"ሴቶች በምንም አይማልሉም አትድከሙ!"
(አሌክስ አብርሃም)
በነገራችን ላይ እንደምታስቡት ሴት"መጀንጀን" ላይ አሪፍ አይደለሁም! ስለመጨረሻ ጅንጀናየ ላውጋችሁ! የሆነ ጊዜ አምስት መንገዶች አስር ማሳለጫዎች ምናምን የሚል የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ሴት ልጅ በራሱ የሚተማመን ወንዳወንድ ወንድ ትወዳለች የሚል ነገር ሰማሁ! እና አንዲት በዛ ሰሞን የወደድኳትን ልጅ ማማለል ፈለኩ! ተቀጣጥረን ተገናኘን ምሳ አብረን በላን (በድሮሮሮሮሮሮሮ ጊዜ የዛሬ ስድስት ዓመት ሰዎች ምሳ ይገባበዙ ነበር) እና ከመሬት ተነስቸ ጀብዱ ነገር ማውራት ጀመርኩ!
"ይገርምሻል የሆነ ጊዜ አንድ ዳይኖሰር የሚያክል በሬ ከቄራ አመለጠ ፤ እና ከቄራ ቡልጋሪያ ድረስ ሰባት ወንዶች ሶስት ሴቶች ሁለት መኪና በቀንዱ እየወጋ አተረማመሰው! ፖሊስ ሁሉ ማስቆም አልቻለም! እና እኔ ስደርስ ወደሆኑ አሮጊት ቀንዱን አሹሎ እየሮጠ ነበር ... በባልቴቷና በበሬው መካከል ሶስት የበሬ እርምጃ ሲቀር ተፈትልኬ ሮጥኩና መሀላቸው ገብቸ ስቆም ጫማየ እንደመኪና ጎማ ፉጭጭጭጭጭጭ አለ! በሬው ደንግጦ ቆመና ተፋጠን እንደቆምን በቀስታ ቀረብኩት .... በእግሩ አስፋልቱን እየቆፈረ ሊወጋኝ ሲሞክር ሸወድኩትና አንገቱ ላይ የታሰረውን ገመድ ቀጨም አድርጌ ለባለቤቱ አስረከብኩ! ይገርምሻል በተፈጥሮየ አልፈራም!
ልጅቱ ስትሰማኝ ቆየችና የበሬውን ነገር እንዳልሰማ ሰው " ዳይኖሰር ስትል አስታወስከኝ! ለምን ዛሬ ኤድናሞል ሙቪ አናይም? አሪፍ የዳይኖሰር ሙቪ አላቸው" ብላ በሚያማምሩ አይኖቿ አየችኝ! ጀብዱየን ውሃ ቸለሰችበት! ቅር እንዳለኝ ወደኤድናሞል የሚወስደን ታክሲ ስንጠብቅ አስገራሚ ነገር ተፈጠረ .... በሬ! የፈረጠጠ በሬ መንገዱን እያመሰው ከፊት ለፊታችን መጣ ... በእርግጥ ነፍሴን ለማትረፍ ባደረኩት ሩጫ ከበሬው የበለጠ ብዙ ሰው እየገፋሁ ሳልጥል አልቀረሁም! ልጅቱ ጋር በተፈጠረው ግር ግር እንደተጠፋፋን ከዛ በኋላ አልተገናኘንም! በእርግጥ ትዝ ያለችኝም የሆነ ካፌ ገብቸ ሁለት ሊትሩን ውሃ ከጠጣሁ በኋላ ነው!