ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት
~ ~ ~ ~ ~
ለሙስሊም ወንዶች ከነ ጭራሹ ሃይማኖት የሌላቸውን ሴቶች ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድላቸውም። ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ባጠቃላይ ማግባትም እንዲሁ የተፈቀደ አይደለም። ከዚህ ተለይቶ የሚወጣው እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት ብቻ ነው። ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ግን ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
.
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ ዝንባሌያችን ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
.
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግንኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ለቀጣይ ህይወት መሰናክል እንዳይሆን ያክል ብቻ ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል።
ቁርኣናችን ደግሞ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከታወቁት ጋር ብቻ ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።
ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው። ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ትዳር ፈፅመው ከዚያ ልጆቻቸው የከፈሩ ስንቶች ናቸው? አንዳንዶቹ እንደዋዛ ልጆቹ 18 አመት ሲሞላቸው ሃይማኖታቸውን ይመርጣሉ ይላሉ። ይሄን ሁሉ አመት ኢስላምን አልተማረም፣ ሶላት የለም፣... ። በዚያ ላይ ለልጆች ከአባቶች ይልቅ እናቶች የበለጠ የቀረቡ ናቸው። ጊዜው አይነቱ የበዛ የሞራል ዝቅጠት የተንሰራፋበት ነው። በነዚህና መሰል ምክንያቶች የተነሳ ልጆቹ ኢስላምን የመያዛቸው እድል የመነመነ ይሆናል። እንዲህ አይነት ከባቢ ባለበት ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይፈቀድም።
.
ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523]
እንዲያውም ኢስላም አላህን መፍራትና ግብረ ገብነት ያላቸውን ሴቶች እንዲያገቡ ነው ወንዶችን የሚያነሳሳው። ይህንን ህግ መጠበቅ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ለሚወለዱ ልጆችም፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም፣ ለኢስላምም ውለታ መዋል ነውና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor