HAppy Mûslimah


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


አጫጭር ኢስላማዊ ታሪኮች ብቻ
ONLY SHORT ISLAMIC STORY‼️
Fôr Any Cømments👉 @NihalllAb

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


ÄŠĒŁÄMÛ ÅĹËŸĶŰM WĖŘÊHMÊŤŮĻŁÁHÏ WĖBĒŘÊĶĀŤÛH

ቴሌግራም ገብተው ምንም አዲስ ነገር ለማግኘት ለመስማት ተቸግረዋል? ወይስ ፕሮፋይል ፎቶ ለመቀየር ተቸግረዋል?
እንግዲያውስ ኢሀው የፈለጉትን ቻናል ይዘን ቀርበናል

በማለት አባል ብቻ ይሁኑ


....ከጎናችን ባለው ሰው አይን ውስጥ ይሄ ረመዳን የመጨረሻው እንደሆነ ብንመለከት ምን እናደርግ ነበር? አልያም.... ይሄ ረመዳን የመጨረሻችን እንደሆነ እያየ ምንም ባይለን ምን ይሰማን ይሆን ? ብዬ አሰብኩ...

.....አለ አይደል?.... በሚለዋወጥ አላቂ አለም ውስጥ የማይለወጥ ተደጋጋሚ እኛነት። የመጣውን ስለመጣብን ብቻ መቀበል... የለመድነውን ዑደት መደጋገም... ሲሄድ በግድየለሽነት መሸኘት። ቆይ ከዚ በኋላ ባይመጣስ?.... ለአንዴ እንኳን "ረመዳን ስለደረሰ አውቄም ሆነ ሳላውቅ...." በሚል መልዕክት ፈንታ "....ያ አኺ ፊላህ... ይሄ ረመዳን የመጨረሻችን ይሁን አይሁን ስለማላውቅ በህይወታችን አሳልፈነው የማናውቀው አይነት ልዩ የዒባዳ ወር እንድናሳልፍ ልጠይቅህ ወደድኩ። አድርገነው የማናውቀው አይነት ልዩ ቃል እንገባባ። አደራህን ባሁኑ ለለይል ካልተነሳሁ ቀስቅሰኝ... ተራዊህ ላይም ካልተያየን ተደዋወለን እንተዋወስ... ቁርዓንን ደጋግሞ ከማኽተሙ እንለፍና እንማማረው... የመጨረሻችንም አይደል?... በቀን ውስጥ አላህን ባስታወስናቸው ሰዎች ቁጥር እንፎካከር... መጥፎ ቃል የወጣንም እንደሆን አሁን በምንገባባው ቃል ታስረን ሰደቃ እንስጥበት... እንደውም የተመደበች የሆነች ሰደቃን ያልሰጠንበት ቀን እንዳያልፍ.... የመጨረሻችንም አይደል? ምናልባት ከዚያ በላይ ረመዳኖችን እንድንኖር ተፅፎልን እንደሆንና ተኮራርፈን ቢሆን እንኳ... 'ያኔ ባሳልነፍነው 30 መልካም ቀናት ትዝታ' ስም ያለ ቴክስት አማላጅ አፉ እንባባላለን።" የሚል መልዕልት ቢደርሰኝ ተመኘሁ።

ያ ኡመተል ሀቢብ.... አላፊ የሆኑ ወዳጆቻቹንና... መጪዎቹን የሚቆጠሩ ቀናት አደራ...

@heppymuslim29


ማታ ላይ ከመተኛቷ በፊት ስትኳካል አይተዋት
"ምንድነው በእንቅልፍ ሰዓት እንዲህ የምትቀባቢው?" አሏት።
"አስከሬን እያበጃጀሁ፤ ለገናዦቼ ሥራ እያቃለልኩ ነው " አለች አሉ አንዷ እብድ።

አስክሬን ነንና ዉዱእ አድርገን፣ በልቦናም ንፁህ ሆነን፣ አዝካሮችን አድርገን፣ የምድር ላይ የመጨረሻ ንግግራችንን አሳምረን እንተኛ።

@heppymuslim29


የሻእባን መባቅያው ላይ ቆመን የረመዳን መግቢያን በጉጉት ስንጠብቅ... ጨረቃይቷ እንደ ፈገግታ ብቅ ብላ የራህመቱን ወር መዝለቅ ታበስረናለች።
:
ከሙዕሚኖች ልቦና ውስጥ ጥላቻና ቂምን ነቅላ ይቅርታን የምታነግስ ፡ የመኳረፍን ተራራ ንዳ የመከባበርና መዋደድን ድልድይ የምትገነባዋ!! ሁሉም ለይቅርታ ልቡን በሰፊው ከፍቶ ሁሉንም ይቅር ብያለሁ ፡ እኔም ሰው ነኝና በውልክፍክ አረማመዴ ያስቀየምኳቸው ሁሉ አውፍ ይበሉኝ!! ይላል..ረመዳን አንድ ጣቱን ሲያስገባ።
የይቅር ባይነት ሚዛናችን ሀቢባችን (ሰዐወ) ናቸው!

እነሆ ልባችንን ለይቅርታ በሰፊው ከፍተናል!! በህይወታችን ላይ እሾህ ሆናችሁ ማይፋቅ ጠባሳን ማይረሳ ህመምን፣ ማይሽር ቁስልን ያስታቀፋችሁን : ትንሽ ትልቁን ህመማችንን ትተን ለአሏህ ብለን ይቅር ብለናችኋል!!
ለምን አትሉንም??
ተፈቃሪያችን ﷺ እንዲህ ነበሩና !!

