🔶የኢኽላስ አሳሳቢነት
💎የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡-
” የውሙል ቂያማህ ከሰዎች መጀመሪያ ፍርድ የሚሰጣቸው ሦስት ሰዎች ላይ ነው፡፡ (አንደኛው) በዱንያ ላይ ሳለ በዲኑ ሰበብ ሸሂድ (ሰማዕት) የነበረው ሰው ይቀርባል፡፡ በሱ ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እሱም ያምናል፡፡ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ፡ እሱም፡- ባንተ መንገድ (በኢስላም ላይ) እስክሞት ድረስ ጠላትን ተጋደልኩ ይላል፡፡ ዋሸህ! እንተ የፈለግኸው እገሌ ጀግና ነው እንድትባል ነበር እሱም ተብሎልሀል ይባልና እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል፡፡ (ሁለተኛው ደግሞ) ሸሪዓዊ ዕውቀት የተማረውና ቁርኣን የቀራውም ይመጣል፡፡ በሱም ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እሱም ያምናል፡፡ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ፣ እሱም፡-ዕውቀትን ተምሬ ቁርኣንን ቀርቼ ሌሎችንም ላንተ ብዬ አስተማርኩ ብሎ ይመልሳል፡፡ ዋሸህ! እንተ የፈለግኸው እገሌ ዓሊም ነው፣ እገሌ ቃሪእ ነው እንድትባል ነበር እሱም ተብሎልሀል ይባልና እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል፡፡ (ሦስተኛውም) ሐብት የተሰጠው ሰው ይመጣል፡፡ በሱ ላይ የተዋለለትን ጸጋ ያስታውሰውና እሱም ያምናል፡፡ ታዲያ ምን ሰራህበት? ተብሎ ሲጠየቅ፡ እሱም፡- አንት እንዲለገስ የምትወደው አንድንም ነገር ላንተ ብዬ ብለግስ እንጂ ትቼ ያለፍኩት ነገር የለም ብሎ ይመልሳል፡፡ ዋሸህ! እንተ የፈለግኸው እገሌ ለጋስ (ቸር) ነው እንድትባል ነበር እሱም ተብሎልሀል ይባልና እሳት ውስጥ እስኪጣል ድረስ በፊቱ ይጎተታል፡፡”
📚(ሙስሊም ዘግበውታል)
🤲አላህ በተግባራችን ኢኽላስ ይወፍቀን
https://t.me/hidaya_multi