝ
አይኖቹ ተከፍቶ እነን የገረመኝ
ከዓይኖቹ መከፈት ይልቅ ያስደነቀኝ።
ዓይኖቹ ተከፍቶ ያ ምስክን እውሩ
ሊያያቸው ሚመኘው ብዙዎቹ ነበሩ
ግና....
ሊከተልህ አለው እነሱን ተወና
የዓይኑ ማረፊያው ኢየሱስ ነውና።
ለእነም እንዲሁ ነህ ዓይኖቼ ሲገለጥ
ቀድሜ የማይህ ከራሴ የሚትበልጥ
የእግዚአብሔር እንዲያ ውዱ ኢየሱሴ
ከእኔ አንተ እርቀህ አልችልም በራሴ
የምሬን ነው ሚልህ ኢየሱስ አባቴ
መኖርን አልችልም ተለይቼ ካ'ንተ
ለነፍሴ እንኳ ነፍሷ ነህና እራስህ
ለኔ ህይወት ማለት ጌታ አንተ ነህ
✍️አማኑኤል ነጋሽ(አቡ)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8