ለአሏህ ብለን
ይቅር ብለናል....

••ረ መ ዳ ን••
@heppymuslim29


አባት: ልጄን እንዴት ባሳድገው ነው አላህን ሚፈራ ሷሊህ ሚሆንልኝ?

ጠቢቡ: እድሜው ስንት ነው !?

አባት: ሰባት ወሩ ነው

ጠቢቡ: ዘግይተሃል!!! ልጆችን ሷሊህ አድርጎ ማሳደግ ሷሊህ እናት ከመምረጥ ነው ሚጀምረው።
.
.
.
እና ልላችሁ ምፈልገው ሚስት ስትመርጡ ቆንጆ ብቻ አትበሉ። እናት መሆን ምትችል, ዲን ያላት የሆነች, ሠላማዊ የሆነች, አላማችሁን ምትደግፍ .........ጨምሩበት☺️

@heppymuslim29


አስተውል አንተ የአላህ ባሪያ
=================

~ ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።

~ ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።

~ እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ እውነተኛ ሁን!

~ የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!

~ ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።

~ ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!

~ ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!

~ መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።

~ ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!

~ ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።

~ መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ!!

@heppymuslim29


በአንድ ወቅት ነቢ ሱለይማን ዐለይሂ ሰላም አንዲት ጉንዳን ከድንጋይ መሃል ያገኛሉ ። ጉንዳኗም አብሯት አንድ ፍሬ ስንዴ አጠገቧ ነበር ። ነቢ ሱለይማንም " እዚህ ድንጋይ መሃል እየኖርሽም አሏህ ይረዝቅሻልን ? " ብሎ ይጠይቋታል ። እርሷም " አዎን አሏህ ምን ይሳነዋል ? " ብላ መለሰች ። ለመሆኑ ይህች አንዷ የስንዴ ፍሬ ለምን ያክል ጊዜ ትበቃሻለች " ሲሉም ይጠይቋታል ። እርሷም " ለአንድ ዓመት ይበቃኛል !! " ስትል መለሰች ነቢዩ ሱለይማንም ዐለይሂ ሰላም " እስቲ እኔ ዘንድ ለአንድ አመት ላቆይሽ " ብለው በመውሰድ አንድ የስንዴ ፍሬ ሰጥተው ያስቀምጧታል።
በአመቱም ጉዷን ለማየት ወዳለችበት ሲሄዱ ግማሹን የስንዴ ፍሬ በልታ ግማሹን አስቀምጣዋለች ። ነብዩ ሱለይማይን ተደንቀው " ለአንድ ዓመት አንድ የስንዴ ፍሬ ይበቃኛል ብለሽኝ አልነበረምን ታዲያ ግማሹን በልተሽ ግማሹን ለምን ተውሽው ? " ሲሉ በአግራሞት ይጠይቋታል ። እርሷም " መጀመሪያ ለአንድ አመት አንድ ፍሬ ስንዴ ይበቃኛል ያልኩት እኮ በአሏህ እጅ ላይ ሆኜ ነው !! አሁን ግን ባንተ እጅ ስለገባሁ ሰው ነክና ልትረሳኝ ትችላለክ ብዬ ግማሹን በልቼ ግማሹን ደግሞ ለምናልባት ብዬ አስቀረሁት " ስትል መለሰችለት ።


ተወኩልን ከጉንዳን ተማር ሪዝቅህ በአሏህ እጅ እንደሆነ እወቅ።
@heppymuslim29


ከጥሩ ጋር ዋል ጥሩ ትሆናለህ..!

አንድ አባት ከስራ ቦታው ሲመለስ ልጁን ከቦዘኔ ልጆች ጋር ሲጫወት ያየዋል ልጁን ጠራውና ልጄ ተው ከነሱ ጋር አትዋል ያበላሹሀል አለው።  ''ኧረ አባቴ እኔ ከነሱ ጋር ጨዋታ ብቻ ነው ምጫወተው እነሱ ሚሰሩትን መጥፎ ስራ አልሰራም'' ሲል መለሰለት እና በተደጋጋሚ ቢመክረውም እንቢታውን ቀጠለበት። አባት ከቀናት ቡሀላ ከስራ ሲመለስ በካኪ ወረቀት የሆነ ነገር ይዞ መጣ እና እንካ ሳጥን ላይ አስቀምጠው ብሎ ሰጠው።

ልጁም አባቱ ያመጣውን ለማየት ጓጓና ከፍቷ አየው ልጁ ተደሰተ ያለበሰለ ፖም ነበር በዛ ላይ አንዷ ፍሬ ተበላሽታለች አና ላውጣት ተበላሽታለች ሲል አባቱን ጠየቀው አይ ተወው ዝም ብለህ አስቀምጠው አለው። እናም ከሳምንት በኋላ እስቲ ያንን ያስቀመጥከውን ነገር አምጣው አለው እናም ልጁ በጉጉት ይጠብቅ ስለነበር ደስ አለው ፖም እንደሚወድም ስለሚያቅ ልጁም ተስፈንጥሮ ተነስቷ አመጣና በጉጉት እና በተስፋ ካኪውን ከፈተው።

