በጠገዴ ማክሰኞ ገብያ ከተማ ህዝባዊ የውይይት መድረኮች እየተካሄዱ ይገኛሉ።
በርኖስ ሚዲያ /ህዳር/10/2013 ዓ.ም
በክልል፣በዞንና በወረዳ ሀላፊዎች እንዲሁም በኮማንድ ፖስት አመራሮች አስተባባሪነት በርካታ ቁጥር ያለው የከተማው ነዋሪ በተገኘበት ውይይት ተካሂዷል። የአካባቢው ነዋሪዎች በውይይቱ እንደተናገሩት በአሸባሪው የትህነግ ቡድን ሰብዓዊና ዴምክራሲያዊ መብታውን ተነጥቀው ፣በቋንቋቸው እንዳይናገሩ በባህላቸው እንዳይኖሩ ፣አንዳቸው ከአንዳቸው በጥርጣሬ እንዲተያዩ በማድረግ ከወዳጅ ዘመዶቻቸው ጋር እንዳይገናኙ ሲደረጉ እንደነበር፣በአካባቢው ተሰሚነት የነበራቸውና ስለ ማንነታቸው ያቀነቅኑ የነበሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች ሲሳደዱና ሲገደሉ አንደቆዩ ያስረዳሉ።
አስተያየት ሰጭዎቹ እንደሚሉት አሸባሪውን ቡድን ለህግ ለማቅረብ እየተሰራ ያለው እንቅስቃሴ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረና አሁን ከትህነግ ጭቆና ቀንበር በመዉጣታቸዉ ደስታቸውን እጥፍ ድርብ እንደሆነ ገልፀዋል።
የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶ/ር ሙሉቀን ተገኘ በውይይቱ ማጠቃለያ እንደተናገሩት ወጣቶች አሁን ላይ የተገኘውን የነፃነት ድል ለማስቀጠል በመደረጀት አካባቢያቸውን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸው፣ማህበረሰቡ ተረጋግቶ የተለመደው ተግባሩን ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከማከናወን ጎን ለጎን መረጃዎችንና ጥቆማዎችን ለሚመለከተው አካል ማድረስ እንዳለበት እንዲሁም ለአካባቢ ሰላምና ደህንነት ሲባል ከተፈቀደላቸው አካላት ውጪ የጦር መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይቻልና ማንኛውም አካል ከምሽቱ 3:ዐዐ በሗላ መንቀሳቀስ የማይቻል መሆኑን አሳስበዋል።
ሀላፊው አክለውም እስካሁን ድረስ በምህረት ያልገቡ በወረዳው ሲያገለግሉ የነበሩ ፖሊሶች፣ልዩ ሀይሎች፣ አመራሮች፣ ፀረ ሽፍታዎችና ዞባዊ ሚሊሻዎች እስከ ህዳር 14 ድረስ ትጥቃቸውን አውርደው እጃቸውን ለመንግስት እንዲሰጡና በራሳቸው ፈቃድ ካልገቡ ግን ህጋዊ እርምጃ የሚጀመር እንደሆነና ቀጣይ መንግስት እንደመንግስት ጠንካራ አቋም በመያዝ ከማህበረሰቡ ጋር በመተባበር ለመስራት ጥረት የሚደረግ መሆኑን ተናግረዋል ሲል የጠገዴ ወረዳ መ/ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።
@bernosmedia24