"የገነትን በር"
ግልፅ ቃል ይዣለሁ ትርጉሙ አንድ ነው
ሰምቶ ላደመጠው አንዳች በር አለው
በሬ በሌለበት እህል እንደሌለው
ፍሬን አቀርባለሁ ግንዱ በሽታው ነው
ማወቅ መቅመስ ነው የህይወትን ሽታ
የገነትን በር ከመታገድ ስለቱም ቢበረታ
ያንገት ማቀርቀር ዝምታው በዋዛ
ቢቆልፍብንም በሲኦል ያለ ታዛ
በኢየሱስ ይገባል የያዘ ቁልፉን
ወደ ኋላ የማያይ ይዞ እርፉን
ይህች ናት ሕይወት ከሕይወት
ጨረር ተናክታ ከሞት ወደ እውነት
ነፍስ ትጠግባለች ከእውቀቱ ሰምታ
መንፈስ ትረጋለች ሰክና በፍቅሩ ሰላምታ
ፈጣሪ አይሆንም ገዳይ
ፍርድ በእጁ ለእኛ ጉዳይ
ሊያኖር ፈጥሮ በፈቃዱ
ሟችስ ሰው ነው ከመንገዱ
ሩጫ ሩጫ ትንግርት ተጠናውቶ
ተቀባይ ከሁሉ አይሰማ አጥርቶ
ተላላ አንደበት ቂልነትን እንዲያመነዥግ
ሁከት እና ጩኸት ጥልን እንዲያንዠረግግ
አለማወቅ አይሆንም ጽድቅ
መቀመጥ ኩራዝ ይዞ በድቅድቅ
ያለ ድሪም ለግዢ ሩጫ
ካለ ፍለጋ አይኖርም መውጫ
እንቅብ ስር ተቀብሮ ያለ አፈር
ከጨለማው ፅልመት መዳከር
ጋዝ ያለ እሳት እንደማይፈራ
ሰው ያለ አምላክ ምነኛ ለከንቱ ተገራ
መጣ ያለ የስንፍናው ክፍያ
እጅግ አብቅሎ ሊያሳጣው ማረፊያ
ብዙ ያሸልላል ያስቀረራል ቀረርቶ
ባዶ ነገርን ማጮህ ይመቻል አኩርቶ
አለማውቅን ሲያወሩት ቢገጥሙ
ማወቅን ቀበራ ነው ያለቀባሪው
ግን የመጣውን ደመና ያየ አርበኛ
በወንዙ መድረቅ እንቅልፉን ያልተኛ
ስጦታ መጣ ብሎ ቦይን የቀደደ
ውሃው ይጎበኘዋል እረፍቱን ለወደደ
ገጣሚ አሳፍ
@YE_KIDAN_KALI
#SHARE #SHARE
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
ግልፅ ቃል ይዣለሁ ትርጉሙ አንድ ነው
ሰምቶ ላደመጠው አንዳች በር አለው
በሬ በሌለበት እህል እንደሌለው
ፍሬን አቀርባለሁ ግንዱ በሽታው ነው
ማወቅ መቅመስ ነው የህይወትን ሽታ
የገነትን በር ከመታገድ ስለቱም ቢበረታ
ያንገት ማቀርቀር ዝምታው በዋዛ
ቢቆልፍብንም በሲኦል ያለ ታዛ
በኢየሱስ ይገባል የያዘ ቁልፉን
ወደ ኋላ የማያይ ይዞ እርፉን
ይህች ናት ሕይወት ከሕይወት
ጨረር ተናክታ ከሞት ወደ እውነት
ነፍስ ትጠግባለች ከእውቀቱ ሰምታ
መንፈስ ትረጋለች ሰክና በፍቅሩ ሰላምታ
ፈጣሪ አይሆንም ገዳይ
ፍርድ በእጁ ለእኛ ጉዳይ
ሊያኖር ፈጥሮ በፈቃዱ
ሟችስ ሰው ነው ከመንገዱ
ሩጫ ሩጫ ትንግርት ተጠናውቶ
ተቀባይ ከሁሉ አይሰማ አጥርቶ
ተላላ አንደበት ቂልነትን እንዲያመነዥግ
ሁከት እና ጩኸት ጥልን እንዲያንዠረግግ
አለማወቅ አይሆንም ጽድቅ
መቀመጥ ኩራዝ ይዞ በድቅድቅ
ያለ ድሪም ለግዢ ሩጫ
ካለ ፍለጋ አይኖርም መውጫ
እንቅብ ስር ተቀብሮ ያለ አፈር
ከጨለማው ፅልመት መዳከር
ጋዝ ያለ እሳት እንደማይፈራ
ሰው ያለ አምላክ ምነኛ ለከንቱ ተገራ
መጣ ያለ የስንፍናው ክፍያ
እጅግ አብቅሎ ሊያሳጣው ማረፊያ
ብዙ ያሸልላል ያስቀረራል ቀረርቶ
ባዶ ነገርን ማጮህ ይመቻል አኩርቶ
አለማውቅን ሲያወሩት ቢገጥሙ
ማወቅን ቀበራ ነው ያለቀባሪው
ግን የመጣውን ደመና ያየ አርበኛ
በወንዙ መድረቅ እንቅልፉን ያልተኛ
ስጦታ መጣ ብሎ ቦይን የቀደደ
ውሃው ይጎበኘዋል እረፍቱን ለወደደ
ገጣሚ አሳፍ
@YE_KIDAN_KALI
#SHARE #SHARE
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8