ነገር ግን ሁሉም የፖም ፍሬዎች ተበላሽተው ነበር ልጁ በጣም ተናደደና አየሀ አባዬ ያኔ የተበላሸውን የፖም ፍሬ ላውጣው ስለህ እሺ ብትለኝ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም አለው አባትም ሌላ ካኪ ወረቀት አመጣና ሰጠው አሁንም ደስ ብሎት ከፍቶ ሲያይ ፖም ነበር ነገር ግን አባቱ አሁንም ያመጣው አልበሰለም እና ልጅ አልበሰለም እኳ ሲል ጠየቀው  አባትም አዎ  ሂድ ሳጥኑ ላይ አስቀምጠው አለው ልጅም እሺ ብሎ ከማስቀመጡ በፊት የተበላሸ እንደሌለው አረጋግጦ አስቀመጠው።

አሁንም ከሳምንት ቡሀላ አባት እስቲ ያንን ነገር አምጣው አለው ልጅም በደስታ እና በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኖ ካኪውን አመጣው የፈራው እንደበፊቱ እንዳይበላሽ በመስጋቱ ሲሆን ደስ ያለው ደሞ ፖም ስለሚወድ ነበር እና ልጅ ካኪውን ከፈተው ማሻአላህ ሁሉም ሳይበላሽ በስለው ነበር ልጅም በጣም ደስ ተሰኘ እና  አባት ያኔ ፖም ለምን የተበላሸ ይመስልሀል? ሲል ጠየቀው ልጅም "አንዱ ተበላሽቶ ስለነበር ሁሉንም አበላሻቸው እኔ ላውጣው ስልህ ባወጣው ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር" አለው።

አባትም  "አየህ እኔም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ምልህ ለዚ ነው ልክ እንደ ፖሙ ሁሉ አንተንም በጊዜ ሂደት እንዳያበላሹህ ነው የተበላሸውን ፖም ላውጣው ስትለኝ አውጣው ብልህ ኖሮ ሁሉም አይበላሽም ነበር አንተም ከመጥፎ ጓደኞች ጋር አትዋል ስልህ ካልዋልክ አትበላሽም ነገር ግን የኔን ምክር ችላ ብለህ ከነሱ ጋር ከዋልክ በጊዜ ሂደት እንደነሱ መሆንህ አይቀርም : በሌላ ቀን የመጣሁት ፖም ደግሞ ያልተበላሸው በአጠገቡ የተበላሸ ነገር ሰለሌለ ነው ከጥሩ ነገር ጋር ስላለ ነው ሰለዚህ አንተም ከጥሩ ጋር ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ"።  "ከጥሩ ከዋልክ ጥሩ ትሆናለህ: ከመጥፎ ጋር ከዋልክ መጥፎ ትሆናለህ።


@heppymuslim29


ልጅቱ ባለሙያ ጓደኛዋን ልትጎበኝ እና የዓሳ ጥብስ አሰራር ልታሳያት ቤቷ ትሄዳለች ። ጓደኛዋም ዓሳውን ከጭንቅላቱ እና ከጭራው ቆራርጣ መጥበሻ ላይ ስታደርግ ትመለከታለች ።

" ለምን ቆረጥሽው " ብላ ስትጠይቃት
" እናቴ ስትቆርጥ አይቼ ነው ። ቆይ እናቴን ልጠይቃት " ትልና እናቷ ጋር ትደውላለች ።

እናትም ...
" እኔም እናቴ ስታደርገው አይቼ ነው ማደርገው ፣ ቆይ ልጠይቃት " ብላ እናቷ ( የልጅቱ አያት) ጋር ትደውላለች ።

አያትየውም ...
" እኔ ዓሳውን እምቆራርጥ የነበረው መጥበሻው ሙሉውን ስለማይዝልኝ ነበር! " በማለት መለሰችላት።

☞ እና ምን ለማለት ነው? .... ምክንያታዊ እንሁን ፣ እንጠይቅ ፣ እንረዳ የተባለውን ሳንረዳ አናስተጋባ ።

@heppymuslim29


አንድ የ30 አመት ጎልማሳ ብዙ ከወላወለ በኋላ እድሜ ልኩን ሲመኘው የነበረን የምህንድስና ትምህርት ለመማር ለምዝገባ ወደ አንድ ኮሌጅ ሄደ፡፡ ቢሮ እንደገባ የተማሪዎች አማካሪ አገኘውና ሲያማክረው “በመማርና ባለመማር መካከል ብዙ ወላውያለው ” አለው፡፡

አማካሪው ምክንያቱን ሲጠይቀው፣ “አሁን 30 አመቴ ነው፡፡ ስመረቅ እኮ 35 ሊሆነኝ ነው” በማለት የመወላወሉን መነሻ ምክንያት ነገረው፡፡

አማካሪው የመለሰለት መልስ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወደ ትምህርት ገፋው፡፡ “የዛሬ አምስት አመት እኮ ብትማርም ሆነ ባትማር 35 አመት መሙላትህ አይቀርም፡፡ ሳትማር 35 አመት ከሚሞላህ፣ ተምረህ ቢሞላህ አይሻልም?”

እስቲ አንድ ጊዜ ጸጥ በሉና እድሜያቹ ስንት እንደሆነ አስቡት፡፡ ከዚያም በአሁኑ እድሜያቹ ላይ አምስት አመት ደምሩበት፡፡ ድምሩ ስንት መጣ?

ብትማሩም ባትማሩም እድሜያቹ መጨመሩ አይቀርም ሳትማሩ እድሜያቹ ከሚጨምር ተምራቹ እድሜያቹ ቢጨምር የተሻለ ነው ።

በሉ ተንቀሳቀሱ!!
@heppymuslim29


አንዲት አባቷ የመስጂድ ኢማም የሆነች ልጅ ነበረች። ልጁ በቁንጅናዋ ተማርኮ ዚና እንዲሰሩ ይጠይቃታል፤ ቆንጆይቱም "እሺ ነገር ግን ሁለት መስፈርቶች አሉኝ እነርሱን ካሟላህ " ትለዋለች። መስፈርቷንም በዚህ መልኩ ትነግረዋለች።
1ኛ) ትንሽ ጊዜ ስጠኝ።
2ኛ) እንደምታቀው አባቴ የመስጅድ ኢማም ነው እና ስጠኝ እስካልኩህ ጊዜ ድረስ መስጂድ እየሄድክ በጀምዐህ ሶላትህን ስገድ" ትለዋለች።
:
ልጁም እሺ ብሎ ተስማማ።
ቃሉንና መስፈርቱን ለመጠበቅ ሲል መስጂድ መሄድን አዘወተረ።

በመጨረሻም የሰጣት ጊዜም አለቀ።
"ያንን የሰጠሁህን መስፈርት ተገበርከው ቃልህንስ በትክክል እያከበርክ ነው"? የሚል ጥያቄ አነሳችለት።
እርሱም "አው! እየተገበርኩ ነው ነገር ግን ቃል ያስገባሁሽን ነገር አሏህ ይቅር ይበለኝ። ሁሉም ነገር ተቀይሯል። መስጂድ በምመላለስበት ሰዓት ወደ አሏህ ተመልሻለሁ" አላት።

አርሷም "ማሻ አሏህ! እኔም እሺ ያልኩህ ዝሙት ለመስራት ሳይሆን "ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለች" በሚለው በዚህ በአሏህ ቃል እርግጠኝነት ተሞልቼ ነው።

اتْلُ مَا أُوحِيَ إِلَيْكَ مِنَ الْكِتَابِ وَأَقِمِ الصَّلَاةَ ۖ إِنَّ الصَّلَاةَ تَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ ۗ وَلَذِكْرُ اللَّهِ أَكْبَرُ ۗ وَاللَّهُ يَعْلَمُ مَا تَصْنَعُونَ
ከመጽሐፍ ወደ አንተ የተወረደውን አንብብ፡፡ ሶላትንም ደንቡን ጠብቀህ ስገድ፡፡ ሶላት ከመጥፎና ከሚጠላ ነገር ሁሉ ትከለክላለችና፡፡ አሏህንም ማውሳት ከሁሉ ነገር በላጭ ነው፤ አሏህም የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃል፡፡
📒ሱረቱል ዐንከቡት (45)

@heppymuslim29


እንዴት ሰለምክ? በማለት ነበር ጋጤዘኛው የጠየቀው። አይኑን ሰበር አንገቱን አጠፍ አድርጎ አቀረቀረና ንግግሩን ጀመረ
 "የዘመን ቀመሩ ሲፈተል በ1993 ከዕለታት በአንዱ ቀን ከባለቤቴ ጋር ለመዝናናት ራቅ ብለን ተጓዝን። ዛፍ ቅጠሉን ጋራ ሸንተረሩን እያቆራረጥን አንድ መንደር ስንደርስ መሽቶ ነበርና መመለሻው መንገድ ጠፍቶን እየኳተንን በርሀብ ነደድን። ከአላፊ አግዳሚዎቹ አንዱን የሚበላ ነገር የምናገኝበትን ደህና ሆቴል እንዲጠቁመን ጠጋ ብለን ጠየቅን። አለባበሳችንን ተመለከተና እንግዳ መሆናችንን አስተዋለ"ደህና ሆቴል የለም። ምግብ ቤትም ቢሆን በዚህ ሰዓት ዝግ ነው። ወደ ከተማ ለመመለስ ደግሞ መሽቷል። ሰዓቱ የጅብ ነው። ባይሆን ወደ እኔ ቤት እንሂድና ራታችሁን በልታችሁ ታርፋላችሁ። ጠዋት ሲነጋ መንገዱን አሳያችኋለው" አለን።

ወደ ቤቱ ወሰደን። አንዲት ደሳሳ ጎጆ ውስጥ አስገባን። ጨለማ ነው። ትንሽዬዋ ጠረጴዛ ላይ ያለው ፋኖስ ይንቀለቀላል። አምስት ሕጻናትና ሁለት አዛውንቶችን ከአንድ ጥግ ተቀምጠዋል። ግርግዳ ማገሩን እያየን ቀለል ያለ መጠነኛ እራት አቀረበልን። በልተን ስንጨርስ "አንተና ሚስትህ እዚህ አልጋ ላይ በነፃነት እረፉ። እኔና ቤተሰቤ ሌላ ክፍል ውስጥ እንተኛለን" በማለት ተሰናበተን።

ለሊቱን በበቂ ሁኔታ ተኛን። ማለዳ ጎህ ከመቅደዱ በፊት ነቃን። ላደረገልን መልካም ነገር ልናመሰግነው ከተኛንበት ክፍል ለባብሰን ወጣን። ሌላ ክፍል ግን አላገኘንም። አይኔን ወርውሬ ስመለከት ሰውየው አንዲት ዛፍ ላይ ተሰቅሏል። ከስሩ ደግሞ ቤተሰቦቹ ተጎዝጉዘዋል። ህፃናቶቹም ኩርምት ብለው ሽፋሽፍቶቻቸውን ከድነዋል።

ባለቤቴ በሁኔታው አለቀሰችች። በዚያ ቀዝቃዛ አየር እንዴት ለማያውቁት ሰው ውጪ ማደርን ምርጫቸው ያደርጋሉ። እስልምና ለእንግዳ ያለው ቦታ ገረመን።  "ይህ የምናየው እስልምና ከምንሰማው ፍፁም ይለያል" ተባባልን። ወደሰውየው እየተንጠራራሁ እስልምናን እንዴት ማወቅ እችላለሁ በማለት ጠየቅኩት።
"የቁርአን ትርጉምና  አንዳንድ መፅሐፎችን ገዝተህ አንብብ" አለኝ የዛፉ ቅርንጫፍ ላይ ተጋድሞ ቁልቁል እየተመለከተኝ።

ወደ ሀገሬ እንደተመለስኩ ስለ እስልምና ለማወቅ በርካታ መፅሐፍትን ሸማመትኩ። ለተከታታይ ሁለት ወራት በጥሞና ተቀምጬ አነበብኩ። ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለና ሙሐመድም የአላህ መልእክተኛ መሆናቸውን በእውነት መሰከርኩ። እኔን ምክንያት አርጎ ከአንድ ሺህ የሚበልጡ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ። አሁን በሀገረ ሩማንያ እስላማዊ ማዕከል እየገነባሁ ነው።  እስልምናን በአለም ላይ ለማስፋፋት ኢንሻ አላህ እተጋለሁ።

በመልካም ስነ ምግባር ዳዕዋ ማድረግ እንዲ ነው።

@heppymuslim29


" የኾነ ጊዜ መግሪብ ሶላት ወደ መስጅድ እየሄድኩ ከፊቴ አንድ የማዉቀዉ ወጣት ተቀድሞኝ ነበር። በጎኔ በኩል ደግሞ ሁለት ሴቶች እያወሩ ይሄዳሉ።

አንደኛዋ ሴት ወደ መስጅድ የሚገቡ ሰዎችን ተመልክታ 'አዛን ሲሰማ ወደ መስጅድ የሚቻኮል ወጣት ሳይ ደስ ይለኛል' አለች።

ይሄን የሰማዉ ከፊቴ ያለዉ ወጣት ወደ'ነሱ ዘወር ብሎ 'ሁሌም ዱዓዬ መስጅድ ስመላለስ የምትወድልኝን ሚስት ስጠኝ ነዉ። ስልክሽን ስጭኝና ከሶላት በኃላ ልደዉልልሽ?' አላት። ሴቶቹም እኔም በሳቅ ወደቅን። ካላመንሽ ይሄዉ ምስክሬ ብሎ እኔኑ ያዘኝ። እዉነት ነዉ በተደጋጋሚ መስጅድ አየዋለሁ ግን ምን ብዬ ልመስክር።

'አይደል?' አለኝ። እኔም መስጅድ በተደጋጋሚ እንደማየዉ ተናግሬ በቆሙበት ትቻቸዉ ወደ መስጅድ ገባሁ።

.. ያ ወጣት ያችኑ ልጅ ያለፈዉ እሁድ እንዳገባት ሰማሁ። አንዳንድ አጋጣሚዎች ዓጂብ ናቸዉ " አሉ ሀጂ

@heppymuslim29


....አንድ ጊዜ አልሃጃጅ ኢብን ዩሱፍ ወደ ጌታው የሚማፀን አይነስውር ያያል ይባላል። ምን ሆኖ ነው ሲልም ይጠይቃል። አላህ "አይኑን እንዲያበራለት እየጠየቀ ነው" ሲሉ ይመልሱለታል። አይነስውሩ አንዴ ልብሱን እየነካካ አንዴ ፀጉሩን እያሻሸ ዱዐ የሚያደርግበት ሁኔታ ያን ያህል ያመረረ እንዳልሆነ ያስታውቅ ነበር። አልሃጃጅ በዘመኑ ጨካኝ ከሚባሉ መሪዎች አንዱ ከመሆኑ ጋር በሁኔታው ተበሳጭቶ ወደ ሰውየው ይጠጋና "እኔን አውቀኸኛል?" ሲል ይጠይቀዋል። አይነስውሩም በመርበትበት "አዎ፣ እንዴታ! እርሶን የማያውቅ ማን አለ" ሲል ይመልሳል። አልሃጃጅም... "እስከ ፈጅር ጊዜ ሰጥቼሃለው። ፈጅር ላይ አይንህ በርቶ ባላገኘው በአላህ እምላለሁ አንገትህን ህዝብ ፊት ነው የምቀላው" ብሎት ይሄዳል። አይነስውሩ ከፍርሃቱ ሌሊቱን ሙሉ እያለቀሰ ጌታውን ከዚ ጉድ እንዲያወጣው ሲማፀንና ሲዋደቅ ያድራል። በነጋታው ጠዋትም አይኑ በርቶ ያገኘዋል። አልሃጃጅም... "ዱዐ ማለት እንዲ ነው" አለው ይባላል።


.....ጀባሩ በዱዐቸው ላይ ለነፍሱ እንደሰጋው አይነሰውር ችክ ብለው በሰጪነቱ ላይ ተስፋ የማይቆርጡትን ይወዳል። ፊርደውስ በሳምንት አንዴ በሚሰገድ ጁምዐ፣ በአመት አንድ ወር በሚቆምበት የረመዳን ዱዐ ብቻ አትገኝም።

@heppymuslim29


ተፍሲር ላይ ነበርን። ኡስታዙ ሱረቱል ዩሱፍን እየዳሰሰልን የዩሱፍን "እነርሱ ከሚጠሩኝ የበለጠ እስር ቤት እኮ ለኔ የተወደደ ነው" የሚለውን አያህ እያነሳ "እርግጥ ዩሱፍን እስር ቤቱ ለትልቅ ስኬት ቢያመቻቸውም ከዚህ የምንረዳው ግን አላህ ዱዓን እና ምኞትን በየትኛውም ሰዓት ስለሚመልስ ዱዓችሁ እና ምኞታችሁ ላይ ጠንቃቃ ሁኑ!" አለን
ምን አስታውሼ መሰላችሁ? የ ፉዓድ ሙና ጽሁፍ ላይ የትኛው እንደሆነ እርግጠኛ አይደለሁም( ስለ ገጣሚያን ያነሳው ይመስለኛል) "አምሪያ" የምትባል ገፀ ባህሪ የሆነ አይነት የጓደኛሞች ግሩፕ አላት እና በየወሩ የቁርአን ኺትማ ፕሮግራም እንዲሁም በወሩ ላይ ከነሱ እኩል ያልቀራችውን ደስ የሚል ቅጣት የሚቀጡበት ደስ የሚል ስብስብ አነበብኩ። "ምናለ እንዲህ አይነት ግሩፕ በኖረኝ" ማለቴን እርግጠኛ ነኝ። "ስጠኝ!" ብዬ ዱዓ ማድረጌን ግን እንጃ። አላህ ግን አመታትን ቆይቶ ተመሳሳዩን ነገር በኔም ህይወት ላይ ሰጠኝ እና "ካንተ ውጪ በ እውነት የሚያመልኩት አምላክ የለም! ብዬ አመሰገንኩት። እና የተመኘሁትን የሰጠ አላህ የለመንኩትን ይረሳል? በፍጹም!!!

እና ልላችሁ የፈለግኩት በዱዓችሁ ላይ በምኞታችሁ ላይ ጌታችሁን እመኑት እና ለምኑት! ምናልባት ነገ ወይም ከ አመታት በኋላ እንደኔ ትመሰክላችሁ

@heppymuslim29


< ከዘመናት በፊት አንድ ባለ ሀብት ነበር። ይህ ባለ ፀጋ ድንገት በአንዱ እለት አንዲትን ውብ ባሪያ ይመለከታል። ባለ ፀጋው በውበቷ ስር ወደቀ። በነጋ በጠባ ቁጥር ምስሏ በምናቡ ይመላለሳል። ትውስታዋ ከልቦናው ሊፋቅ ተሳነው። የፍቅሯ ታሳሪ ሆነ። በፍቅርና በናፍቆት መሀል የምትናወጥ ልቡን ይዞ ወደ አሳዳሪዋ አመራ። ባሪያይቱን ከፍ ባለ ገንዘብ ሊገዛት ጠየቀው። የባሪያዋ አሳዳሪም ባለ ፀጋው ከባሪያዋ ጋር በፍቅር መውደቁን ከአይኖቹ ተረዳ። አሰብ አደረገና። " አይ በዚህ ዋጋ አትሸጥም! " በማለት ያለውን ሁሉ አስረክቦ ባሪያይቱን እንዲገዛው አደረገ። ባለሀብቱ የለበሰውንም ባርኔጣና ኩታን ሳይቀር አስረክቦ ተፋቃሪውን ይዞ ተጓዘ። >

  አየህ አይደል! አፍቃሪ ላፈቀረው ነገር ያለውን ሁሉ ይሰዋል። ሚሰዋው ቢጠፋ የቀረችው አንዲትን ነፍስ እንኳን ብትሆን እርሷንም አይሰስትም። የርሱ መሻት የተፈቃሪው ደስታና ውዴታን መጎናፀፍ ነው። ታድያ በፍጡራን መካከል ላለ አላቂ ፍቅር ይህን ያህል ቤዛ የሚደረግለት ከሆነና ሀብትና ንብረትን እስከማጣት ካስደረሰ ፡ ስለምን የጌታህን ፍቅር ያለ ምንም ክፍያ ትሻለህ? ክልከላውን ስትዳፈር ልብህ ላይ ያለው የማፍቀር ሂማ እየሞት እንደሚጠፋ ተሰወረህ? የትዕዛዙን በትር ስትይዝ የኩራትን ኩታ ከደረብክም በራስህ ላይ የፅልመት ካባን ነው የደረብከው። እኔነትህን ጥለህ ቅረበው። መሻትህን ግደለው። ምንምነትህን ገልጠህ ከዱንያ ፍቅር ተራቁተህ ቅረበው። ጣላት ይህችን ነፍስ! ተዋድቀህ የእውነት ሚስኪንና አሳዛኝ ባሪያ ሁንለት። እንዲያ ነው ፍ ቅ ሩ ን የምታገኝ!

(አብዱ ሩሚ)

@heppymuslim29


"ኃጢአተኛ ሰው ኢማም ሆኖ ማሰገድ ይችላል ወይ?" አላቸው ከመስጊዱ ሰዎች መካከል አንዱ።

"አላህ ሰትሮት ነው እንጂ ይህ ፊት ለፊታችሁ ቆሞ የሚመክራችሁ ሰው ጭምር ከጥፋት የፀዳ ይመስችኋልን?" አሏቸው ኢማሙ።

@heppymuslim29


የገባሁበት ታክሲ ሊሞላ የኋለኛው ወንበር ብቻ እንደቀረው አንዲት ልጅ ያዘለች ወጣትና ልትሸኛት የተከተለቻት ሌላ ሴት አብረው መጡ።ባለ ልጇ ጠጋ ብላ የኋላ ወንበር መሆኑን አይታ ተመለሰች።ወደኔ ዞር ብላ "ትቀይሪኛለሽ?"ስትለኝ፣ወደኋላ እየጠቆምኩ "እዛ ጋርኮ ቦታ አለ" አልኳት።ቆጣ ብላ "ልጅ ይዤ እንዴት ነው እዛ 'ምቀመጠው?አይታይሽም?...ለነገሩ ተሸፍነሻል እንዴት ይታይሻል?¡"አለችና ወደኋላ አለች።(ሶስተኛ ሰው ቢደርቡ ላይመቻት ይችላል፣ይበልጥ የሚሻላትም ያ ነው ብዬ ነበር እንደዛ ማለቴ)።ንግግሯ ሰውነቴን ቢነዝረኝም ፊቴን ከሷ አዞሬ የታክሲውን መሙላት ተጠባበቅኩ።ግን አላስቻለኝም።ምክንያቴን ሳልነግራት ባልፍ፣ከጥላቻዋ ሌላ ኒቃብ ያደረጉ እህቶችን በሙሉ ለሰው ባለማዘን ጎራ መመደቧ ነው ብዬ ወረድኩና ተጠጋኋት።...(ፋይዳ ላይኖረው ነገር!)
.
ገና ስታዬኝድምጿን በእጅጉ ከፍ አድርጋ ተንጨረጨረች።




ደገመችው።ብዙ አወራች።

አላስጨረሰችኝም።


.
ምንም ብላት ትርጉም አልባ መሆኑ ገባኝ።ላወራ አፌን ሳንቀሳቅስ በስድብ ትቀድመኛለች፣እኩል ባወራም ድምጿ ድምፄን ይውጠዋል።ትዕግስቴ ሲሟጠጥ

ጮክ ብላ እጇን ወዲያና ወዲህ እያወናጨፈች ደጋግማ አማተበች።

ደነፋች።ብዙ ጮኸች።

አሁንም አቋረጠችኝ።

ታቦቶቿን ጠራች።(መምራት ልል አልነበረም)።ከዚህ በላይ አንድ ቃል ማውጣት ጊዜዬን ማቃጠል ነው።ትቻት ሄድኩና ቀጣይ ታክሲ ውስጥ ገባሁ።
.
በሚያሳዝን ሁኔታ መንገዳችን አንድ ስለሆነ ጥቂት ቆይታ ገባችና ተቀመጠች።




.

.
ድምጿን ከፍ አድርጋ እኔን ለጎሪጥ እያየች፣ሲላትም የታቦቶቿን ስም እየጠራች ስድቧን ቀጠለች።እኔ ግን ምንም ማለት አልፈለኩምና ዝምታን መረጥኩ።
.
ሰው ሁሉ እየዞረ ያያታል(እንደጤነኛ አይመስለኝም ግን)
.

.
እንባዬን መቆጣጠር አቃተኝ።በጥላቻዋ ውስጥ እልፍ ጥላቻዎች፣በንቀቷ ውስጥ እልፍ መደፈሮች ታዩኝ።...ባለፈው አንዱ ሎንችን ውስጥ ልገባ "ወንበር አለ?"ብዬ መጠየቄን ሰምቶ "ወንበር ለተማረ ነው" ያለኝ ትዝ አለኝ።...ለወንድሜ ጉዳይ ትምህርት ቤት ሄጄ ጥበቃውን አቅጣጫ ስጠይቀው "ማንበብ ከቻልሽ የመምህራን ማረፊያ የሚል ተፅፎበታል" ያለኝም ታወሰኝ።
.
እንዲሁ እንደጮኸች መውረጃዬ ደርሶ ልወርድ ስነሳ፣
አለችኝ።
.
አልኳትና ወረድኩ።ሰማችኝና ለአፍታ ፀጥ አለች።እንባዬን ጠረኩና ጉዞዬን ቀጠልኩ።ድምጿ ግን ተከተለኝ...የዒምራን ሱራ ውስጥ ያለች አንዲት አያም በራሴው ድምፅ ትሰማኝ ጀመር።

***
لَتُبْلَوُنَّ فِي أَمْوَالِكُمْ وَأَنفُسِكُمْ وَلَتَسْمَعُنَّ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِن قَبْلِكُمْ وَمِنَ الَّذِينَ أَشْرَكُوا أَذًى كَثِيرًا ۚ وَإِن تَصْبِرُوا وَتَتَّقُوا فَإِنَّ ذَٰلِكَ مِنْ عَزْمِ الْأُمُورِ

በገንዘቦቻችሁና በነፍሶቻችሁ በእርግጥ ትፈተናላችሁ፡፡ ከእነዚያም ከእናንተ በፊት መጽሐፍን ከተሰጡትና ከእነዚያም ከአጋሩት ብዙን ማሰቃየት ትሰማላችሁ፡፡ ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ይህ ከጥብቅ ነገሮች ነው፡፡
***

@heppymuslim29


~አንዲት ሴት አጋጣሚዋን እንዲህ ትናገራለች

" የሆነ ጊዜ ኒቃብ መልበስ ፈለኩና ቤተሰቦቼን ሳማክራቸዉ አባቴም እናቴም ከለከሉኝ።ፍቃደኛ አልሆኑም ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ኒቃብ ለመልበስ ወስኜ ለበስኩ።ቤተሰቦቼ ኒቃቡን ሲመለከቱ ማንም ለትዳር አይጠይቅሺም፣መማር አትችይም፣መስራት አትችይም…እያሉ መጮህ ጀመሩ። የአላህ መሻት ሆነና በዛዉ ሳምንት ዉስጥ የሆነ ወጣት ለትዳር ጠየቀኝ። ኒካህ ታሰረ።

ባሌም የሆነ ቀን እንድህ አለኝ «ታውቂያለሽ ከ9 አመታት በፊት ነበር የምወድሽ።ኒቃብ እስከምትለብሺ ነበር የምጠብቀዉ። ልክ እንደለበሽ አንቺን ለማግባት መጣሁ» አለኝ። ከአምስት አመታት ብሃላ ቁርአን  በ10 አይነት አቀራር አስሀፈዘኝ በጣም አጋዤም ነበር። "

@heppymuslim29


በሙሳ ዘመን ነው....አንድ በጣም ድህነት ያጎሳቆላቸው ለዘመናት በችግር እና በረሀብ የኖሩ ባልና ሚስት ነበሩ።

ይሁን እንጂ ይህን ሁሉ ዘመናት በሰብር አሳልፈዋል...። እናም አንድ ቀን እቤታቸው ጋደም ብለው ሳለ ሚስት ለባለቤትዋ፦ "ሙሳ አላህን ማናገር የሚችል ነቢይ ነው አይደል?" ብላ ትጠይቀዋለች።

እሱም፦"አዎን" ይላታል። "ታዲያ ለምን እሱጋ ሄደን ስለ ሁኔታችን አንነግረውም አላህንም ስለኛ ያናግረው ሀብታም እንዲያረገን ቀሪ ህይወታችንን በድሎት እንድንኖርም ይጠይቅልን።" አለችው። ባልም በሚስቱ ሀሳብ ይስማማና ሌሊቱ እንደነጋ ጉዞ ወደ ሙሳ ዐ.ሰ ቤት ጀመሩ። ሙሳንም ዐ.ሰ አገኟቸው። ስለድህነታቸው ነግረዋቸውም በዚህ ጉዳይ እሳቸው አላህን እንዲለምኑላቸው ጠየቋቸው።

ሙሳም ዐ.ሰ አላህን ለመኑላቸው። አላህም፦"ሙሳ ሆይ! እኔ እነዚህን ሰዎች በችሮታዬ ለአንድ አመት ያህል ሀብታም አደርጋቸዋለሁ አንድ አመት ካለፈም ወደነበሩበት ድህነት እመልሳቸዋለሁ።"ብሎ መለሰላቸው።

እሳቸውም ጥንዶቹ ጋ በመሄድ አላህ ዱዓቸውን ሙስተጃብ እንዳደረገላቸው ሀብታምም እንደሚሆኑ ነግረዋቸው እናም ግን ለ አንድ አመት ቢቻ እንደሚቆይ አክለው ነገሯቸው። እነዚህ ምስኪኖችም የሰሙትን ማመን ተሳናቸው። በአጭር ግዜ ውስጥ ካለሰቡበት መንገድ ሀብታም መሆን ጀመሩ።ማንም ከሚኖረው የተሻለ ኖሮ መኖርም ጀመሩ።

እናም አንድ ቀን ይህች ብልህ ሚስት ለባሏ እንዲህ አለችው፦"ይህ ፀጋ ይህ ድሎት ለ አንድ አመት ብቻ እንደሚዘገይ ታውቃለህ አይደል? ስለዚህ በዚህ ንብረታችን አንድ መልካም ስራ እንስራ" ባልይውም በሀሳቧ ይስማማል።

ከዚያም በከተማዋ ግንባር ቦታ ላይ አደባባይ መልክ አንድ ትልቅ ቤት ይገነቡና 7 በር አበጁለት። ለሰውም መተላለፊያ ሰሩ። ቤቱ ተገንብቶ ካለቀ በኋላ እዛ ቤት ውስጥ ምግብ እያዘጋጁ ለአላፊ አግዳሚ ጠዋት ማታ ምግብ ይቀልቡ ጀመር...። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ወራት አስቆጠሩ።

ሙሳም በትኩረት ይከታተሏቸው ነበር። ማይደርስ ቀን የለምና ያ የተወሰነላቸው ቀን ቀጠሮውን ጠብቆ ከች አለ። እነሱ ግን የቀጠሮ ቀኑ ሁላ ትዝ አላላቸውም በስራቸው ተጠምደዋል። ያ ቀጠሮ ቀናቸው አለፈ እነሱ ግን ያው ናቸው ምንም አልቀነሱም ብቻ በስራቸው ተጠምደዋል....

ሙሳም ዐ.ሰ ባዩት ሁኔታ ተገርመው፦ "ያ ረብ ቃል የገበኽላቸው ለ አንድ አመት ሆኖ ሳለ እንዴት እስካሁን እልደኸዩም?"ብለው አላህን ጠየቁ። /እዚጋ እሳቸው ሰዎቹን ተመቃኝተው ሳይሆን የአላህን ሂክማ ለማወቅ ነው የጠየቁት/

ቸር የሆነው አላህም፦ "ሙሳ ሆይ! ለነዚህ ጥንዶች ከፀጋ በሮቼ አንዲትን በር ስከፍትላቸው...እነሱ ደሞ 7 በር ከፍተው ባሪያዎቼን መቀለብ ጀመሩ። ሙሳ ሆይ! እነሱ ይሄን ሲያረጉ አይቼ የከፈትኩላቸውን በር መዝጋት ከበደኝ"አለው።

@heppymuslim29

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.